DiscoverDW | Amharic - Newsየአሜሪካን የኢሚግሬሽን ባለሥልጣናት ሚኒሶታ የሚኖሩ ሶማሊያውያንን ማሰር መጀመራቸው ስጋት አሳድሯል
የአሜሪካን የኢሚግሬሽን ባለሥልጣናት ሚኒሶታ የሚኖሩ ሶማሊያውያንን ማሰር መጀመራቸው ስጋት አሳድሯል

የአሜሪካን የኢሚግሬሽን ባለሥልጣናት ሚኒሶታ የሚኖሩ ሶማሊያውያንን ማሰር መጀመራቸው ስጋት አሳድሯል

Update: 2025-12-04
Share

Description



የአሜሪካ የኢሚግሬሽን ባለሥልጣናት፣ በሚኒሶታ ግዛትበሚገኘው ሰፊ የሶማሊያ ማኅበረሰብ ውስጥ ዘመቻ እንደሚጀምሩ እየተነገረ ባለበት ሁኔታ፣ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ደግሞ ሶማሊያውያን ስደተኞች አሜሪካ ውስጥ እንዲኖሩ እንደማይፈልጉ ከሰሞኑ ተናግረዋል።



ይህ ሁኔታ በሚኒሶታ ግዛት በተለይ እርሷ በምትሰራበት ሆስፒታል አካባቢ የፈጠረውን ስጋት አስመልክቶ ፣በግዛቲቱ የሚኒያፖሊስ ከተማ ነዋሪ የሆነችውና ዶቸ ቬለ ያነጋገራት፣ሮዛ ዘውዴ ገልጻለች።



''ይሄ ነገር እንደተጀመረ ሆስፒታላችን ባዶ ነበር፣ በቃ ማለት ትችላለህ በጣም ባዶ።በቃ ሰው በጣም ፈርቶ አይመጣም ነበር፤ እና ይሄን ነገር በጣም ታዝቤያለሁ።ዛሬ በሽተኞቻችን ስማቸው እንደዚህ ያልተጻፈው ስል፣እንዲህ እንዲህ ነው አይሲኢ ስለሚመጡ ነው ሲሉኝ በጣም ነው የተገረምኩት፣ከሆስፒታል መጥተው ሊወስዷቸው ነው ማለት ነው? እያልኩኝ።''



እርምጃው የገጠመው ተቃውሞ



በእዛው አካባቢ፣ሶማሊያውያን ስደተኞችን አለአግባብ ማሳደድ እንዲቆም የሚጠይቅ ስብሰባ መካሄዱንም፣ሮዛ ተነግራለች።



"ጠንካራ ሰራተኞች ናቸው፤በሆስፒታል ውስጥም ብዙ ስራ የሚሰሩ ናቸውና ይህ ነገር እነሱ ላይ ጥቃት እንዲደርሳባቸው አንፈልግም፣ እኛ ለነሱ ድምፅ መሆን አለብን እና የሚቀጥለው ስብሰባ ሲኖር እኔ እንደውም ምን አልኳት በጣም ደስ ይለኛል በሚቀጥለው ሣምንት እሄዳለሁ አልኳት ለአንደኛዋ ነጭ ነርስ።''



ሶማሊያውያን ስደተኞችን ዒላማ ያደረገው ዘመቻ



የሕግ ባለሙያው አቶ ሙሉአለም ጌታቸው፣ በሚኒሶታ ግዛት የስደተኞች ጉዳይ ጠበቃ ናቸው። አቶ ሙሉአለም እንደሚሉት፣ከ80 እሰከ 100 ሺህ የሚገመቱ ሶማሊያውያን ስደተኞች በሚኖሩባት ሚኒሶታ ግዛት፣ የኢሚግሬሽን ባለሥልጣናት የከፈቱት ዘመቻ ብዙ ምክንያቶች አሉት ዋነኛውም፤



"እነዚህ ከዚህ ቀደም በኮቪድ ሠዓት ላይ ሚኒሶታ ላይ የነበሩና ከዛም ቀጥሎ ከኮቪድም በኋላ ተያይዘው የመጡ፣ በተለይ በኢኮኖሚ ዝቅተኛ የሆኑ ማኅበረሰቦች የሚደግፉ ፕሮጀክቶች ላይ ከተሳተፉ ሰዎች በብዛት ሶማሊያውያን ስደተኞች ይገኙበታል።እና በተሳተፉበት ሂደት ውስጥ ብዙ ገንዘብ ተመዝብሮ ነበር።ምርመራው በኋላ ላይ በፍትሕ ሚኒስቴር ሲመራ፣ ከተገኙት ውስጥ ትልቅ ገንዘብ የወሰዱት ሶማሌዎች ናቸው። እነዚህ ደግሞ ወደ ኬንያ እና ወደ ሦስተኛ አገር ገንዘባቸውን አሸሽተው ነበር የቻሉት ሰዎች ማለት ነው።ስለዚህ የሶማሊያን ማኅበረሰብ በአብዛኛው ማዕከል ያደረገው ወይም ወደ ዋሽንግተን ፖለቲካ ውስጥ ያመጣው ዋነኛው ይሄኛው ነው።''





በአሁኑ ሠዓት ጉዳዩን ለማጣራት ሶማሊያውያንስደተኞች በቁጥጥር ስር መዋል መጀመራቸውን የገለጹት የሕግ ባለሙያው እርምጃው ለኢትዮጵያን ስደተኞች ጭምር ከባድ ስጋት መሆኑን አመልክተዋል።



''እንግዲህ ሶማሊያዊ ስደተኛ በመሆንህ የምትታሰር ከሆነ፣ ለኢትዮጵያኖችም ከባድ ስጋት ሆኗል።ምክንያቱም በአብዛኛው ነጮቹ እውነት ለመናገር እዛ አካባቢ አይለዩም።ማነው ኢትዮጵያዊ ማነው ሱማሊያዊ የሚባለው ማለት ነው።ምንአልባት ሴቶችንና ወንዶችን አንዳንዴ የምትለይበት መንገድ የአለባበስ ስርዓታቸው ብቻ ነው።''



ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ማወቅ ያለባቸው



የሕግ ባለሙያው፣ቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት ምናልባትም በአሜሪካ ታሪክ በአስከፊነቱ የሚጠቀስ የስደኞች አያያዝ የሚታይበት ሊሆን እንደሚችል ይሰጋሉ።ከዚህ አኳያም በተለይ ለኢትዮጵያን ሰደተኞች ምክር አላቸው።



''አንደኛ ከሚገባው በላይ ድንጉጥ አለመሆን ጥሩ ነው።ማለት፣ እነዚህ ጊዜያት ያልፋሉ ያለጥርጥር ማለት ነው። ሁለተኛ መብታችንን ማወቅ ያስፈልጋል። ምንድነው አንድ ነገር ቢከሰትብን ብንያዝ እስከምን ጊዜ ነው የሚሄደው?ስንት ቀን ልታሰር እችላለሁ?ብታሰር ጠበቃ አለኝ ወይ ልደውልለት የምችለው ማን ጋር ነው የምደውለው?እነዚህ ዕውቀቶች ቢኖሩን ጥሩ ነው፣ ምክንያቱም ሕጉ ውስብስብ ነው ብቻህን የምትጋፈጠው ነገር አይደለም።እና እዚህ ሃገር እስከኖሩ ድረስ እዚህ ዓይነት መዋቅር ውስጥ ራሳቸውን ቢከቱ በጣም የሚረዱ ሰዎች አሉ።''



እንደ ማኅበረሰብ ደግሞ፣አሜሪካዊ ዜግነት ያላቸውና በቤተክርስትያናት እና በመንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ያሉ፣ ሠነድ የሌላቸውና ጉዳያቸውን በሕግ ሂደት ያሉትን ወገኖች የመርዳት ግዴታ እንዳለባቸው ማሰብ አለባቸው ብለዋል።



እንዲሁም ሰርቶና ተምሮ ለመለወጥ ሰፊ እድል የምትፈጥረው አሜሪካ፣ ጥሩ ባህሏ እንዲቀጥል ማድረግ እንደሚያስፈልግ የተናገሩት የሕግ ባለሙያው፣ሰሞኑን በአፍጋኒስታናውያንና ሶማሌያውያን ስደተኞች ላይ ከደረሰው ልምድ በመማር በየትኛውም የወንጀልና የማጭበርበር ድርጊቶች ላይ ባለመግባት፣ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።



ታሪኩ ኃይሉ



ኂሩት መለሰ



ፀሐይ ጫኔ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የአሜሪካን የኢሚግሬሽን ባለሥልጣናት ሚኒሶታ የሚኖሩ ሶማሊያውያንን ማሰር መጀመራቸው ስጋት አሳድሯል

የአሜሪካን የኢሚግሬሽን ባለሥልጣናት ሚኒሶታ የሚኖሩ ሶማሊያውያንን ማሰር መጀመራቸው ስጋት አሳድሯል

ታሪኩ ኃይሉ