DiscoverDW | Amharic - Newsየአሸንዳ በዓል አከባበር በትግራይ ክልል
የአሸንዳ በዓል አከባበር በትግራይ ክልል

የአሸንዳ በዓል አከባበር በትግራይ ክልል

Update: 2025-08-22
Share

Description

የዘንድሮዉ የአሸንዳ በዓል በትግራይ ክልል ዛሬ መከበር ጀምሯል። ለሶስት ቀናት የሚዘልቀውና በአብዛኛዉ ልጃገረዶች የሚያከብሩት አሸንዳ በተለይ መቀሌ ዉስጥ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ነዋሪዎች እያከበሩት ነዉ።በበአሉ ላይ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች እና ከሌሎች ሀገራት የተጓዙ ሰዎች ታድመዉበታል።ይሁንና የመቀሌዉ ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለሥላሴ ከዚያዉ ከመቀሌ እንደዘገበዉ ዘንድሮዉ በዓል ከዚሕ በፊት ከነበሩት በዓላት ቀዝቀዝ ያለ ነዉ።ዝርዝሩን እነሆ።



በኢትዮጵያ የሰሜኑ ክፍል ነሓሴ ወር አጋማሽበድምቀት ከሚከበሩ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት መካከል የሆነው አሸንዳ፥ ዘንድሮም በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች እየተከበረ ይገኛል። በዋነኝነት ከነሓሴ 16 እስከ 18 የሚከበረው አሸንዳ፥ ዛሬ በትግራይ ዓብይዓዲ የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና የትግራይ ባለስልጣናት በታደሙበት ይፋዊ መክፈቻ ስነስርዓት ተካሂዷል።



በየዓመቱ በመቐለ የአሸንድ በዓል በርካታ እንግዶች ከውጭና ሀገር ውስጥ በታደሙበት በድምቀት ይከበራል። ዘንድሮም በርካታ እንግዶች ቢታደም፥ እንዳለፉት ዓመታት አይደለም የሚሉ አስተያየቶች ይሰጣሉ።



ሚሊዮን ኃይለሥላሴ



ነጋሽ መሐመድ



ልደት አበበ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የአሸንዳ በዓል አከባበር በትግራይ ክልል

የአሸንዳ በዓል አከባበር በትግራይ ክልል

ሚሊዮን ኃይለ-ሥላሴ