DiscoverDW | Amharic - Newsበጸጥታ ስጋት ውስጥ በቆየው የጋምቤላ ክልል እና የሰላም ጥረት
በጸጥታ ስጋት ውስጥ በቆየው የጋምቤላ ክልል እና የሰላም ጥረት

በጸጥታ ስጋት ውስጥ በቆየው የጋምቤላ ክልል እና የሰላም ጥረት

Update: 2025-12-22
Share

Description

‹‹በጋምቤላ ክልል የሚከሰቱ ግጭቶች በክልሉ ያለውን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ለማሻሻል የሚደረጉ ጥረቶችና እርምጃዎችን እየተፈታተነ ነው፡፡ ›› ኢሰመኮ፡፡



በክልሉ ያለው ግጭትን ለመፍታትም ከወንጅል መከላከል በተጨማሪ የማህበረሰብ ውይይቶችን በማካሄድ ሰላም እና ዕርቅ ማውረድ እንደሚያስፈልግ ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ አመልክተዋል፡፡ የኢትየጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በጋምቤላ ክልል እየተስተዋለ ያለውን የጸጥታ ሁኔታ ላይ ባወጣው መግለጫ በተከሰተው ግጭት የሰው ህይወት ማለፉን ገልጸዋል፡፡ በክልሉ በተለያዩ ጊዜያት የሚከሰቱ ግጭቶች በዘላቂነት ለማስቆምና ወደፊት ተመሳሳይ ሰብአዊ መብቶች ጥሰት እንዳይከሰቱ ለመካከል የክልሉና ፌደራል መንግስት ተገቢውን እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ ኮሚሽኑ አብራርተዋል፡፡



የኢሰመኮ መግለጫ



በጋምቤላ ክልል ህዳር 28/2018 ታጣቂዎች በተሸከርካሪ ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን እና ሌሎች ሰላማዊ ሰዎች ላይ ደርሰዋል በተባሉ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን ተከትሎ ግጭት መስፋፋቱ ተዘግበዋል፡፡ የኢትየጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው በክልሉ ኢታንግ ልዩ ወረዳ፣አቦል ወረዳ እና ጋምቤላ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች የተከሰቱ ግጭቶችን እየተከታል እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡



በኢትየጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሰብአዊ መብቶች ክትትልና ምርመራ ሥራ ክፍል ከፍተኛ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ በዳሳ ለሜሳ በተከሰተው ግጭት የሰው ህይወት ላይ ጉዳት መድረሱን እንዲሁም የተለያዩ ተቋማት በአገልግሎት እንዲያቆሙ ምክንያት መሆኑን አመልክተዋል፡፡ በሰው ንብረት ላይ ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪም የትራንስፖርት አገልግሎትም ላይም ተጽህኖ ማሳደሩን አክለዋል፡፡



በጸጥታ ስጋት ውስጥ በቆየው በጋምቤላ ከተማ የሰዎች እንቅስቃሴ ጀምረዋል



በጋምቤላ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አንድ የሀገር ሽማግሌ በሰጡን አስተያየት በቅርቡ በክልሉ ዋና ከተማ የተከሰተው ግጭት አቦል በተባለ ወረዳ በተደጋጋሚ በተሽከርካሪ እና በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ እንደሆነ አስታውቋል፡፡ በከተማው የተከሰተው ግጭትም ቁጥራቸውን በውል ባልጠቀሱ ሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሱን አብራርተዋል፡፡ ጥቃት ያደርሳሉ ያሏቸው ታጣቂዎችም ከባድ መሳሪያ የታጣቁ መሆናቸውን፣ አቦልና ኢንታግ በተባለ ልዩ ወረዳ መኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል፡፡



የፌደራል ጸጥታ ሐይሎች ወደ ስፍራው መግባታቸውን ተከትሎ ግጭቱ መብረዱን ጠቁመው በጋምቤላ ከተማ የሰዎች እንቅስቃሴ መጀመሩን፣ወደ አቦልና ላሬ የሚወሰዱ መጓጓዣ አገልግሎት አለመጀመሩን አክለዋል፡፡



በጋምቤላ ከተማ የሰዎችና የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ መጀመሩን የነገሩን ሌላው ስሜ አይጠቀስ ያሉ የከተማው ነዋሪም ከህዳር ወር መጨረሻ አንስቶ በተከሰቱ ጸጥታ ችግሮችበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉን አመልክተዋል፡፡ በከተማው በፌደራል ጸጥታ ሐይሎች፣ የሐገር ሽማግሌዎችና ሌሎች ነዋሪዎች ጋር ውይይት ከተደረገው ወዲህ የሰዎች እንቅስቃሴ መጀመሩን ነዋሪው ተናግረዋል፡፡ በዛሬው እለትም በከተማው ውስጥ ሱቆች እና የተለያዩ ተቋማት አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን አመልክተዋል፡፡



በክልሉ በቅርቡ የተከሰተውን የሰላም እጦት ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ እንዲሰጡን በስልክ የጠየቅናቸው የጋምቤላ ክልል ሰላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ማበር ኮር ‹‹የክልሉ ሰላም አሁን ተረጋግተዋል›› በማለት ስልካቸውን ዘግተዋል፡፡ የኢትየጵ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በመግለጫው እንዳመለከተው ‹‹በግጭቶችና ጥቃቶች ላይ ተሳታፊ የሆኑ ቡድኖች እና ግለሰቦች ላይ ተገቢውን የወንጀል ምርመራ በማድረግ ተጠያቂነት የማረጋገጥ ጥረቶችን የበለጠ አጠናክሮ መቀጠል›› እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡



ነጋሳ ደሳለኝ



አዜብ ታደሰ



ኂሩት መለሰ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

በጸጥታ ስጋት ውስጥ በቆየው የጋምቤላ ክልል እና የሰላም ጥረት

በጸጥታ ስጋት ውስጥ በቆየው የጋምቤላ ክልል እና የሰላም ጥረት

ነጋሣ ደሳለኝ