DiscoverDW | Amharic - Newsበኢትዮጵያ ደቡባዊ ግዛት ከሰማይ ተቀጣጥሎ የታየው ባዕድ ነገር ምንነት
በኢትዮጵያ ደቡባዊ ግዛት ከሰማይ ተቀጣጥሎ የታየው ባዕድ ነገር ምንነት

በኢትዮጵያ ደቡባዊ ግዛት ከሰማይ ተቀጣጥሎ የታየው ባዕድ ነገር ምንነት

Update: 2025-01-10
Share

Description

ትናንት ማምሻውን በኢትዮጵያ ደቡባዊ አጋማሽ አከባቢዎች ከሰማይ ተቀጣጥሎ ወደ ምድር ሊወድቅ ሲል ታይቷል የተባለውን ባዕድ ነገር በማስመልከት አስተያየታቸውን ለዶቼ ቬለ የሰጡ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት የስነከባቢ አየር ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ገመቹ ፋንታ፤ ኢንስቲትዩታቸው ምስሉን በመውሰድ ሳይንሳዊ ትንታኔ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡ ባለሙያው እንዳሉት እየተቃጠለ ወደ ምድር ስጓዝ የታየው ባዕድ ነገር በሁለት መልኩ የሚገለጽ ነው ይላሉ፡፡ “አንደኛው በሰው ሰራሽ የስፔስ (ከባቢያዊ አየር) ቁሶች ምክንያት የተከሰተ ሊሆን ይችላል” ያሉን ባለሙያው ይህም “በሰዎች የሚመጥቁ ሳተላይቶች የአገልግሎት ጊዜያቸውን ስጨርሱ ተሰባብረው ወደ ከባቢ አየር ልወድቁ ይችላሉ” ሲሉ ቀዳሚውን መላምት አስቀምጠዋል፡፡ ምናልባትም ሳተላይቶችን ለማምጠቅ ጥቅም ላይ የሚውሉ ሮኬቶች ስብርባሪም ሊሆን እንደምችል ጠቁመዋል፡፡



በአፍሪቃ የህዋ ሳይንስ ተቋም ሰለመገንባት የመከረው አውደ ጥናት



እየተቀጣጠሉ ወደ ምድር የሚወድቁት ባዕድ ነገሮቹ ምን ሊሆኑ ይችላሉ በሚል የተቀመጠው ሁለተኛው መላምት ደግሞ በተፈጥሮአዊ የህዋ አካላት ላይ የተከሰተ ሊሆን ይችላል የሚል ነው፡፡ ይህም ተፈጥሮአዊ ክስተት መሆኑ ነው፡፡ “በተፈጥሮአዊ የህዋ አካላት ምክንያት የሚከሰተው በፕላኔት አፈጣጠር እና ከሶላስ ሲስተም አፈጣጠር ጋር ተያያዘ ነው ሊሆን ሚችለው” የሚሉት ዶ/ር ገመቹ “ይህም በፕረላኔት ውስጥ የሚሽከረከሩ አለቶች ስብርባሪ ሊሆን ይችላል” በማለት ገለጻቸውን ቀጥለዋል፡፡ እነዚህ በሰበቃ የሚሰባበሩ አለቶች መሬት ላይ ስደርሱ መጠናቸው እጅጉን እንደሚቀንስም አብራርተዋል፡፡



የተባባሰው የህዋሓት ውዝግብ



እነዚህ ባዕድ ነገሮች ወደ መሬት ስወድቁ “አስትሮይድ” በመባልም ይጠራሉ፡፡ ክብደታቸው ቀለል ያለ ሆነው በአየር ላይ ተቃጥለው በነው ሲያልቁ ደግሞ “ሚቲዮራይት”ይባላሉ፡፡ የሆነ ሆኖም በትናንትናው እለት በኢትዮጵያ ምድር ሰማይ ላይ የታየው ተቀጣጣይ ነገር በሰው ሰራሽ አሊያም በዚህ በተፈጥሮ ክስተት የሚፈጠር ሊሆን እንደምችል ነው በባለሙዎቹ የተገመተው፡፡ ከዚህ በፊት ባለፈው ክረም ጅማ አከባቢ ተመሳሳይ ባዕድ ነገር እንደመብረቅ ሆኖ መውደቁን በማስታወስ ከትናንቱ ክስተት ጋር ምን ያመሳስላቸዋል የተባሉት የስነከባቢ ተመራማሪው፤ “ጅማ የወረደው ወደ ምድር ወድቆ ታይቷልና ያም ቢሆን ትክክለኛ አስተሮይድ ነው ወይ የምድር አለት ነው ብሎ ለመለየት በኢትዮጵያ አዳጋች ነው” በማለት እንደነዚህ አይነት ክስተቶች ከሰውሰራሽ እና ከተጠቀሰው ተፈጥሮአዊ ምክንያቶች እንደማይወጣ ግን አስረድተዋል፡፡



መሰል ክስተቶች በዓለም ዙሪያ በየጊዜው ተደጋግመው የሚስተዋሉና በብዛት ሰዎች በማይኖሩባቸው ባህርና በተለያዩ የምድር አካላት እንደሚወድቁም ባለሙያው ጠቁመዋል፡፡ እነዚህ ባዕድ ነገሮች ወደ ምድር ላይ ደርሰው ስወድቁ መጠናቸው ከጥቃቅን የአሸዋ ስብርባሪ መጠን እስከ 100ሜትር ስፋት ልኖራቸው የሚችል ግዙፍ ሊሆኑም እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡ ባዕድ ነገሮቹ ከተፈጥሮ መዘውራቸው በመውጣት ወደ መሬት ስወድቁ ምን ምክንትስ ይኖር ይሆን ተባሉት የስነህዋ ተመራማሪው፤ “ስነህዋ ምርምር እንደሚያሳየው በጣም ራቅ ያለ ቦታ ላይ የኮከቦች ወይም ጋላክሲዎች መጋጨትና ፍትጊያ ልኖር ይችላል” በማለት ይህ ፍትጊያ ከመስመራቸው በማውጣት መድርን ጨምሮ በተለያዩ ፕላኔቶች ላይ ልወድቁ እንደምችሉ አስረድተዋል፡፡



የህንድ የጠፈር ምርምር ግስጋሴ



ትናንት በደቡባዊ የኢትዮጵያ ክፍል በስፋት በሰማይ ላይ የታየው የሚቀጣጠል ነገር እስካሁን ምድር ላይ ለመውደቁ የተገኘ ማስረጃ አለመኖሩን የገለጹት የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት የስነከባቢ አየር ተመራማሪው ዶ/ር ገመቹ ፋንታ፤ ለዚህ የህብረተሰቡ ጥቆማ እንደሚያሻቸው ገልጸዋል፡፡ ባለሙያው ተቀጣጣይ ነገሩ ሰማይ ላይ ሳይበታተን ወደ ምድር በሚወድቅበት አጋጣሚ ጉዳትም ሊያደርስ እንደሚችል በማስጠንቀቅ ማህበረሰቡ ባዕድ ተቀጣጣይ ነገሩ ሰው ወዳለበት ስፍራ የሚወድቅ ከሆነ መሸሽ እንደሚስፈልግም ጠቁመዋል፡፡



ስዩም ጌቱ



ነጋሽ መሐመድ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

በኢትዮጵያ ደቡባዊ ግዛት ከሰማይ ተቀጣጥሎ የታየው ባዕድ ነገር ምንነት

በኢትዮጵያ ደቡባዊ ግዛት ከሰማይ ተቀጣጥሎ የታየው ባዕድ ነገር ምንነት