DiscoverDW | Amharic - Newsበቀለ መኮንን በሥነ ጥበቡ ዘርፍ ለኢትዮጵያ የመጀመርያ የሆነዉን የፕሮፌሰር ማዕረግን ተቀበሉ
በቀለ መኮንን በሥነ ጥበቡ ዘርፍ ለኢትዮጵያ የመጀመርያ የሆነዉን የፕሮፌሰር ማዕረግን ተቀበሉ

በቀለ መኮንን በሥነ ጥበቡ ዘርፍ ለኢትዮጵያ የመጀመርያ የሆነዉን የፕሮፌሰር ማዕረግን ተቀበሉ

Update: 2025-12-04
Share

Description

በቀለ መኮንን በሥነ ጥበቡ ዘርፍ ለኢትዮጵያ የመጀመርያ የሆነዉን የፕሮፌሰር ማዕረግን ተቀበሉ



«አንዳንድ ጊዜ ማዕረግም ፣ ሹመትም ፣ ሽልማትም በተለያዩ ምክንያት እና አጋጣሚዎች ያልተገባ ሰው እጅ ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ። ይህ ይበልጡን በሀገራችን፣ በዓለምም ላይ ታይቷል። ለፕሮፌሰር በቀለ መኮንን አይነቱ ደግሞ እንዲህ ግጥም ያለ፣ በልኩ የተሰፋ ሆንዋል።



የበቄ ፕሮፌሰርነት በሥነ-ጥበብ ዘርፍ የተሰጠ የመጀመሪያው ቢሆንም፣ የሰውየው የበቀለ ብቻ አይደለም። የመጪው ትውልድ ሁሉ ነው። የሥነ-ጥበብነት ብቻ ሳይሆን የመቻል ፕሮፌሰርነት ነው። ከእንግዲህ ለአንድ ሥነ-ጥበበኛ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መሰጠት እንደሚችል ማሳያው፣ ማመላከቻው፣ ዳገቱ ፣ ምልክቱ ነው፤ በቀለ መኮንን። ያሉትና የመጪዎቹ የሥነ-ጥበብ ልሂቃን ተስፋና ብርታትም ነው። እንደሚቻል ማሳያውም ፣ ማረጋገጫውም ሆኗል። ይህ ለሥነ-ጥበቡ ብቻም ሳይሆን ለሙዚቃውም ፣ ለትያትሩም ነው። ለመሆኑ ግን በሙዚቃ ወይም በትያትርስ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ተሰጥቶ ያውቅ ይሆን? ካላወቀም ይኸው የመቻል ምልክቱ፤ የቢሾፍቱው በቀለ መኮንን አለላችሁ፤ በቄ እንኳን የመጀመሪያው ሆንክ። ምልክት ነህ። "አቤቤ ሱቅ ጋ" እንደሚባል ከእንግዲህ "በቀለ መኮንን ጋ" ትባላለህ።» ሲሉ በአዲስ አድማስ ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ አስተያየታቸዉን ያጋሩት፤ ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ ናቸዉ።



በሥነ-ጥበብ ዘርፍ የመጀመሪያው ፕሮፌሰር



የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለታዋቂው የሥነ-ጥበብ ባለሙያ ሰዓሊና ቀራጺ በቀለ መኮንን በሥነ-ጥበቡ ዘርፍ፤ የሙሉ ፕሮፌሰር ማዕረግን ሰጥቷል። ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን ከኢትዮጵያ ባሻገር በሌሎች አፍሪቃ ሃገራት እና በዓለማቀፍ መድረኮች አገራቸዉን ያስጠሩ፤ እዉቅናን ያገኙ የመጀመሪያው ባለ ሙሉ ፕሮፌሰር ናቸዉ። ዶቼ ቬለ ከቀናቶች በፊት ሙሉ ፕሮፌሰር ማዕረግን የተቀበሉትን ጥበባኛዉን በቀለ መኮንን እንኳን ደስ ያሉት ሲል በስልክ አግኝቷቸዋል።



«አስተማሪዎቻችን ማግኘት ሲገባቸዉ እኛ ጋር መጥቷል። ይህ የጊዜ ሁኔታ ነዉ። ለነገሩ ለሁሉም በርከፋች ነዉ። ሁሉ ነገር በጊዜዉ ነዉ» ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን እንደነገሩን እሳቸዉን ጨምሮ 16 ኢትዮጵያዉያን 75 ኛ ዓመቱን እያከበረ ባለዉ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግን በደብዳቤ ኅዳር 17 ቀን 2018 ዓ.ም ተቀብለዋል። ከትናንት በስትያ ማክሰኞ ኅዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ደግሞ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በተካሄደዉ ይፋዊ የማዕረግ አሰጣጥ ሥነ-ስርዓት ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት የተለያዩ ከፍተኛ አመራሮች እና የክፍል ኃላፊዎች፣ ምሁራን፣ እና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ብሎም ተማሪዎች ተገኝተዋል። በሥነ ጽሑፉም፤ በሥነ ሥዕሉም በሥነ ቅርፁም ሞያቸዉን ከአገር ባሻገር በአለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያን ያስጠሩት ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን፤ ከተሰጦ ሞያቸዉ የቱን ያስቀድሙ ይሆን ሥነ -ስዕሉን ሥነ -ቅርሱን ወይስ ሥነ-ግጥሙን ስንል ጠይቀናቸዋል?



«ሁሉም ሲሰራ በጭንቅ ነዉ የሚታለፈዉ ግጥምም፤ ስዕልም ስነ ቅርሱም ስራዉ ተሰርቶ እስኪaleቅ፤ ማለትም እስኪወለድ ድረስ ነፍስን ስግስ አድርጎ ይይዛል። አንዳንዴም መልሶ መልሶ ከመጀመርያዉ ለመስራት ያስገድዳል እና ሁሉም ያዉ ነዉ። ሲወለድ እና ሲሳካ ደስ ይላል።»



ቤተኛ በጎተ ተቋም እና በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ሥነጥበባት ማዕከል



የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴሥነ-ጥበባት ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ጌትነት፤ በቀለ መኮንንን የሚያዉቋቸዉ ለረጅም ዓመታት ነዉ። በተለይ በጀርመን ባህል ማዕከል በጎተ ተቋም እና በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ሥነጥበባት ማዕከል ግጥሞቻቸዉን ባቀረቡበት መድረክ ሁሉ አቶ ይታገሱ ጌትነት ተገኝተዋል። የአለ የሥነ-ጥበብና ዲዛይን ት/ቤት የመጀመርያው ሙሉ ፕሮፌሰር ፤ የፕሮፌሰር በቀለ መኮንን ሥራዎች እንደዉ ሊዘረዝሩልኝ ይችላሉ?



« ጥበባዊ ስራዎቹ በጣም ብዙ ናቸዉ። ይሔን ይሔን ብሎ መጥራቱ ከባድ ሊሆን ይችላል። ስራዎቹ በአፍሪቃ ህብረት ቅፅር ግቢ የሚገኘዉ የአፄ ኃይለሥላሴ ስነ ቅርስ፤ አብርሆት ቤተ መጽሐፍት መግብያ ላይ የሚገኘዉ ቅርስ፤ ስዕል ጤፎ የተባለዉ ኤግዚቢሽን፤ በጣልያን ሃገር የቅኝ ግዛትን ምንነት ያሳየበት . . . . ሲሉ በሰፊዉ ዘርዝረዋል።



ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም በማኅበራዊ መገናኛ ገጣቸዉ እንዳሰፈሩት ፤ ደግሜ እላለሁ ይላሉ «ደግሜ እላለሁ ሁለ ገቡ በቀለ መኮንን በስራው መኾንን የኾነ፤ ስለኾነ መባሉ አይገርምም። ይልቁንም ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን ብለን ስንጠራ ክብሩ ለራስ ነው። "የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለሰዓሊና ቀራጺ በቀለ መኮንን በሥነ ጥበብ ዘርፍ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ።" በሚለው ዜና ውስጥ ሰባ አምስት ዓመታት ለኖረ ዩኒቨርሲቲ አንድ የጥበብ ሰውና ሙሉ ፕሮፌሰር እንደራበው እንዳይኖር በቀለ መኮንን የተባለ ሁሉን አቀፍ ለዚህ አንጋፋ ተቋም የዘመን ጉዞው አንድ ክብርና መጠሪያ በመሆኑ እኮራለሁ። ደስ ብሎናል።» ሲሉ አስተያየታቸዉን አስቀምጠዋል። የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ ሥነ-ጥበባት ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ጌትነት፤ እንደሚሉት ደግሞ አንጋፋዉ ጥበበኛ ይህ ማዕረጉ ከዚህ ቀደም ብሎ በሁሉም ልብ የተሰጠ ነበር።



የዛሬዉ ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን የሥነ ጥበብ አስተማርያቸዉ እንደነበር የነገሩን ፤ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የአለ የሥነ-ጥበብ እና ዲዛይን ት/ቤ ዳይሬክተር ሠዓሊ አገኘሁ አዳነ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ገጻቸዉ ላይ ባስቀመጡት አስተያየት ።«የቤት ሰው፣ መምህር፣ ባልደረባ፣ የሞያ አባት … ከፍ ሲል፣ ሲከብር፣ ድካሙ ፍሬ ሲያፈራ ወዘተ. ልብ ይሞላል። ጎሽ ደግ አረክ ልጃችን፣ ወንድማችን፣ የሞያ አባታችን ይባላል። እንኳን ደስ ያለህ/አለን።»



ዓለማቀፍ መድረኮችን የተጋራ ጥበበኛ



በቀለ መኮንን ንጉሡ ባለግዙፍ ሰብዕና፣ ከሰው ፊት የሚያቀረ‍ቡት፣ የሚያኮራ፣ ጥንቅቅ ያለ ሙያተኛ፣ በጥረቱ ከጉልበተኞች ቅሚያና ንጥቂያ፣ ከሰሜነኛው ንፍቀ ክበብ (global north) በር ጠባቂነት በጥበብ ሾልኮ በርካታ ዓለማቀፍ መድረኮችን የተጋራ፣ ረብ ያለው ተግባር እየፈጸመ ያለ ሰው የሚሠራበት ተቋም #አዲስ_አበባ_ዮኒቨርስቲ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቶታል። የአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ት/ቤት የመጀመርያው ሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መሆኑ ነው። በቄ በድጋሚ እንኳን ደስ ያለህ። ይህ ድል ለጥበብ ዘርፉ አርዓያነት ያለው ተግባር በመሆኑ ዩኒቨርስቲያችንም ምስጋና ይገባዋል።» ሲሉ አስቀምጠዋል። በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የአለ የሥነ-ጥበብ እና ዲዛይን ት/ቤ ዳይሬክተር ሠዓሊ አገኘሁ አዳነ፤ ጥበበኛዉ በቀለ መኮንን የፕሮፌሰርነት ማዕረግ መሰጠት፤ አሁን ዘመኑ ለሥነ ጥበብ ያለዉን ንቃት ያሳየ፤ ለሥነ-ጥበብ ያለዉን ዉዴታ ያስመሰከረ ብለዉዉታል።



ሠዓሊ አገኘሁ አዳነ በሚመሩት የአለ የሥነ-ጥበብና ዲዛይን ት/ቤት የመጀመርያው ሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተቀበሉት ፕሮፌሰር በቀለ መኮንንን በሠዓሊነት በቀራፂነት ወይስ በገጣሚነት ነዉ የሚያዉቋቸዉ? «በሁሉም ነዉ የማዉቀዉ፤ በቀለ መኮንን በሩስያ የከፍተና ትምህርቱን አጠናቆ እንደተመለሰ የታሪክ ተመራማሪዉ ስዩም ወልዴ በማረፋቸዉ ምክንያት፤ እሳቸዉን ተክቶ አስተማሪ ሆኖ ከገባ በኋላ ነበር። በቀለ መኮንን አስተማሪየ ነበር፤ አሁን ደግሞ ባልደረባዬ ፤ ጓደኛዬ ፤ ከጓደኛም በላይ ነዉ።»



ኢትዮጵያዉስጥ ለሥነ-ጥበብ ለሥነ ቅርፅ ያለን ግንዛቤ እንደ አዉሮጳዉያን የጠለቀ አይደለም የሚል አስተያየቶች ይሰማሉ። ለዚህም በስዕሉ በቀራጺነት ሞያ ላይ ያሉ ሰዎች ስራቸዉ እንብዛም ትኩረት አይሰጡም ይባላል በዚህ ይስማማሉ? ስንል ሁሉ ገቡን የጥበብ ሰዉ ፕሮፊሰር በቀለ መኮንን ጠይቀናቸዋል።



ባለፈዉ ማክሰኞ በሥነ-ጥበቡ ዘርፍ፤ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሙሉ ፕሮፌሰር ማዕረግን በይፋ የተቀበሉት ኅዳር 23 ቀን 2028 ነዉ። የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በደብዳቤ ያሳወቃቸዉ ደግሞ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ኅዳር 17 ቀን ነዉ። የሥነ-ጥበብ ባለሙያ ሰዓሊና ቀራጺ በቀለ መኮንንን እንኳን ደስ ያሎት እያልን ለሰጡን ቃለ ምልልስ በዶቼ ቬለ ስም በማመስገን ሙሉ ዝግጅቱን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።



አዜብ ታደሰ



ፀሐይ ጫኔ

Comments 
loading
In Channel
loading
00:00
00:00
1.0x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

በቀለ መኮንን በሥነ ጥበቡ ዘርፍ ለኢትዮጵያ የመጀመርያ የሆነዉን የፕሮፌሰር ማዕረግን ተቀበሉ

በቀለ መኮንን በሥነ ጥበቡ ዘርፍ ለኢትዮጵያ የመጀመርያ የሆነዉን የፕሮፌሰር ማዕረግን ተቀበሉ