DiscoverDW | Amharic - Newsየኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሸሪያ በሚመሩ ባንኮች ላይ የጣለውን ገደብ ማንሳቱ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ  በሸሪያ በሚመሩ ባንኮች ላይ የጣለውን ገደብ ማንሳቱ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሸሪያ በሚመሩ ባንኮች ላይ የጣለውን ገደብ ማንሳቱ

Update: 2025-11-06
Share

Description

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በእስላማዊ ባንኮች ላይ ጥሎ የነበረውን ገደብ ማንሳቱ ባንኮቹን ሊያነቃቃ እንደሚችል የባንክ ባለሞያ ተናገሩ ። ብሔራዊ ባንክ ከሁለት ዓመት በፊት በ14 በመቶ ገደብ ተግባራዊ ያደረገው እና በዚህ ጣሪያውን አሻሽሎ 24 በመቶ ያደረሰው የብድር ጣሪያ ግሽበትን ለመቆጣጠር ያለመ ነበር። የብድር ጣሪያ ገደቡ መነሳት ባንኮቹ ፋይናንሳቸውን ለማሳደግ ሲያግዛቸው ከዓመታት በኋላ የፖሊሲ ድል እንዳገኙ ተነግሮላቸዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለጥቂት ዓመታት ከወለድ ነጻ አገልግሎት ወይም በሸሪያ በሚመሩ ባንኮች ላይ ተጥሎ የነበረው የብድር ጣሪያ ገደብ የተነሳው ባለፈው የሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ነበር። እስላማዊ ባንኮቹ እንደሚሉት እንደሌሎች ከሌሎች መደበኛ ባንኮች ጋር አንድ ላይ ተጥሎባቸው የነበረው ገደቡ ድርብ ጉዳት እንዳደረሰባቸው ነው ሲገልጹ የቆዩት። የባንክ ባለሞያው አቶ ባህሩ ያሲን እንደሚሉት የብሔራዊ ባንኩ ቀደም ሲል ጥሎ የነበረው ገደብ የባንኮቹን ዕድገት ገትቶታል። ዉሳኔው ደንበኞች በባንኮቹ ላይ እምነታቸው እስኪሸረሸር አድርሶ ነበርም ይላሉ ።

«ይኼ የብድር ጣሪያ በተጣለ ጊዜ በ2023 እነዚህ እስላማዊ ባንኮች የሚባሉት ከወለድ ነጻ ነው የሚባሉት፤ በዚያ ወቅት ላይ ሁሉም ሊባል በሚችል መልኩ አዲስ እና ብዙም ብድር ያልሰጡ ነበሩ ። እና ያ የብድር ገደብ ሲጣልባቸው ዕድገታቸውን ቀጥ ነው ያደረገው።»

የባሔራዊ ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቶችን ለመጀመሪያ ጊዜ ካስተዋወቀበት እና የአገሪቱ የመጀመሪያ ሙሉ እስላማዊ ባንኮች ፍቃድ ከሰጠበት ከ2011 ጀምሮ በኢትዮጵያ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በፍጥነት ተስፋፍቷል። የቁጥጥር ማዕቀፉ አሁን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደንበኞችን ለሚያገለግል ዘርፍም መሰረት መጣሉ ይነገራል። ነገር ግን ተንታኞች እንደሚሉት ማዕከላዊ ባንኩ በሌሎች መደበኛ ባንኮች ላይ የሚከተለውን ዓይነት አሠራር በእነዚሁ ከወለድ ነጻ ባንኮች ላይ መተግበሩ ባንኮቹን ገና ከመቋቋማቸው የደንበኛ እምነት እስከመሸርሸር የደረሰ ፈታኝ ሁኔታ እንዲጋፈጡ አድርጓቸዋል ይላሉ ። የባንክ ባለሞያው ባህሩ ያሲንም ይኸው ሃሳብ ይገዛቸዋል።

«ሰው ደንበኛው የነበረውን እስላማዊ ባንክ ላይ የነበረውን ዕይታ የተንሸዋረረ እንዲሆን አድርጎታል። ማለት ያን ያህል ትርፋማ አይደለም፤ ባንኮቹ ቶሎ ማደግ ባለመቻላቸው ምክንያት የደንበኛ ምልከታውም ለስራ የነበረውን እምነቱንም ሸርሽሮታል።»



የብሄራዊ ባንክ የብድር ጣሪያ ገደብ ሲያበጅ በአጠቃላይ ባንኮች ወደ ገበያው በሚያሰራጩት ገንዘብ ግሽበትእንዳይፈጠር የሚል ዓላማ ያነገበ እንደነበር የጠቀሱት ባለሞያው ነገር ግን ሸሪአን አሟልተው የተቋቋሙ ባንኮቹ በሀገሪቱ ካሉ አጠቃላይ ባንኮች የነበራቸው የማበደር አስተዋጽዖ ከአንድ በመቶ ስለማይበልጥ በዚያው ልክ ለግሽበት የሚኖራቸው ሚናም አነስተኛ ነው። አቶ ባህሩም እንደሚሉት ምንም እንኳ ባንኮቹ በገበያ የግሽበት ሁኔታ ውስጥ ምንም ሚና የላቸውም ባይባልም፤ እስካሁን ከነበረባቸው ሚና አንጻር ግን ገደቡ ተጥሎ ሊቆይ ባልተገባው ነበር።

«ዘምዘም፣ ሂጅራ፣ ራሚስ እና ሸበሌ ባንኮች ናቸው ። እነዚህ አራት ባንኮች በጥቅል የሰጡት ብድር ካጠቃላይ ኤኮኖሚው ላይ ካለው አጠቃላይ ብድር አንድ ከመቶም አይሞላም። እለዚህ ለግሽበት ያላቸው አስተዋጽዖ ዜሮ ነው ማለት ነው። »





ይህ በርግጥ ብሄራዊ ባንክ ገደቡን ለማንሳት አንዱ ምክንያት ነው። የብሔራዊ ባንኩ እንደሚለው ግን የገደቡ መነሳት የወለድ አልባ ባንኮቹ ሥራቸውን እንዲያስፋፉ እና እያደገ ለሚሄደው ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት ያስችላቸዋል ። በተጨማሪም ባንኮቹ ፋይናንሳቸውን ወደ አምራች ዘርፎች ለማስገባት እና በብድር ዕድገት ላይ ከነበረባቸው ገደብ ወጥተው በብቃት እንዲወዳደሩ ያስችላቸዋል፤ ይላል። በብሔራዊ ባንኩ ሃሳብ እንደሚስማሙ የተናገሩት የባንክ ባለሞያው ባንኮቹ ከነበሩት አንጻር አሁን የመነቃቃት ጊዜ ሊያመጣላቸው ይችላል።





«ኮንቬንሽናል ባንክ ላይ ያለ ባንክ ያለውን ቢያንስ ሊኩዲቲውን በዚህ መንገድ ሊያስተዳድር ይችላል። የተከማቸ ካፒታል ካለው ለሌላው ባንክ ማበደር የሚችልበት ሁኔታ ይኖራል። የሊኩዲቲ እጥረት ካለበት ደግሞ ከዚያ ባንክ መበደር ይችላል። አሁን እነዚህ እስላማዊ ባንኮቹ የተከማቸ ሊኩዲቲ እያላቸው የመንግስት ግምጃ ቤት ሰነድ መግዛት አይችሉም። ይኼ በመነሳቱ ግን ወደ ማበደር ስለሚሄዱ የተወሰነ ዕድገታቸውን ያነቃቃላቸዋል።»

በኢትዮጵያ የባንክ ኢንደስትሪ መሪዎች የብድር ጣሪያ ደንቡ ፈጠራን የሚያደናቅፍ እና የተዛባ ፉክክር ያስከተለ ነው በማለት ሲሟገቱ ቆይተዋል። ባንኮቹ ካፒታሉ እያላቸው፣ ተቀማጭ ገንዘብ ለማንቀሳቀስ፣ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የገንዘብ ድጋፍ ለመስጠት አልያም በቂ የባንክ አገልግሎት ለሌለው ማኅበረሰብ ለመድረስ ቢፈልጉም በገጠማቸው ተግዳሮት ምክንያት መገታታቸውን ሲገልጹ ቆይተዋል።

ታምራት ዲንሳ

ሸዋዬ ለገሠ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ  በሸሪያ በሚመሩ ባንኮች ላይ የጣለውን ገደብ ማንሳቱ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሸሪያ በሚመሩ ባንኮች ላይ የጣለውን ገደብ ማንሳቱ