የሰደድ እሳት በአሜሪካ ደቡባዊ ካሊፎርኒያ
Description
በአሜሪካ ደቡባዊ ካሊፎርኒያ የሰደድ እሳት ተነስቶ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ እና የሰው ህይወት መጥፋቱ እየተነገረ ነው። በዚህ ግዛት ተለይም የብዙ ኢትዮጵያውያን መኖሪያ በሆነው የሎስ አንጀለስ ከተማ አቅራቢያ ቃጠሎው በርትቷል ተብሏል።
የሰደድ እሳቱ እስካሁን ከ105 ካሬ ኪሎ ሜትር በላይ ተቃጥሏል፣ በአደጋው አምስት ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። ከ70,000 በላይ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል። ከ1.6 ሚሊዮን በላይ ቤቶች ደግሞ የመብራት መቆራረጥ አጋጥሟቸዋል።
ከ1,000 በላይ ግንባታዎችም ወድመዋል። እሳቱን በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረት እየደረገ ቢሆንም በጠንካራ ንፋስ እና በረጅም ጊዜ ድርቅ የተነሳ የሰደድ እሳቱ በፍጥነት እየተስፋፋ መሆኑ ተገልጿል። በቃጠሎው በዩናይትድ ስቴትስ የታዋቂ ሰዎችን ጨምሮ በርካታ መኖርያ ቤቶች መውደማቸዉ እየተዘገበ ነዉ። እስካሁን በቃጠሎዉ በትንሹ የአምስት ሰዎች ህይወት መጥፋቱን ዶቼ ቬለ DW ዘግቧል። በክልሉ አምስት ዋና ዋና የእሳት ቃጠሎ ቦታዎች ላይ ወደ 1,900 የሚጠጉ ሕንፃዎች ወድመዋል፤ ወደ 130,000 ሰዎች ቦታዉን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸዋል ። በሽዎች የሚቆጠሩ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ሰደድ እሳቱን ለማጥፋት እየተረባረቡ መሆኑም ተነግሯል። ከሦስት ቀናት በኋላ ቀጠሮ የተያዘለት ዓመታዊ ግዙፉ የሆሊዉዱ የኦስካር የሽልማት መድረክ በርካቶች በሰደድ እሳቱ ቤታቸዉን ጥለዉ ቦታዉን መልቀቅ በመገደዳቸዉ ምክንያት የሽልማት መድረኩ፤ ወደ ጥር 18 ቀን መተላለፉም ተሰምቷል። ትናንት ረቡዕ በሆሊውድ ኮረብቶች ላይ የተቀሰቀሰው አዲስ የሰደድ እሳት አደጋ ቦታዉ ላይ የሚገኙትን ቱሪስቶችን ብሎም የቱሪስት መስዕብ ቦታዎችን ሁሉ አደጋ ላይ መጣሉ እየተዘገበ ነዉ።
ሙሉ ቃለ ምልልሱን የድምፅ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።
አበበ ፈለቀ
እሸቴ በቀለ
ፀሀይ ጫኔ























