DiscoverDW | Amharic - Newsየትግራይ ኃይሎች ተቃውሞን ማኅበረሰቡም እንዲቀላቀል ተቃዋሚዎች ጥሪ አስተላለፉ
የትግራይ ኃይሎች ተቃውሞን ማኅበረሰቡም እንዲቀላቀል ተቃዋሚዎች ጥሪ አስተላለፉ

የትግራይ ኃይሎች ተቃውሞን ማኅበረሰቡም እንዲቀላቀል ተቃዋሚዎች ጥሪ አስተላለፉ

Update: 2025-10-16
Share

Description

በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎችየትግራይ ኃይሎች አባላት ሰሞኑን የጀመሩትን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል እንዲቀላቀል ጥሪ ጠየቁ ። ዓረና ትግራይ ለሉአላዊነት ዴሞክራሲ የቆየ የትግራይ ሕዝብ የለውጥ ፍላጎት ወደ ጎዳናዎች መፍሰስ ጀምሯል ብሏል ። የትግራይ ኃይሎች ባለፈው ሰኞ የጀመሩት ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል ።



ባለፈው ሰኞ በመቐለ የተጀመረው የትግራይ ኃይሎች አባላት ተቃውሞ ዛሬም በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ቀጥሎ የዋለ ሲሆን፤ በመቐለ ደግሞ የጦር ጉዳተኞች የተለያዩ ጥያቄዎች በማንሳት በከተማዋ ሰልፍ አድርገዋል። እነዚህ ሰሞኑን በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች መንገዶች በመዝጋት ጭምር ተቃውሞ እያደረጉ ያሉት የትግራይ ኃይሎች አባላት ከደሞዝ እና ጥቅማጥቅም ጥያቄ በዘለለ የለውጥና የማኅበራዊ ፍትህ ፍላጎት ነው በማለት በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገልፀዋል።



የቀጠለው ተቃውሞ



በዚሁ ጉዳይ ዙርያ ዛሬ መግለጫ ያሰራጨው ተቃዋሚው ዓረና ትግራይ ለሉአላዊነት እና ዴሞክራሲ ምልክት እያሳየ የቆየ የትግራይ ሕዝብ የለውጥ ፍላጎት ወደ ጎዳናዎች መፍሰስ ጀምሯል ብሏል። ከዚህ በፊት በተበታተነ መንገድ የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጥያቄዎቻቸው እና ተቃውሞቻቸው ሲገልፁ ቆይተዋል ያለው ዓረና ትግራይ ለሉአላዊነት እና ዴሞክራሲ፥ በማሳያነትም የአስተዳደር መዋቅሮች በኃይል ከመቀየር ጋር ተያይዞ የነበረው ተቃውሞ፣ የጦር ጉዳተኞች እና ምልስ ታጋዮች ጥያቄዎች፣ መምህራን እና አጠቃላይ መንግስት ሠራተኞች የሚያቀርቡት የውዝብ ደሞዝ ጥያቄ፣ ከወንጀሎች መበራከት ጋር በተያያዘ ያለው የሕዝብ ቅሬታ በማሳያነት አቅርቧል።



የትግራይ ኃይሎች



የትግራይ ኃይሎች እነዚህ የሕዝብ ተቃውሞዎች ከማፈን ወጥተው የራሳቸው ጥያቄዎች ይዘው ወደጎዳናዎች መውጣታቸው ዓረና ትግራይ እንደሚደግፈው የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ዓምዶም ገብረስላሴ ተናግረዋል።



ከዚህ በተጨማሪ ተመሳሳይ መግለጫ ያወጣው የትግራይ ነፃነት ፓርቲ በበኩሉ በትግራይ ያለው ስርዓት ለመገርሰስ ወጣቶች፣ ሴቶች እና ሌሎች የማኅበረሰብ ክፍሎች ጥያቄዎቻቸው ይዘው ተቃውሞው ይቀላቀሉ ሲል ጥሪ አቅርቧል።



የፓርቲዎች ድጋፍ



በትግራይ ኃይሎች እየተደረጉ ያሉተ ተከታታይ ተቃውሞዎች ተከትሎ በክልሉ የሰው እና ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ሲስተጓጎል ሰንብቷል። በዚህም በኤኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ እንቅስቃሴ ጫና ተፈጥሯል።



የዓረና ትግራይ ሊቀመንበር አቶ ዓምዶም ገብረስላሴ እንደሚሉት በትግራይ ኃይሎች አባላት በሰልፍ እየቀረቡ ያሉ አጀንዳዎች የመላው ሕዝብ ጉዳዮች ስለሆኑ ፖርቲዎች፣ ሲቪል ማኅበራዊ እና አጠቃላይ ለውጥ ፈላጊ ሕዝብ ሊቀላቀላቸው ይገባል ብለዋል።



ትናንት የትግራይ ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ያሰራጨው መረጃ እንደሚያመለክተው፦ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ በዚሁ የትግራይ ኃይሎች ጥያቄዎች አስቸኳይ ስብሰባ ማድረጉ ያስታወቀ ሲሆን፤ ሲዘጋጅ ቆየ የተባለ የትግራይ የፀጥታ ኃይሎች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ረቂቅ ደንብ ወደሚመለከታቸው አካላት መምራቱ መግለፁ ይታወሳል።



ሚሊዮን ኃይለሥላሴ



ማንተጋፍቶት ስለሺ



ታምራት ዲንሳ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የትግራይ ኃይሎች ተቃውሞን ማኅበረሰቡም እንዲቀላቀል ተቃዋሚዎች ጥሪ አስተላለፉ

የትግራይ ኃይሎች ተቃውሞን ማኅበረሰቡም እንዲቀላቀል ተቃዋሚዎች ጥሪ አስተላለፉ

ሚሊዮን ኃይለ-ሥላሴ