DiscoverDW | Amharic - Newsየጀርመን ፕሬዝዳንት ፍራንክ ዋልተር ሽታየይንሜየር የአፍሪቃ ጉብኝት
የጀርመን ፕሬዝዳንት  ፍራንክ ዋልተር ሽታየይንሜየር የአፍሪቃ ጉብኝት

የጀርመን ፕሬዝዳንት ፍራንክ ዋልተር ሽታየይንሜየር የአፍሪቃ ጉብኝት

Update: 2025-11-04
Share

Description

የጀርመን ፕሬዝዳንት ፍራንክ ዋልተር ሽታየይንሜየር ባለፈው ቅዳሜና እሁድ የተጀመረውን የአፍሪቃ ጉብኝታቸውን ቀጥለዋል።የሽታይንሜየር የአፍሪካ ጉብኝት ባለፈው ቅዳሜና እሁድ በግብፅየተጀመረ ሲሆን፤ በካይሮ የታላቁ የግብፅ ሙዚየም ምረቃ ላይ ተገኝተዋል። እድሉን ተጠቅመው ከፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አልሲሲ ጋር ለመገናኘት ችለዋል። የጀርመን ፌዴራል ፕሬዝዳንት ግብፅ በመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ውስጥ አሸማጋይ በመሆን ላላት ወሳኝ ሚና አመስግነዋል።ፕሬዚዳንቱ በርካታ የአረብ ሀገራት ስለ ጋዛየወደፊት ሁኔታ «ስጋት ያጠላበት በራስ መተማመን» እንዳላቸው ገልጸዋል።በጋዛ ጉዳይ ማን እንደሚሳተፍ ግልፅ አይደለምም ይላሉ።«በተለይም ፍልስጤማውያን እስካልቻሉ ድረስ ለሚመጡት ወራት እና ምናልባትም ለዓመታት በጋዛ ሰርጥ ውስጥ የፀጥታ ደህንነትንን ለማስፈን ማን እንደሚሳተፍ አሁንም ግልጽ አይደለም።»ብለዋል።



የጀርመን ድጋፍ ጋዛን መልሶ ለመገንባት



እሑድ ዕለት ወደ ጋና ከመጓዛቸው በፊት ለጋዜጠኞች ባደረጉት ንግግር፣ ሽታይንሜየር ጀርመን የጋዛ ሰርጥን መልሶ ለመገንባት ድጋፍ እንደምታደርግ ጠቁመዋል።ዓለምም ይህንን ይደግፋል ብለው ተስፋ ያደርጋሉ። «እናም ዓለም አሁን ሙሉውን ሂደት፣ የሚቀጥለውን ሂደት መጠበቅ ብቻ ሳይሆን፣ በቀላሉ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ወደ ዘላቂ መረጋጋት ለመቀየር እንደሚረዳ ተስፋ ይደረጋል።» ብለዋል። ትናንት ሰኞ ጠዋት ወደ ጋና ያቀኑት የጀርመኑ ፕሬዝዳንት ለሁለት ቀናት ጉብኝት እያደረጉ ነው። ሽታይንሜየር ትናንት በጋና ሲደርሱ ፕሬዝዳንት ጆን ድራማኒ ማሃማ በወታደራዊ ክብር ተቀብለዋቸዋል። በመዲናዋ አክራ በተደረገው ስብሰባሁለቱ ሀገራት በንግድ ፣ በሳይንስ እና በጤና ዘርፎች የሁለትዮሽ ትብብርን ስለማጠናከር ተወያይተዋል።



ፍልሰት ሽብርተኝነት እና የፀጥታው ምክርቤት ማሻሻያ



በውይይቱፍልሰት፣ በሳህል ክልል ውስጥ ያለውን ሽብርተኝነት እና አለመረጋጋትን ስለመዋጋት እና የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ማሻሻያ ከተነሱ ርዕሰ ጉዳዮች መካከል ናቸው። ፕሬዝዳንት ማሃማ ፤ ጀርመን በፀጥታዉ ምክር ቤት ማሻሻያ ስላላት ድጋፍ አመስግነው፤ ነገር ግን በምክር ቤቱ ውስጥ ለአፍሪካ ህብረት አባላት ሁለት ቋሚ መቀመጫዎችን ስለመመደብ ታላቅ እርምጃ እንዲወሰድ አሳስበዋል።

«ይህ ታሪካዊ ኢፍትሃዊነት መስተካከል አለበት ።ፕሬዚዳንት ሽታየንማየር እና የጀርመን መንግስት ለዚህ መርህ እንዲቆሙ ምኞቴ ነው።ጋና ሁሉም ሀገራት ከንግግር አልፈው እርምጃ እንዲወስዱ፣እና የፀጥታው ምክር ቤት ውክልና፣ የበለጠ ዴሞክራሲያዊ እና ህጋዊ እንዲሆን ጥሪ አቅርባለችል።»ብለዋል።



የኮምፓክት ዊዝ አፍሪቃ አጋር ሀገር



ጋና፤ በአህጉሪቱ መዋዕለ ንዋይን ለማሳደግ በበርሊን የተጀመረው የኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ መርሃግብርቁልፍ አጋር ናት። ከዚህ አንፃር በኢኮኖሚ እድገት እንዲሁም በበርሊን እና በአውሮፓ ህብረት በሚደገፉ የአካባቢው የክትባት ምርቶች ትብብር ላይ መወያየታቸውንም አክራ የሚገኘው የኮንራድ አደናወር ፋውንዴሽን ቢሮ ዳይሬክተር የሆኑት አናሊና ቫሰርፋል ገልፀዋል።ፕሬዝዳንቱ ከጋና ከሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮች እንዲሁም ከጀማሪ ኩባንያ መስራቾች ጋርም መክረዋል።ፍራንክ-ዋልተር ስቴይንሜየር ዛሬ ማክሰኞ በሰሜናዊ ጋና ወደሚገኘው ኩማሲ የተጓዙ ሲሆን፤ ይህም የጀርመኑ ፕሬዝዳንት በታህሳስ 2017 ዓ/ም ካደረጉት ጉብኝት ወዲህ ሁለተኛው ጉዞ ነው።



የፕሬዚዳንቱ የአንጎላ ጉብኝት



የጀርመኑ ፕሬዝዳንት ዋልተር ሽታየን ማየር የመጨረሻ ጉብኝት በአፍሪካ በነዳጅ በበለፀገችው ሀገር ወደ አንጎላ ሲሆን፤ መጭውን ረቡዕ እና ሀሙስ ማለትም በጎርጎሪያኑ ከህዳር 5 እስከ 7 እዚያው ይቆያሉ።በዚህ ጉብኝት ሽታይንሜየር አገሪቱን የጎበኙ የመጀመሪያው የጀርመን ፕሬዝዳንት ይሆናሉ። በጉብኝቱ ከአቻቸው ጆአኦ ሎሬንሶ ጋር በመሠረተ ልማት እና ታዳሽ ኃይል ላይ ያተኩረ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል ።

ፕሬዚዳንቱ ቀደም ሲል በሰጡት መግለጫ አንጎላ የነዳጅና የጋዝ አቅራቢ በመሆኗ ለዓለም ትኩረት የምትሰጥ ብቻ ሳትሆን፣ የራሷን ኢኮኖሚ ማሳደግ እና ተጨማሪ ምሰሶዎችን መደገፍ እንደምትፈልግ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ጀርመንን በጎበኙበት ወቅት ገልፀዋል።ይህም አንጎላ ለጀርመን ጥሩ አጋር ያደርጋታል ብለዋል። ሀገሪቱ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በደቡብ አፍሪካ ውስጥ እውነተኛ የመረጋጋት መልህቅ ሆናለች ያሉት ሽታየንማየር ይህም አንጎላ ለመገኘት ጥሩ ምክንያት ነው ሲሉ ገልፀዋል።



ፕሬዚዳንት ሽታየንማየር በአውሮፓ ህብረት የሚደገፈውን የአትላንቲክ ውቅያኖስን ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ዛምቢያ የማዕድን ቦታዎች ጋር ለማገናኘት የሚሰራውን ፕሮጀክት የሎቢቶ ኮሪደርን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።



ፀሐይ ጫኔ

እሸቴ በቀለ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የጀርመን ፕሬዝዳንት  ፍራንክ ዋልተር ሽታየይንሜየር የአፍሪቃ ጉብኝት

የጀርመን ፕሬዝዳንት ፍራንክ ዋልተር ሽታየይንሜየር የአፍሪቃ ጉብኝት

ፀሀይ ጫኔ