የዓለም ዜና

ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና ዜናዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ። የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በአፕል ፖድካስት እና በስፖቲፋይ ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።

የመስከረም 23 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና

• በምዕራብ ሱዳን በከበባ ውስጥ በምትገኘው የኤል ፋሽር ከተማ የፈጥኖ ደራሽ ወይም የአር ኤስ ኤፍ ኃይሎች ባደረሷቸው ጥቃቶች በአስር ቀናት ውስጥ 91 ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ ። • የዓለም የምግብ ድርጅት (WFP) የከፋ ነው የተባለ የገንዘብ እጥረት ማጋጠሙን ተከትሎ በሶማሊያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ለረሃብ መጋለጣቸውን አስታወቀ። • የማዳጋስካሩ ፕሬዚዳንት አንድሪ ራጆኡሊና ስልጣን ለመልቀቅ ዝግጁ አይደለሁም አሉ። • ጋዛ ውስጥ ለሚገኙ ፍልስጥኤማዉያን የርዳታ ቁሳቁስ ይዘው በአጀብ ወደ ጋዛ ይጓዙ ከነበሩ በርካታ ጀልባዎች ውስጥ የመጨረሻዎቹ በእስራኤል ጦር ኃያል መጠለፋቸውን አስተባባሪዎቹ አስታወቁ።

10-03
11:48

የመስከረም 22 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና

በጎዴ የአፈር ማዳበሪያ እና የነዳጅ ማጣሪያ ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ ፤ ሁለት የኬንያ አንቂዎች ዩጋንዳ ውስጥ ታገቱ ፤ ሞሮኮ 3 ሰዎች በፖሊስ ተገደሉ፤ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ: በኢቦላ በሽታ ከ 40 በላይ ሰዎች ሞቱ፤ ማንችስተር አንድ ሙክራብ ላይ በተሰነዘረ ጥቃት ሁለት ሰዎች ተገደሉ፤ የትራምፕ አስተዳደር የበጀት እገዳ

10-02
09:47

የማክሰኞ መስከረም 21 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና

ሸንኮራ፥ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ዛሬ በደረሰ አደጋ ከ30 በላይ ሠዎች ሞቱ፤ ቡታጀራ፥ ሁከትና ብጥብጥ አንስተዋል ሲል ፖሊስ የጠረጠራቸውን 47 ሰዎች በቁጥጥር ማዋሉን ዐሳወቀ፤ ኪንሻሳ፥ የኮንጎ ወታደራዊ ፍርድ በቀድሞ የአገሪቱ ፕሬዚደንት ላይ ቤት የሞት ፍርድ በየነ፤ ሙይንሽን፥ በቦንብ ጥቃት ሥጋት ለሰአታት ተቋርጦ የነበረው ኦክቶበርፌስት እንደገና ተከፈተ፤ ቤርሊን፥የሉፍታንዛ አውሮፕላን አብራሪዎች አድማ ሊጠሩ እንደሚችሉ አስጠነቀቁ

10-01
12:06

የማክሰኞ መስከረም 20 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና

አ.አ፥ የኢትዮጵያ የመዋዕለ-ንዋይ ፍሰት ኹኔታ፦ «ለአሜሪካ እና ሌሎች የውጭ ንግዶች ፈታኝ» መሆኑ ተገለጠ፤ አንታናናሪቮ፥ ማዳጋስካር በተቃውሞ ሰልፍ 22 ሰዎች ተገደሉ፤ ፓሪስ፥ በፈረንሣይ የደቡብ አፍሪቃ የቀድሞ አምባሳደር ሆቴል ውስጥ ሞተው ተገኙ፤ጋዛ፥ሐማስ በዶናልድ ትራምፕ የቀረበውን ባለ 20 ነጥብ የጋዛ ምክረ-ሐሳብ እያጤነበት ነው፤ ዶሓ፥ በጋዛ ተኩስ አቁም ምክረ-ሐሳብ ላይ አስተያየት እየተሰጠ ነው

09-30
10:00

የመስከረም 19 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና

• የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ በሱዳን የከፋ የጎርፍ አደጋ እንዳይከሰት ተከላክሏል ሲሉ የውሃ ሃብት ሚንስትሩ ሃብታሙ ኢተፋ ተናገሩ ። • በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምሥራቅ ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ ትናንት እሁድ ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ወጣቶች ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር ግጭት ገብተው 3 ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች አራት ሰዎች ቆሰሉ ። • የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 18 በመቶ የነበረውን የባንኮች ዓመታዊ የብድር ዕድገት ጣሪያ ወደ 24 ከመቶ ከፍ ማድረጉን አስታወቀ።

09-29
11:30

የመስከረም 18 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና

• በአማራ ክልል በሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች በመንግስት የጸ,ጥታ ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭት መባባሱን ናዋሪዎች ተናገሩ ። • የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት «ባንዳ » ያላቸው ኃይሎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም እውን እንዳይሆን ለማደናገር» ይጥራሉ ሲል ከሰሰ። • በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምሥራቅ ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ ዛሬ ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ወጣቶች ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር ባደረጉት ግጭት ሰዎች ሳይቆስሉና ሳይሞቱ እንዳልቀረ የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ ፡፡ • አሜሪካ በጋና ላይ የጣለችውን የቪዛ ገደብ ማሻሻሏን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

09-28
13:20

የመስከረም 17 ቀን 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና

የጋምቤላ ክልል መንግስት ለ128 ታራማዎች ይቅርታ ማድረጉን አስታወቀ። የቀድሞው የሶሪያ ፕረዚደንት ባሽር አል አሳድ የእስር ትዕዛዝ እንደወጣባቸው የሐገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ። ከፈረንሳይ በእንግሊዝ የባሕር ወሽመጥ በላስቲክ ጀልባ አቋርጠው ወደ እንግሊዝ ለመሻገር ከሞከሩ ስደተኞች መካከል 2 ሴቶች መሞታቸውን

09-27
12:21

የመስከረም 16 ቀን 2018 የዓለም ዜና

የመስቀል ደመራ ክብረ በዓል ፣ ኢትዮጵያ እና ሩሲያ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ለመገንባት ተፈራረሙ ፣ በደቡብ ሱዳን የተጠናከፈው አመፅ፣ ዩናይትድ ስቴትስ የላይቤሪያ የቀድሞ የአማፂያን አዛዥን በግዳጅ መለሰች፣ የትራምፕ አስተዳደር ለውጭ ሀገር ዜጎች የንግድ መንጃ ፈቃድ እንዳያገኙ ገደብ ጣለ

09-26
09:31

የሐሙስ መስከረም 15 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና

ሙጃ፥ ሰሜን ወሎ በመንግሥት ጦር እና በፋኖ ታጣቂዎች ውጊዪያ እየተደረገ ነው፤ መቐለ፥ ስምንት የሲቪል ማኅበራት ለሰላም ጥሪያቸው በጎ ምላሽ አለማግኘታቸውን ዐሳወቁ፤ ፓሪስ፥ የፈረንሳይ የቀድሞ ፕሬዚደንት አምስት ዓመት ተፈረደባቸው፤ ሮም፥ ጣሊያን እና ስፔን ለጋዛ ሠርጥ ነዋሪዎች ርዳታ የጫነች መርከብን ለማገዝ የጦር መርከቦችን አሰማሩ፤ ጋዛ፥ በእሥራኤል ጦር ጄቶች ጥቃት ቢያንስ 17 ሰዎች ተገደሉ፤ ዴልሂ፥ ሕንድ ሕይወት ያጠፋ ነውጥ በተቀሰቀሰባት ላዳክህ ውስጥ አስቸኳይ ጊዜ አወጀች

09-25
10:43

የመስከረም 14 ቀን 2018 የዓለም ዜና

የኢትዮጵያ ፀጥታ አስከባሪዎች ከሶስት ሳምንት በፊት ያሰሯቸዉ ሁለት የሸገር ኤፍ ኤም ጋዜጠኞች ዛሬ በዋስ ተለቀቁ።ጋዜጠኞቹ እንዲለቀቁ የተለያዩ መገናኛ ዘዴዎችና የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ተቋማት ሲጠይቁ ነበር።-ለጋዛ ሕዝብ ርዳታ ጭነዉ የነበሩ ጀልባዎችን የእስራኤል ጦር በሰዉ አልባ አዉሮፕላን ደብድቧል መባሉ እንዲጣራ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠየቀ---።የእስራኤል ጦር ዛሬ ጋዛ ዉስጥ 40 ሰዎችን ገድሏል።---የሩሲያና የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል ሐገራት ጠብና ፍጥጫ እየከረረ ነዉ።ትንሺቱ የቀድሞ የሶቭየት ሕብረት ሪፐብሊክ ኢስቶኒያ ከሩሲያ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር እያጠረች ነዉ።

09-24
10:25

የማክሰኞ መስከረም 13 ቀን፣ 2018 ዓ.ም የዓለም ዜና

ቦን፥ የደኅንነት ስጋት እንዳሳሰባቸው የጃራ ተፈናቃዮች መጠለያ ነዋሪዎች ገለጡ፤ ለንደን፥ ኢትዮጵያዊው ተገን ጠያቂ በወሲባዊ ጥቃት 12 ወራት ተበየነበት፤ ናይሮቢ፥ የኬንያ አየር ማረፊያ ሠራተኞች አድማ ለመምታት የሰባት ቀናት ገደብ ሰጡ፤ ርፉር፥ ሱዳን ውስጥ በኮሌራ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ3,000 መብለጡ ተገለጠ፤ ባማኮ፥ በወታደራዊ ኹንታ የሚመሩ ሦስት የምዕራብ አፍሪቃ አገራት ከ(ICC)መውጣታቸውን በይፋ ዐሳወቁ፤ ዋሽንግተን፥ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ አንቲፋን አሸባሪ ሲሉ ፈረጁ፤ ብራስልስ፥ ኔቶ የአየር ክልል እየጣሰች ነው ያላትን ሩስያን አስጠነቀቀ

09-23
11:03

የመስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና

የመስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ፣ነጻ ጋዜጠኞችን ማዋከብን እንዲያቆሙ ተጠየቁ። ሂዩመን ራይትስ ዋች ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፣ሀሳባቸውንና አመለካከታቸውን በነጻነት የመግለጽ መብታቸውን በመጠቀማቸው የታሰሩትን በሙሉም በአስቸኳይ እንዲለቁ ጥሪ አቅርቧል። ባሕር ዳር ከተማ አቅራቢያ በደረሰ የመኪና አደጋ 3 የአንድ ቤተሰብ አባላትን ጨምሮ 11 ሰዎች ሞቱ ። 10 ሰዎችም ቆሰሉ ለፍልስጤም መንግስት እውቅና የሚሰጡ ሀገራት ቁጥር እየጨመረ ነው። ዛሬ ኒውዮርክ በሚካሄድ ጉባኤ ተጨማሪ ሀገራት ለፍልስጤም መንግሥት እውቅና ይሰጣሉ ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

09-22
11:13

የመስከረም 11 ቀን 2018 የዓለም ዜና

የዛሬው የዓለም ዜና በካፋ ዞን በህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ላይ በደረሰ አደጋ በ27 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ፣ብሪታንያ፣ ካናዳ እና አውስትራሊያ በዛሬው ዕለት ለፍልስጤም መንግስትነት በይፋ እውቅና መስጠታቸውን እና ርምጃው በእስራኤል እና በዩናይትድ ስቴትስ ዘንድ ውግዘት ማስከተሉን፤በቁጥጥር ስር የዋሉት የደቡብ ሱዳን የቀድሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ነገ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ መባሉን እንዲሁም የኬንያ አትሌቶች ዛሬ በተካሄደው የበርሊን ማራቶን በሁለቱም ፆታዎች ማሸነፋቸውን ያስቃኛል።

09-21
08:09

DW Amharic የመስከረም 10 ቀን 2018 የዓለም ዜና

የኢትዮጵያ መንግሥት አራት ጄኔራልነትን ጨምሮ ለ66 ከፍተኛ ወታደራዊ የጦር መኮንኖች ማዕረጎች ሰጠ። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድን ቀጠና “ሰላም ለማጠናከር ባላት ቁርጠኝነት” እንደተበረታቱ በአሜሪካ ውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ ማሳድ ቡሎስ ተናገሩ። እስራኤል በጋዛ በፈጸመቻቸው ጥቃቶች 34 ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የጤና ባለሥልጣናት አስታወቁ። የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ከአሜሪካ አቻቸው ዶናልድ ትራምፕ እንደሚገናኙ አስታወቁ። የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የኤች-ዋን ቢ (H-1B) ቪዛ አመልካቾች በዓመት 100,000 ዶላር እንዲከፍሉ የሚያስገድድ ትዕዛዝ አጸደቁ።

09-20
10:56

የመስከረም 9 ቀን 2018 የዓለም ዜና

አርዕሥተ ዜና፣ -ከሁለት ሳምንት በፊት አዲስ አበባ ዉስጥ የታሰሩ ሁለት ኢትዮጵያዉያን ጋዜጠኞች ፍርድ ቤት በዋስ እንዲለቀቁ ቢወስንም አለመለቀቃቸዉን ባልደረቦቻቸዉ አስታወቁ።የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቾች ጋዜጠኞቹ እንዲለቀቁ እየጠየቁ ነዉ።---የጋዛ ጦርነት ለዛላቂዉ እንዲቆም፣እስራኤል ለጋዛ ሕዝብር ርዳታ እንዳይደርስ የጣለችዉ እገዳ እንዲነሳና ሐማስ ያገታቸዉ እስራኤላዉን እንዲለቀቁ ለፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት የቀረበዉን ረቂቅ ዉሳኔ ዩናይትድ ስቴትስ ዉድቅ አደረገችዉ።----ሳዑዲ አረቢያ የሚደርስባትን ጥቃት ለመከላከል የፓኪስታንን የኑክሌር መሳሪያና ዕዉቀት ልትጠቀም እንደምትችል ኢስላምአባድ አስታወቀች።

09-19
11:01

የመስከረም 8 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና

የአፍሪካ ኅብረት በሱዳን የተኩስ አቁም ላይ እንዲደረስ እና በሀገሪቱ የሚመራ ውይይት ለማስጀመር ጥረቱን እንደቀጠለ የኅብረቱ ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ማሕሙድ አሊ ይሱፍ ተናገሩ። ኮንጎ ውስጥ በድጋሚ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ በአጭር ጊዜ ውስጥ የበርካቶች ህይወት መቅጠፉን የዓለም የጤና ድርጅት አስታወቀ። ሳዑዲ አረቢያ እና የኑኩልየር የጦር መሳሪያ የታጠቀችው ፓኪስታን አንዱ ሌላውን ካልታሰበ ጥቃት ለመከላከል የሚያስችል ነው የተባለለት ስምምነት ደረሱ ።

09-18
11:23

የመስከረም 7 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና

የመስከረም 7 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና አቶ ክርስቲያን ታደለ እና አቶ ዮሐንስ ቧያለው መታመማቸውን ጠበቃቸው ተናገሩ። ሁለቱ የምክር ቤት አባላት በሀገር ውስጥ የተሻለ ህክምና ማግኘት እንደሚፈልጉም ለጠበቃቸው ነግረዋቸዋል። ወደ ግሪክ በመጓዝ ላይ በነበረች የበፕላስቲክ ጀልባ ሲጋዙ የነበሩ ቢያንስ 50 የሱዳን ስደተኞች በምሥራቅ ሊቢያ የባህር ጠረፍ ላይ መሞታቸውን IOM አስታወቀ። ትናንት ማምሻውን ከባለቤታቸውና ከአሜሪካ ባለሥልጣናት ጋር ብሪታንያ የገቡት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ በዊንድሶር ቤተ መንግስት በእንግሊዙ ንጉስ ሳልሳዊ ቻልርስ ዘውዳዊ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

09-17
08:58

የመስከረም 6 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና

የደቡብ ሱዳን ባለሥልጣናት ሀገሪቱ ነጻነቷን ካገኘችበት ጊዜ ጀምሮ በሚሊየኖች የሚቆጠር ዶላር መዝረፋቸውን የተመድ አስታወቀ። የጁባ መንግሥት ክሱን አስተባብሏል። እስራኤል ዛሬ በማለዳ ጋዛ ከተማ ላይ የተገመተውን የምድር ጥቃት ጀመረች። እርምጃዋ ከተመድ ጠንካራ ትችት አስከትሏል። ባለፈው ዓመት ጀርመን ውስጥ በተካሄደ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የፖሊስ መኮንን በስለት ወግቶ የገደለ የአፍጋኒስታን ዜጋ በዛሬው ዕለት የዕድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት። የታሊባን መሪዎች በአንድ የአፍጋኒስታን ክፍለ ሀገር ውስጥ ገመድ አልባ የኢነርኔት አገልግሎት ወይም ዋይፋይ አገዱ። ምክንያቱ ኢስነምግባራዊነትን ለመከላከል የሚል ነው።

09-16
11:44

የመስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም. የዓለም ዜና

የመስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና እስራኤል ዛሬ በጋዛ ከተማ በፈጸመችው የአየር ድብደባ ቢያንስ 16 ፍልስጤማውያን መገደላቸውንና ህንጻዎችም መውደማቸውን የፍልስጤም ባለሥልጣናት አስታወቁ። እስራኤል በጋዛ ሲቲ የአየር ድብደባ ባካሄደችበት በዛሬው እለት የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩብዮ መንግስታቸው እስራኤልን እንደሚደግፍ ተናግረዋል። ሩብዮ ሀማስ እንደታጣቂ ቡድን ህልውናው ማክተም እንዳለበትም ተናግረዋል። ሩስያ ሀብቴን ለመውሰድ በሚቃጣ ማንኛውንም ሀገር ላይ እርምጃ እወስዳለሁ ስትል ዛሬ የአውሮፓ መንግስታትን አስጠነቀቀች። ዜናው በዝርዝር

09-15
09:48

የመስከረም 4 ቀን 2018 ዓ/ም የዓለም ዜና

• በኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ከወሰዱ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች መካከል 8.4 በመቶው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባ ውጤት ማግኘታቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። • የመሐመድ ሐምዳን ደጋሎ የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል በሀገሪቱ ደቡባዊ ክፍል የሚገኙ ቁልፍ የብሔራዊው ጦር ይዞታዎች እና የህዝብ መገልገያ የመሰረተ ልማቶችን በድሮን እንዳጠቃ አንድ ከፍተኛ የጦር መኮንን ተናገሩ። • እስራኤል በጋዛ ማዕከላዊ ክፍል የምትወስደውን ወታደራዊ እርምጃ ስታጠናክር የከተማዋ ነዋሪዎች ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ ለቀው መውጣት ጀመሩ ።

09-14
08:37

Recommend Channels