የታኅሳስ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. የስፖርት ዝግጅት
Description
የ10ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ትላንት በሁለት ከተሞች ተካሂዷል
አዳማ ላይ የሲዳማ ቡና እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የተካሄድ ሲሆን በጨዋታውም ሁለቱም ቡድኖች 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ንጥብ ተጋርተው ወጥተዋል ፡፡በአዲስ አበባ ስታዲየም ቀን 7 ሰአት ላይ ጨዋታቸውን ያደረጉት ድሬዳዋ ከተማና አዳማ ከተማ 1 ለ 1 ሲለያዩ በ10 ሰአት የመቻል እና ኢትዮኤሌክትሪክ ጨዋታ ያለምንም ግብ 0ለ0 ተጠናቋል
በመሆኑም 10ኛውን ዙር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና በ 21 ነጥብ ሲመራውፋሲል ከነማ በ 20 ነጥብ ሁለተኛሆኖ ይከተላል መቻል ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና አዳማ ከነማ ሁሉም በ 17 ነጥብ በግብ ክፍያ ተለያይተው ከ 3 እስከ 6 ያለውን ደረጃ ይዘዋል
15ኛው የምስራቅ አፍሪካ ካራቴ ሻምፒዮና
የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ሲካሄድ የቆየው 15ኛው የምስራቅ አፍሪካ ካራቴ ሻምፒዮና 12 የወርቅ ሚዳልያ በማግኘት በኢትዮጵያ የበላይነት ተጠናቆዋል።
ሶማሊያ፣ ኬንያ፣ ማዳጋስከር እና ሱዳን በተሳተፉበት እና በአዲስ አበባ ሲካሄድ በሰነበተው በዞኢህ የምስራቅ አፍሪካየካራቴ ሻንፒዮና በሁለቱም ምድብ ከተግኘው 12 የወርቅ ሜዳልያ በተጨማሪ በሲኒየር ውድድሮች 9 የብር እና 3 የነሀስ ሜዳሊያ ተገኝቶዋል ።
አትሌቲክስ
ትላንት እሁድ በጀርመን በተካሄደው የበርሊን ማራቶን ውድድር ኬንያውያን አትሌቶች ሳባስቲያን ሳዌ እና ሮዝሜሪዋንጂሩ የላቀ ድሎችን አስመዝግበዋል።ኬንያዊው አትሌት ሴባስቲያን ሳዌ የበርሊኑን ማራቶን ለምጨትርስ የውሰደበት ግዜ 2፣02፣16 ሲሆን ኢትዮጵያዊውአትሌት ጨምደሳ ደብላ ባ ጃፓናዊው አትሌት ተቀድሞ 2፡06፡57 በመግባት ሶስተኛ ሆኖ ውድደሩን ጨርሶዋል
ሮዝመሪ ዋንጂሩ በውድድሩ የመጀመሪያ አጋማሽ ብኢትዮጵያውያን ሯጮች ታጅቦ የቆየች ቤሆነም 15 ኪሎ ሜትርሲቀረው ከተፎካካሪዎቿ ጥላ በመውጣት ወድድሩን 2፣21፣05 ሰከንድ በመግባት አሽንፋለች ሁለተኛ የውጣችውኢትዮጵያዊዋ አትሌት ደራ ዲዳ 2፡21፡08 ስትሆን አልማዝ ገብሩ 2፣21.29 በመግባት ሶስተኛ ሆናልች ሆናለች ።
የአፍሪካ ዋንጫ
በ2025 እንደጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር የሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ትላንት በሞሮኮ ራባት ከተማ አተናጋጅዋ ሞሮኮ ከኮሞሮስ ጋር ባደረገችው ጨዋታ ተጀመሮዋል ትላንት በምድብ ሀ የተደለደልችው አስተናጋጀዋ ሀገር ሞሮኮ ራባት ከተማ የመክፍቻ ጨዋታውን አድርርጋለች ብጨዋታውም ሞሮኮ ካሜሮስን 2 ለ0 አሽንፋልች .
ዛሪ ማምሻውን ሶስት ጭዋታዎች የሚካሄዱ ሲሆን ከምድብ ሀ ማሊ ከ ዛምቢያ
ከመደብ ለ ደቡብ አፍሪካ ከ አንጎላ፣
ከመደብ መ ግብፅ ከ ዙንባቡዪ ይጫወታሉ
35ኛው የ አፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ 24ት የአፍሪካ ሀገራት ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድኖች በስድስት ምድብ ተካፍለውየሚፋለሙበት ሲሆን።24ቱ ቡድኖች እያንዳንዳቸው በአራት ቡድኖች በስድስት ምድብ ተከፍለዋል። ከምድብ ጨዋታ በኋላ ከየምድቡ አንደኛ ና ሁለተኛ ሆነው ያጠናቀቁት ሁለቱ ቡድኖች እና ከአራቱ ምርጥ ሶስተኛ ሆነው የጨረሱ ቡድኖች ጋር በመሆን ወደ ቀጣዪ ዙር የሚያልፉ ይሆናል ።
35ኛው የፍሪካ ዋንጫ ምድብ ድልድል
ምድብ ሀ: ሞሮኮ፣ ማሊ ፣ዛምቢያ ኮሞሮስ
ምድብ ለ፡ ግብፅ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ አንጎላ፣ ዚምባብዌ
ምድብ ሐ፡ ናይጄሪያ፣ቱኒዚያ፣ ኡጋንዳ፣ታንዛኒያ
ምድብ ሴኔጋል፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ ቤኒን፣ ቦትስዋና
ምድብ ሠ፡ አልጄሪያ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ሱዳን
ምድብ ረ: አይቮሪ ኮስት ፣ ካሜሩን ፣ጋቦን ፣ሞዛምቢክ
የእንግሌዝ ፕሪምየር ሊግ
በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አርሰናል የሊጉን መሪነት እንደያዘ ፣ዎልቭስ፣በርንሌ እና ዊስትሀም ደግሞ የሊጉንየመጨረሻወን የደርጃ ይዘው ይስንብታሉ .
በ17ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የቅዳሚ እለት ጨዋታ ኒውካስል እና ቸልሲ 2ለ2 ተለያይተው ነጥብ ተጋረተውወጥተዋል . በኢትሀድ ስታድየም የተስተናገደው የማንችስተር ሲቲ እና የዊስት ሀም ዪናይትድን ጨዋታ በሲቲ 3ለ0 አሸናፊነት በ17 ኛው ሳምንት የእንግሌዝ ፕሪምየር ሊግ ሁለት ቀይ ካርድ የተስተናገደበት ብቸኛ ጨዋታ በቶትንሀምሆትስፐር ስታድየም የተስተናገደው እና 61.ሺህ በይ ተመልካች በስታድየም ተግኝቶ የታደሙበት ሊቨርፑል ቶትንሀምን 2 ለ 1 የረታበት ጨዋታ ነበር ትላንት እሁድ አስቶን ቪላ ከማንቼስተር ዩናይትድ ጋር ባደረገው ጨዋታ 2 ለ 1 በሆነ ውጤትአሸንፎዋል ። በ መሆኑም በእንግሌዝ ፕሪምየር ሊግ የ 17ኛ ሳምንት ጨዋት አረሰናል በ 39 ነጥብ ሲመራ ማንችስተርሲቲ በ ሁለት ነጥብ ዝቅ ብሎ በ 37 ነጥብ ሁለትኛ አስቶን ቪላ በ 36 ነጥብ ሶስተኛ ቸልሲ እና ሊቨርፑል በኩል በ 29 ነጥብ በግብ ክፍያ ተብላልጠው አራተኛ እና አምስተኛ ደርጃላይ ይገኛሉ።
የጀርመን ቡንዲስ ሊጋ
15ኛ ሳምንቱን በያዘው በጀርመን ቡንዲስ ሊጋ ጨዋታ ባየር ሙኑሽ ይዲንሀምን 4 ለ 0 በሆን ሰፊ ውጤት በማሸነፍየቡንዲስ ሊጋውን ሰንጠረዥ በ 9 ነጥብ የበላይነት ይዝዋል ማይንትስ ከ ሴት ፓውሊ፣ አጉስ በርግ ከ ብሪማን ፣ስቱትጋርት ከ ሆፍንሀም ሁሉም በተመሳሳይ 0ለ0 ሲለያዪ ሀንቡርግ ከ ፍራክፈርት 1ለ1 በሆነ ውጤት ነጥብ ተጋርቶወጥተዋል.የጀርመን ቡንዲስሊጋን የደረጃ ሰንጠርዥ ባየር ሌቨርኩሰን እና ሊፕ ዚንግ በኩል 29 ነጥብ በግብ ክፍያተበላልጠው ሶስተኛ እና አራተኛ ደረጃን ይዘዋል.የጀርመን ቡንዲስ ሊጋ ቀጣይ ጨዋታ ከ ፈርንጆቹ ክረምት እረፍትበሁዋላ ጃንዋሪ 9 ቀን 2026 ፍንክፈርት ዶርቱመንድን በሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጀምራል.
ሀና ደምሴ
ኂሩት መለሰ






















