DiscoverDW | Amharic - News
DW | Amharic - News
Claim Ownership

DW | Amharic - News

Author:

Subscribed: 53Played: 3,507
Share

Description

News, Analysis and Service from Germany and Europe - in 30 Languages
4773 Episodes
Reverse
የጎርጎሪዮሱ 2025 ዓ.ም ተጠናቅቆ አዲስ ዓመት ከባተ እነሆ ዛሬ አራተኛ ቀኑ ተቆጥሯል ። የዛሬው እንወያይ የጎርጎሪዮሱ 2025 ዐበይት ክስተቶችን ወደ ኋላ መለስ ብሎ ይቃኛል ። በዛሬው እንወያይ መሰናዶ ሦስት ተሳታፊዎች ትንታኔ ሰጥተዋል ።
ለትናንት ቅዳሜ አጥቢያ በአሜሪካ ወታደሮች ተይዘው የተወሰዱት የቬንዙዌላው ፕሬዚደንት ኒኮላስ ማዱሮ የዕጽ ዝውውር የሽብር ወንጀል ክስ ሊመሰረትባቸው ነው። የፕሬዚዳንቱን መያዝ ተከትሎ አሜሪካ በጊዜያዊነት ቬንዙዌላን የማስተዳደር ፍላጎት እንዳላት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በይፋ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የነዳጅ አቅርቦት ላይ በየማደያዎቹ በሚፈጠር ችግር ከፍተኛ መጨናቅ እየታየ ነው፡፡ አሽከርካሪዎች እና የተሸከርካሪ ባለንብረቶች የነዳጅ መሸጫ ማደያዎች ላይ በየጊዜው የሚፈጠረው ማስተጓጎሎች ተጨማሪ የዋጋ ክለሳን በመጠበቅ የሚፈጠር ነው ይላሉ፡፡
ባለፈው ሳምንት አርብ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስተር ቢንጃሚን ናትናያሁ ባለፉት ሶስት አስርት አመታት ከሶማሊያ ተነጥላ እራሷን ነጻ አገር በማወጅ ዕውቅና ስትሻ የቆየችውን፤ ግን በማንም ጥያቄዋ ተቀባይነት አግንቶ የማያውቀውን ሶማሊያ ላንድን እስራኤል ዕውቅና የሰጠችና በነጻ- ሉላዊ አገርነት የተቀበለቻት መሆኑን ማሳወቃቸው ውዝግብ ቀስቅሷል
የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩላቸው ፕረዚደንቱ በአሜሪካ ልዩ ሐይሎች መያዛቸውን አረጋግጠው ለፈጸሙት ወንጀል «በሕግ ይጠየቃሉ »ብለዋል። የቬንዙዌላ መንግስት በበኩሉ ስለሐገሪቱ ፕሬዚደንት መያዝ እስከአሁን ያለው ነገር የለም።
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግሮችን በውይይት መፍታት ለምን አቃተ?
ኢትዮጵያ ውስጥ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ማሽቆልቆሉን ተከትሎ መንግሥት የተለያዩ የትምህርቱ ማሻሻያ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል፡፡ ከነዚህም አንዱ ቅዳሜ ቅዳሜ የሚሰጥ የማጠናከሪያ ትምህርት ነው። የዚህ ትምህርት ጥቅሙ ወይስ ጉዳቱ ያመዝናል?
አቶ አበባው ደሳለው የአብን ተመራጭ የፓርላማ አባል የፍትሕ ሚኒስትሯን ሐና አርዓያ ሥላሴን "ከፖለቲካ ጫና ወጥታችሁ እውነተኛ ፍትሕ የምታሰፍኑት መቼ ነው" ብለው ጠይቀዋል። ሚኒስትሯ "አንድ ሰው የፖለቲካ ግቡን ለማሳካት በሕገ ወጥ መንገድ የሚንቀሳቀስ ከሆነ ፖለቲከኛም ሆነ፣ የመንግሥት ኃላፊ የሕግ ተጠያቂነትን እናረጋግጣለን። ሲሉ መልሰዋል
ከሦስት ዐሥርተ ዓመታት በላይ የዘለቀው ጥበቃ አሁን ባልተጠበቀ ሁኔታ ተስፋ የፈነጠቀላት መስሏል። እስራኤል ለሶማሌ ላንድ የሉአላዊ ሀገርነት እውቅና ስትሰጥ የመጀመሪያዋ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሀገር ሆናለች።
ከ5ሺህ በላይ ይሆናሉ የተባሉ ኢትዮጵያውያን ድንገት ወደሀገራቸው እንዲሚመለሱ ተነግሯቸዋል። ኢትዮጵያውንንም ተጠቃሚ ያደርግ የነበረው ቋሚ የመኖሪያና የስራ ፈቃድ የሚያስገኘው የDV መርሃ-ግብር መቋረጡ ተነግሯል። እነዚህ ስደተኞችን የሚያዋክቡ አሰራሮች ወደ አውሮጳ ኅብረት አባል ሀገራትና ብሪታንያም ጭምር የመዛመታቸው አዝማሚያ ያሰጋል።
ከጥቂት ዓመታት በፊት የዓለም የፕረስ ነጻነትን ቀን የማስተናገድ እጋጣሚ ሰምሮላት በነበረው ኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኀን የነጻነት ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ መምጣቱ መነገር ከጀመረ ውሎ አደረ።
ልዑል አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ሠልማን ዩናይትድ ስቴትስን ሲጎበኙ ከ7 ዓመት ወዲሕ የመጀመሪያቸዉ ነዉ።ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በመካከለኛዉ ምሥራቅ «ምትክ የሌላቸዉ» መሪ ላሏቸዉ ልዑል ያደረጉት አቀባበልም ልዩ ነዉ።ልዑሉ ራት ተጋበዙ፣ ዋይት ሐዉስ፣ ቀይ ምንጣፍ ተዘረጋ፣ የክብር ዘቡ ተሰለፈ፣ ማርሹ ተንቆረቆረ----
አነጋጋሪው የጄፌሪ ኤፕስታይን የወሲብ ቅሌት ሰነድ ይፋ እንዲደረግ የአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች እና ሴኔት በአብላጫ ድምፅ ወሰኑ ። የሕግ አውጭዎቹ ባለሥልጣናትን ጨምሮ የታዋቂ ሰዎችን የወሲብ ቅሌት ይዟል የተባለው ሰነድ ይፋ እንዲሆን ድጋፍ ከማግኘቱ በፊት ለዓመታት የዘለቀ ተቋማዊ ክህደት ተፈጽሞበት እንደነበር የጥቃቱ ሰላባዎች ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የመማሪያ መጻሕፍት አታሚ ድርጅት እና የወጣቶች የኢንቨስትመንት ባንክ ጨምሮ በዚህ ዓመት አምስት ኩባንያዎች እንደሚያቋቁም አሳውቋል። ከሁለት የሩሲያ ኩባንያዎች ጋር የመግባቢያ ሥምምነቶች የተፈራረመው ተቋም ከ2011 ጀምሮ የስኳር ፋብሪካዎች ለመሸጥ ሲደረግ የነበረው ጥረት አቋርጧል።
ናማታኒ ክዌክዌዛ በ18 ዓመቷ ነበር WELEAD TRUST የተባለ ወጣት መሪዎችን የሚያሰለጥንና በፖለቲካ ውሳኔዎች ሂደቶች እንዲሳተፉ የሚሠራ ድርጅት የመሠረተችው።በተባባሰው የዚምባብዌ ጨቋኝ ድባብ ክዌክዌዛ ለሕግ የበላይነትn ለፖለቲካዊ ተሳትፎ ትታገላለች፤ታስራለች፤ቁም ስቅልና የማስፈራሪት ሙከራዎች ደርሰውባታል። ስኬት ዋጋ ያስከፍላል ትላለች።
የዝግጅቱ አስተባባሪ የሆኑት የታሪክ መምህርና የማኀበራዊ ጉዳይ ባለሙያ አቶ ተፈራ ኃይሉ፣የሰሞኑበክብረ በዓል፣እንደ ሻምበል ከተማ ጆባ ሁሉ በኮሪያ ዘመቻ ለተሳተፉ ኢትዮጵያውያን አርበኞች ምስጋና ለማቅረብ የተዘጋጀ እንደነበር ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል።
የኮንጎ ዴሞክራቲክ መንግስትና ኤም23 ባለፈው ሀምሌም ከሰላም ምምነት ደርሰው የነበር ቢሆንም ሁለቱም ስምምነቱን ሳያከብሩ ነበር የቆዩት። ያሁኑ ስምምነት በቀጣይ ሊሚደረጉ ድርድሮች መነሻ በመሆን እንድሚያገልግል የታመነ ሲሆን፤ ከበፊቱ ስምምነት የየለየ እንደሆነና ለተግብራዊነቱ የሚሰሩ---
በዓለም ዙሪያ በሚካሔዱ ግጭቶች ምግብ እንደ የጦር መሣሪያ ጥቅም ላይ እየዋለ እንደሚገኝ የተባበሩት መንግሥታት ምክትል ጸሀፊ ተናገሩ። በዓለም 673 ሚሊዮን ገደማ ሰዎች እንደራባቸው ወደ መኝታቸው ይሔዳሉ። ከእነዚህ ውስጥ 307 ሚሊዮን አፍሪካውያን ናቸው። አሚና መሐመድ ዓለም ረሐብን ከማቆም ይልቅ ለወታደራዊ ወጪዎች ትኩረት እንደሰጠ ተችተዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ማርበርግ የተሰኘው ተሐዋሲ መከሰቱን የጤና ሚኒስቴር አረጋግጧል። በዚህ ምክንያትም የሰዎች ሕይወት ተቀጥፏል። ማርበርግ ተሐዋሲ የኤቦላ ተሐዋሲ ቤተሰብ ከሚባሉት አደገኛና ለሞት ከሚያደርሱ ተሐዋሲያን አንዱ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።
ለመሆኑ በቅርብ ዓመታት የዘር ማጥፋት ወይም የጦር ወንጀል የተፈፀመዉ ናይጄሪያ ይሆን? ብቻ ዶናልድ ትራምፕ 8 ጦርነት አስቁሜያለሁ ይላሉ፣ትራምፕ እንደ ጠቅላይ አዛዥ የሚያዘምቱት ጦር ሶማሊያን፣ የመንን፣ ኢራንን፣ የቬኑዙዌላ ጠረፍን ይደበድባል አሁን ደጎሞ ናጄሪያ ላይ እየዛቱ ነዉ
loading
Comments