በኒውዮርክ የግራ ክንፍ ፖለቲከኛ በከንቲባነት ማሸነፍ አነጋጋሪ ሁኗል
Description
በዩናይትድ ስቴትስ የኒውዮርክ ምርጫ የግራ ክንፉ ፖለቲከኛ ዞኽራን ማምዳኒስ የከተማዪቱ ከንቲባነትን ማሸነፋቸው አነጋጋሪ ሁኗል ። የአሜሪካ ዴሞክራቶች የግራ ክንፍ ዴሞክራቱ ስለማሸነፋቸው ብዙም አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል ።
የአውሮጳ የግራ ክንፍ ፖለቲከኞች ግን ከወዲሁ ደስታቸውን እየገለጡ ነው ። ዞኽራን ማምዳኒ በኒውዮርክ ምርጫ በከንቲባነት ሲያሸንፉም የመጀመሪያው ሙስሊም ናቸው ። ልክ እንደ ለንደን ከንቲባ ሣዲቅ ካን ሁሉ ዞኽራን ማምዳኒ በበዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የቃላት ጥቃት ደርሶባቸው እንደነበር በተለያዩ የመገናኛ አውታሮች ተዘግቧል ።
በመላው ዩናይትድ ስቴትስ በተከናወነው የመካከለኛው የሥልጣን ዘመን ምርጫ (mid term election) በተለያዩ ግዛቶች ተከናውኗል ። በብዙ ቦታዎች ዴሞክራቶች ማሸነፋቸው ተገልጧል ። ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሞ የዋሽንግተን ወኪላችን አበበ ፈለቀን በስልክ አነጋግሬው ነበር ። አበበ፦ የምርጫ ውጤቱ በትራምፕ አስተዳደር ላይ ያለው አንደምታ ምንነትን በማብራራት ይጀምራል ።
ለመሆኑ እንዲህ አነጋጋሪ የሆኑት ሰውዬ ማን ናቸው? እንዴትስ የዴሞክራቶቹ ከተማ በሆነችው ኒውዮርክ ሊያሸንፉ ቻሉ?
ዞኽራን ማምዳኒስ በፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ አይወደዱም ። እንደውም ፕሬዚደንቱ ኒውዮርክ ከተማ ላይ ጫና እንደሚያሳድሩ ዝተዋል ። በአንጻሩ ደግሞ የአውሮጳ የግራ ክንፍ ፖለቲከኞች ከወዲሁ ደስታቸውን እየገለጡ ነው ። ይኼ ምንን ያሳያል?
ሙሉ ቃለ መጠይቁን ከድምፅ ማገናኛው ማድመጥ ይቻላል ።
አበበ ፈለቀ/ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ























