DiscoverDW | Amharic - Newsየሰሜን ሸዋ ዞን እና የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዮ ዞን አጎራባች አካባቢዎች ማህበረሰቦች ግንኙነት
የሰሜን ሸዋ ዞን እና የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዮ ዞን አጎራባች አካባቢዎች ማህበረሰቦች ግንኙነት

የሰሜን ሸዋ ዞን እና የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዮ ዞን አጎራባች አካባቢዎች ማህበረሰቦች ግንኙነት

Update: 2025-12-18
Share

Description

ለዘመናት የገነቡትን ወዳጅነት የሚሽረሽርግጭት ውስጥ ገብተው ባለፉት 6 ዓመታት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ እና የኦሮሞ ብሔረሰብ አዋሳኝ ቦታዎች የሚኖሩ ኗሪዎች በብሄር ስም ተቧድነው በፈጠሩት ግጭት በርካቶች ሞተዋል፣ተቋማትም ወድመዋል፡፡ ‹‹ያለፈው ዓመት ምንም ተወርቶ የማያልቅ እና የሚፈታም አይመስልም፤ እዚህ ሀገር ላይ ሰው መልሶ የሚኖርበትምአይመስልም፤ የሞቱትን ብናጣ፣ የሄዱትንም ብናጣ አሁን ጥሩሰላም ላይ ነው ያለነው፡፡››



በርካታ ሕይወትና ንብረት የወደመበት የዕርስ በርስ ግጭት በሰላም ተፈታ



በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን የጂሌ ጥሙጋ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አቶሀሜ ሙሄ በግጭቱ የሰው ህይወት ከመጥፋቱ በዘለለ ለዘመናትየገነባነው ወዳጅነትን ነው ያጣነው ይላሉ፡፡ ‹‹ሁላችንም ተጎዳን በሰው ህይወት፣ በንብረት ሁሉም ነገር ከላይም ከታችም ማንም ተጠቃሚ የሚሆን የለም፣ በአማራም ብሔረሰብ በኦሮሞም ብሔረሰብ በዚህ ጉዳት እንጂ የሚጠቀም የለም፡፡›› በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ እና የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አዋሳኝቦታ ላይ የሚገኙ የሁለቱ ብሔር ነዋሪዎች የፈጠሩት ግጭት የእርስ በእርስ ግጭት ነው የሚሉት የሀገር ሽማግሌዎች አቶ ጠጄ አደፍርስ ከሚያዝያ 2017 ዓ/ም በኋላ በመነጋገራችን ዳግም የብሔር ግጭት እንዳይከሰት አድርገናል ይላሉ፡፡



‹‹ማኅበረሰቡ አብሮ የሚኖረው ጎራ ለይቶ መጣብህ መጣብኝ በሚል የነበረ ግጭት ነው፡፡ »



ከ2017 ዓ/ም ሚያዝያ መጨረሻ ጦርነት ከተካሄደ በኋላ ኦሮሞና አማራ በተለያዩ መንገድ የሀገር ሽማግሌዎች ሕዝብ ለህዝብ ግንኙነት ፈጥረው ታርቆ ከዚያ ወዲህ ቀጠናችን ሰላም ነው፡፡››

በባለፈው ዓመት በነበረው ግጭት አካባቢያችንን ለቅቀን ተሰደንነበር ያሉት አቶ አወቀ ታደሰ አሁን ላይ ተነጋግረን ወደሰላምበመምጣታችን በይፍራታ እና ግድም ወረዳ አዲስ ዓለም ነጌሶቀበሌ ያደረ መሬታችንን ለማረስ በቅተናል ይላሉ፡፡

‹‹ዓምና እዚህ ቦታ ቀበሌያችን ላይ አልገባንም ነበር፤ ሰውምሲገባ የሚያባረው ነበር በመነጋገራችን ምክንያትሰብሎችንዘርተን አምርተናል ጌታ ይመስገን ይላሉ፡፡››





የፖለቲካ መሪዎች ቀርቦ አለመነጋገር ለግጭቱ መባባስ ምክንያት ነበር።



ለ6 ዓመታት እንደ ሀገር በተፈጠረ የፖለቲካ አለመረጋጋት የተከሰተው ግጭት ለበርከታ ሰዎች የህይወት ማለፍ እና ንብረትመውደም ምክንያት ነበር ያሉት በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞንይፍራታ እና ግድም ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አበራ መኮነን ከአመራሩ እስከ ህዝብ የነበረው የሰላም መነጋገር ውጤታማ መሆን ችሏል ይላሉ፡፡



‹‹በሀገራችን ላይ በተከሰተው የፖለቲካ አለመረጋጋት ህብረተሰቡ በአንድም በሌላም ሲታኮስ፣ ሲጋጭ ይውላሉየሚታኮስበትንምየሚጋጭበትንም አያውቅም የተወሰኑ የተመረጡ ሰዎችየመጀመሪያው የሚያጋጭን ነገር ለየንህዝቡን ስናገናኘውተላቀስን ምክንያቱም በግል የተጣላ የለም፤ እየተዋጋ ያለው በፖለቲካ አስተሳሰብ ችግር ምክንያት ነው፡፡››





ግጭቱ በተፈጠረበት ወቅት በሁለቱ ዞን ሃላፊዎች በኩል ተራርቆ ይሰጡ የነበሩ መግለጫዎች ለችግሩ መባባስ ምክንያት ናቸው ያሉት በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን የአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ሰይድ አመራሩ ተቀራርቦ መነጋገር ከጀመረ በኋላ ግን ለበርከታ ህይወት መጥፋት እና ንብረት መውደም ምክንያት የነበረው ግጭት ቆሟል »ብለዋል፡፡

‹‹በሰሜን ሸዋ ዞን በኩል ያለው ደብረ ብርሃን ቁጭ ብሎ መግለጫ መስጠት በእኛ በኩልም ያለው አማራውን ጠቅላላ በጅምላ ፈርጆ ዞን ላይ ሆነ መግለጫ መስጠት ነበር፤ ይህንን እስካላቆምን ድረስ የህዝብን አንድነት ማምጣት አንችልም ብለን ሁላችንም ወደ ራሳችን ተመለስን የማህበረሰብን አቅምበመጠቀም ሰላማችንን ለማፅናት ችለናል፡፡››



ኢሳያስ ገላው

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

Comments 
loading
In Channel
loading
00:00
00:00
1.0x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የሰሜን ሸዋ ዞን እና የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዮ ዞን አጎራባች አካባቢዎች ማህበረሰቦች ግንኙነት

የሰሜን ሸዋ ዞን እና የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዮ ዞን አጎራባች አካባቢዎች ማህበረሰቦች ግንኙነት

ኢሳያስ ገላው