የትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ
Description
ሰሞኑን በትግራይ ክልል የተለያዩ ቦታዎችየትግራይ ኃይሎች ለቀናት መንገድ በመዝጋት ተቃውሞ ሲያሰሙ እንደነበር ዘግበናል ። በትግራይ ደቡባዊ ዞን የሚገኙ የትግራይ ኃይሎች አባላት ባለፈው ሳምንት በሞኾኒ መንገድ በመዝጋት ወደ አላማጣና ወደ መቐለ የሚደረግ የተሽከርካሪዎች ጉዞ አስተጓጉለው መዋላቸው ተነግሮ ነበር ።
ከዚያ በተጨማሪ ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ዓዲግራት፣ ውቅሮ እና አጉላዕ ከተሞች ወደ መቐለ የሚወስዱ መንገዶችንም ዘግተው ነበር ። ስለ ትግራይ ወቅታዊ የፖለቲካ እና የፀጥታ ሁኔታ ደግሞ ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት ከባልደረባዬ ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔርን አነጋግሬው ነበር ። በአጠቃላይ የክልሉ የፀጥታ ኃይላት ጥያቄያቸው ምን ነበር የሚለውን ጥያቄ በማብራራት ይጀምራል ።
የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ በዚሁ የትግራይ ኃይሎች ጥያቄዎች ጉዳይ አስቸኳይ ስብሰባ አድርጎ እንደነበር ይታወቃል ። ሲዘጋጅ መቆየቱ የተነገረለት «የትግራይ የፀጥታ ኃይሎች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ» የሚል ረቂቅ ደንብም ወደሚመለከታቸው አካላት መምራቱ በወቅቱ ተገልጧል ። የፀጥታ ኃይላቱ በበኩላቸው ከአመራሩ ጋር ተወያይተው ችግሩን እንደፈቱም ተጠቅሷል ። በእርግጥ ችግሩ ተፈትቷል ወይ?
አሁንስ ጥያቄው በምን አይነት ሁኔታ ላይ ነው ያለው?
በክልሉ የመልካም አስተዳደር እና የሙስና እንዲሁም ቀደም ሲል የጠቀስነው የፀጥታ ችግሮችም በተደጋጋሚ ይነሳሉ ። ችግሩ ምን ያህል አሳሳቢ ነው ይባላል?
የሕወሓት ከፍተኛ አመራር ባደረጉት ስብሰባ በፀጥታ ኃይላት እና በአመራሩ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ ለሚያደርጉ ብሎም ስም ለሚያጠለሹ አንዳችም ትእግስት እንደሌለ በመጥቀስ «ዜሮ ቶለራንስ» ሲሉ ተደምጠዋል ። ይህ በተለይ በመናገር ነጻነት፤ በጋዜጠኞች እና በፕሬሱ ላይ ምን ፈጥሯል?
በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የትግራይ ኃይሎች አባላት ሰሞኑን ጀምረውት የነበረው የተቃውሞ እንቅስቃሴን ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል እንዲቀላቀል ሲሉ ጥሪ አሰምተው ነበር ። በአጠቃላይ ግን ምሁራን፣ ፖለቲከኞች እና ኅብረተሰቡ ምን እያለ ነው ።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
አዜብ ታደሰ
























