DiscoverDW | Amharic - Newsለፍልሰተኞችና ልጆቻቸው ሕይወት በጀርመን አርኪ ይሆን?
ለፍልሰተኞችና ልጆቻቸው ሕይወት በጀርመን አርኪ ይሆን?

ለፍልሰተኞችና ልጆቻቸው ሕይወት በጀርመን አርኪ ይሆን?

Update: 2025-11-04
Share

Description



ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የጀርመን ህዝብ ስብጥር ብዙ ለውጥ ይታይበታል። የጀርመን ፌደራል ሪፐብሊክ የህዝብ ጥናት ተቋም እንደሚለው በአሁኑ ጊዜ ከአራት ጀርመናውያን አንዱ የውጭ ዝርያ አለው። ከመካከላቸው 21.2 ሚሊዮኑ፣ ማለትም ሦስት አራተኛው ጀርመን ተሰደው የመጡ ናቸው፤ አንድ አራተኛው ደግሞ እዚህ ነው የተወለዱት። ታዲያ ለእነዚህ የኅብረተሰብ ክፍሎች ሕይወት በጀርመን አርኪ ይሆን?



የዶቼቬለው ኦሊቨር ፒፐር እንደዘገበው በቅርቡ ይፋ የተደረገ የጀርመን ፌደራል መንግሥት የህዝብ ጥናት ተቋም ጥናትና ምርምር ከምሥራቅ አውሮጳ ወደ ጀርመን የተሰደዱ ሰዎች ጀርመን በመኖራቸው ከሌሎች አካባቢዎች ከመጡት ስደተኞች በከፍተኛ ደረጃ ደስተኛ መሆናቸውን አመልክቷል። በጥናቱ የቀደመ የፍልስት ታሪክ የሌላቸው ደግሞ ከምሥራቅ አውሮጳ ከተሰደዱት ቀጥሎ ያለውን መካከለኛውን ደረጃ የያዙ ሲሆኑ ፣ ሁለተኛው ትውልድ ወይም የስደተኞች ልጆች ደስታ ደግሞ አነስተኛ ነው።



በጎርጎሮሳዊው 2025 ዓ.ም. በጀርመን የተካሄደ አንድ የዳሰሳ ጥናት ጥናት ካለፉት ዓመታት በተሻለ የጀርመን ነዋሪዎች በሕይወታቸው ይበልጥ ደስተኛ መሆናቸውን ይፋ አድርጓል። በጥናቱ ከተካተቱት 2 ሰዎቹ አንዱ፣ ሕይወት በጀርመን በጣም እንደሚያረካት ትገልጻለች፤ወይም እንደሚያረካው ይገልጻል። ። በአካባቢ ደረጃ ሲታይ እርካታው ከምዕራብ ጀርመን ይልቅ በምሥራቅ ጀርመን በሚገኙ ፌደራዊ ግዛቶች ጨምሮ ተገኝቷል። የሰሜን ጀርመንዋ የሐምቡርግ ህዝብ ከሁሉም ደስተኛዎቹ ናቸው።



በጀርመን የፍልሰተኞች ልጆች የወላጆቻቸውን ያህል አይደሰቱም



የጀርመን ፌደራል መንግሥት የህዝብ ጥናት ተቋም በምህጻሩ BiB ፣ ጥናትና ምርምር ያካሄደው ጀርመን በሚኖሩ እድሜያቸው ከ20 እስከ 52 በሚደርስ 30 ሺህ ግለሰቦች ላይ ነው። ይኽው ጥናት በተለይ ግለሰብ ፍልሰተኞች፣ ከኅብረተሰቡ ጋር ተዋኅደው መኖር አለመኖራቸውን የተመለከቱ ከዚህ ቀደም የተካሄዱ ሌሎች ጥናቶችንም አካቷል። ከ83 ሚሊዮኑ የጀርመን ህዝብ ከአንድ አራተኛው በላይ የፍልሰተኞች ልጆች ናቸው ፤ ወይም ባለፉት 50 ዓመታት ወደ ጀርመን የተሰደዱ የውጭ ዜጎች ናቸው። የBiB ክትትል ሃላፊ ካታሪና ስፒስ ስለጥናቱ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት በተለይ አንዳንዶቹ የጥናት ውጤቶች የተጠበቁ አልነበሩም፤ለአጥኚዎቹ እንቆቅልሽ ሆነውባቸዋል።



« እንደ እውነቱ ከሆነ፣ በህይወት እርካታ ረገድ የተወሰነ መረጋጋት ላይ ደርሰናል። እና አሁን ከኮሮና ወረርሽኝ በፊት ወደ ነበረው ደረጃ ተመልሰናል ማለት ይቻላል። ሆኖም ተመራማሪዎች ጉዳዩን በፍልሰተኞች ቡድኖች ከፋፍለው ሲያጠኑት ልዩነቶችን ተመልክተዋል። ከምሥራቅ አውሮጳ ከመጡት መካከል በርካታዎቹ ሕይወት በጀርመን በጣም ያረካቸው ናቸው። ሁኔታውን ስንመለከተው የውኅደት ተቃርኖ ተመልክተናል። የፍልሰተኞቹ ልጆች በጀርመን ሕይወታቸውያላቸው እርካታ ከፍልሰተኛ ወላጆቻቸው ያነሰ ያነሰ ነው ። »





«የውኅደት እንቆቅልሽ» የሚለው አገላለጽ የማኅበራዊ ሳይንስ እና የውኅደት ተመራማሪው የአላዲን ኤል ማፋላኒ ነው። ኤል ማፋላኒ በትንታኔያቸውየተሳካ ውኅደት የግጭትን አቅም ይጨምራል ብለዋል። «እኛ የፍልሰተኞች ልጆች ከኅብረተሰቡ ጋር መሳተፍ ብቻ ሳይሆን ለመቀይርም ማገዝ እንፈልጋለን ፤ ይህ ደግሞ ብዙውን ጊዜ ለውጥን ከሚቃወሙ ግትር ሰዎች ጋር ወደመጋጨት ሊያመራ ይችላል። ይህም መዋኅድ የሚፈልገውን ወደ ተስፋ መቁረጥ ይወስዳል።» ብለዋል።



በአጠቃላይ ተመራማሪዎቹ ፣ከምሥራቅ አውሮጳ የመጡ አዳዲስ ፍልሰተኞች ጀርመን በሚመሩት ሕይወት በከፍተኛ ደረጃ ደስተኛ መሆናቸውን ደርሰውበታል። ከዚህ ቀጥሎ ያለውን የእርካታ ደረጃ የያዙት ደግሞ የቀደመ የፍልሰት ታሪክ የሌላቸው ናቸው። የመጀመሪያ ትውልድ የስደተኞች ልጆች ግን በጀርመን ሕይወታቸው ፣ ደስታቸው አነስተኛ ነው። የBib ክትትል ሃላፊ ስፒስ እንዳሉት ጀርመን የተወለዱ የስደተኞች ልጆች፣ እንደሌሎቹ በጀርመን ሕይወታቸው የማይረኩበት ምክንያት አንድም የሚጠብቁትን ተስፋ እንዳደረጉት መጨበጥ ባለመቻላቸው ነው።

« በጥናቱ ውጤት መሐረት «ጀርመን የተወለዱ የስደተኞች ልጆች፣ እንደሌሎቹ ያለመርካታቸው ምክንያት የጠበቁትና የሚሆነው ባለመገናኘቱ ነው፤ ከኅብረተሰቡ ጋር መዋኃዱም እነርሱ እንደግለሰብ ፣ ኅብረተሰቡም ተስፋ እንዳደረጉት አለመስራቱም እንዲሁ»



ምሥራቅ አውሮጳውያን በጀርመን ሕይወታቸው እጅግ ደስተኛ ናቸው



ከምሥራቅ አውሮጳ ፣ ጀርመን ከመጡት አንድ አራተኛ የሚሆኑት በጀርመን ሕይወታቸው እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ይናገራሉ። ጀርመን ከምሥራቅ አውሮጳ ወደ ሀገርዋ ከሚካሄድ ፍልሰት ጋር የተያያዘ ረዥም ታሪክ አላት። ይህም ከፖላንድና ከሌሎች የምሥራቅ አውሮጳ ሀገራት ፣ወደ ጀርመን የመጡ የውጭ ሠራተኞችን፣ እንዲሁም የጀርመን ዝርያ ያላቸው የቀድሞ የሶቭየት ኅብረት ግዛቶች ዜጎችን ያካትታል።



ከእስያ እና ከአፍሪቃ ከመጡ ሦስት ስደተኞች ከአንድ የሚበልጡት ጀርመን ውስጥ በሚመሩት ሕይወት ደስተኛ አይደሉም። ይህም በሌሎቹ ቡድኖች ውስጥ ከተካተቱት ስደተኞች ቁጥር ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛው ነው። ተመራማሪዎቹ ምክንያቱ ያጋጠሟቸው አድልዎ እና ዘረኝነት ሊሆኑ እንደሚችሉ ገምተዋል። በጎርጎሮሳዊው 2015 እና 2016 ማለትም ከ10 እና 9 ዓመት በፊት ጀርመን የመጡት ስደተኞች ላይ የሚንጸባረቀው ስሜት ደግሞ የተቀላቀለ ነው። ከሦስት ሶሪያውያን አንዱ ወይም አንዷ እዚህ ጀርመን በመኖሩ ደስተኛ ፣ ሴትም ከሆነች ጀርመን በመኖርዋ ደስተኛ ናት። ከኢራቅና ከኤርትራ የመጡ ተመሳሳይ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች ግን በጥናቱ መሠረት ፣በሚገኙበት ሁኔታ ደስተኛ አይደሉም። እንደተመራማሪዎቹ ፣ የዚህ ምክንያቱ የሶሪያ ስደተኞች ቤተሰቦች ከሀገራቸው እንዲመጡ ማድረግን ጨምሮ ከሌሎቹ በተለየ ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግላቸው መሆኑ ነው።



የሩስያ-ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዩክሬናውያን ጀርመን ገብተዋል



በአሁኑ ጊዜ በጀርመን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተገን ጠያቂዎች ዩክሬናውያን ናቸው። ቁጥራቸው ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጡ ዩክሬናውያን የሩስያ-ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ጀርመን ገብተዋል።ከነዚህ ውስጥ እድሜያቸው ከ50 በላይ ከሆነው 60 በመቶዎቹ በጀርመንሕይወታቸው ደስተኛ አይደሉም። የዚህ አንዱ ምክንያት በሀገራቸው የሚካሄደው ጦርነት ሲሆን፣ ከዚህ ሌላ እድሜያቸው የገፋ ተገን ጠያቂዎችም ብቸኝነት ስለሚሰማቸው ነው። ይህ ደግሞ ከሌሎች ሀገራት በመጡት ተገን ጠያቂዎች ላይም ያለ ነው።





ሩስያ ዩክሬንን ከወረረችበት ከጎርጎሮሳዊው ከየካቲት 2022 ዓም አንስቶ ጀርመን ያስጠጋቻቸው ዩክሬናውያን ከ2024 ዓም በኋላ በጀርመንሕይወታቸው መደሰታቸው በመጠኑ እየጨመረ የሄደ ቢሆንም ፣ አሁንም ግን ዝቅተኛ ነው። ከመካከላቸው ገሚሱ እዚህ በጀርመን ኑሮአቸው ደስተኛ አለመሆናቸውን እንዲሚናገሩ ጥናቱ ማመልከቱን ስፒስ ተንጋረዋል። «በጀርመን ከለላ ከሚፈልጉት በርካታ ቁጥር ካላቸው ዩክሬናውያን መካከል ፣በጀርመን ቆይታቸው ብዙም የማይረኩ በተለይ በእድሜ የገፉ ሴቶች ይገኛሉ። የዚህ ምክንያቱም የትዳር አጋሮቻቸው አሁንም ዩክሬን መገኘታቸውና በጦርነቱም በንቃት የሚሳተፉ መሆናቸው ነው።»





የጀርመንና ቋንቋ ችሎታ ለውኅደትም ሆነ በጀርመን ደስተኛ ለመሆን ቁልፍ ነው



ተመራማሪዎቹ ለሌሎች ግኝቶችም አጽንኦት ሰጥተዋል። የቋንቋ እውቀት ማነስ በጀርመን ደስተኛ ከማያደርጉ ምክንያቶች ውስጥ ተጠቃሽ ነው። ስፒስ እንዳሉት ፈላስያን የጀርመን ቋንቋ ችሎታቸው ባነሰ ቁጥር ሕይወት በጀርመን አስደሳችነቱ እየቀነሰ መሄዱ አይቀርም። « ስደተኞች ከኅብረተሰቡ ጋር በስራው ገበያ በተሻለ መንገድ ተዋኅደው መኖር ብቻ ሳይሆን የዳበረ የቋንቋ ችሎታም የሚኖራቸው ጀርመን ብቻ አይደለም። ይህም በሀገሪቱ የሚኖሩበት ጊዜ በረዘመ ቁጥር ደስተኝነታቸውም በዚያው መጠን ከመጨመሩ ጋርም ይያያዛል።»



ጀርመንን ትተው የሚሄዱ የውጭ ዜጎች ምክንያት



የዳሰሳ ጥናቱ ጀርመንን ጥለው የሚሄዱ ስደተኞችን ሁኔታም ዳስሷል። ከጀርመን ወደ ስፔይን ጣልያን፣ ፖርቱጋልና ግሪክ ከሚሄዱ ሰዎች ውስጥ ጀርመን በነበራቸው ሕይወት በጣም ደስተኞች የነበሩም ይገኙበታል።ስፒስ ሰዎቹ ከጀርመን ወደ እነዚህ ሀገራት የሚሰደዱት ሳቢ ከሆነው የአየር ንብረታቸው ጋር በተያያዘ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋልል። ያ ማለት ግን እነዚህ ሰዎችም በጀርመን ቆይታቸው ደስተኛ አልነበሩም ማለት ግን አይደለም።

« የውጭ ዜጎች ጀርመንን ትተው የሚሄዱት በጀርመን ደስተኛ ባለመሆናቸው ብቻ አይደለም። ከመካከላቸው ጀርመን ረክተው ይኖሩ የነበሩ በርካቶች ይገኙበታል። ይህም ጀርመንን ጥሎ መሄድ፣ በኑሮ አልረካሁም ከጀርመን እሸሻለሁ ማለት እንዳይደለ ማሳያ ነው። በጀርመን ሕይወታቸው የሚረኩ ነገር ግን አዳዲስ ልምዶችን ለማካበት ጀርመንን ትተው ወደ ሌላ ሀገር መሄድ የሚፈልጉም አሉ። »



ኂሩት መለሰ



እሸቴ በቀለ

Comments 
loading
In Channel
loading
00:00
00:00
1.0x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

ለፍልሰተኞችና ልጆቻቸው ሕይወት በጀርመን አርኪ ይሆን?

ለፍልሰተኞችና ልጆቻቸው ሕይወት በጀርመን አርኪ ይሆን?

ኂሩት መለሰ