የመስከረም 28 ቀን 2018 የዓለም ዜና
Update: 2025-10-08
Description
-ኤርትራና ህወሓት ኢትዮጵያን ለመዉጋት እየተዘጋጁ ነዉ በማለት የኢትዮጵያ መንግሥት ከሰሰ።የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በፃፈዉ ደብዳቤ እንዳለዉ የኤርትራ መንግሥትና «አክራሪ» ያለዉ የህወሓት አንጃ ፋኖን ይረዳሉ፣ ኢትዮጵያን ለመዉረርም እየተዘጋጁ ነዉ።---የእስራኤል ጦር ሁለት ሳምንት ሳይሞላ ለሁለተኛ ጊዜ ለጋዛ ሕዝብ ርዳታ የጫኑ የጀርልባዎች ቅፍለትን አገደ።145 በጎ አድራጊዎችን ያዘ።-የሩሲያና የ,ዩናይትድ ስቴትስ ዉዝግብ እየተካረረ ነዉ።ዩናይትድ ስቴትስ የኑክሌር ቦምብ ለመሞከር፣ ለዩክሬን ኑክሌር ማወንጨፍ የሚችል ሚሳዬል ለማስታጠቅም ተዘጋጅታለች በማለት ሩሲያ ወቅሳለች።
Comments
In Channel
























