DiscoverDW | Amharic - Newsየትራምፕ አስተዳደር ከአሜሪካ እንዲወጡ የሚፈልጋቸዉ ኢትዮጵያዉያን ሁኔታ
የትራምፕ አስተዳደር ከአሜሪካ እንዲወጡ የሚፈልጋቸዉ ኢትዮጵያዉያን ሁኔታ

የትራምፕ አስተዳደር ከአሜሪካ እንዲወጡ የሚፈልጋቸዉ ኢትዮጵያዉያን ሁኔታ

Update: 2025-12-15
Share

Description

የትራምፕ አስተዳደር ከአሜሪካ እንዲወጡ የሚፈልጋቸዉ ኢትዮጵያዉያን ሁኔታ



የትራምፕ አስተዳደር በዩናይትድ ስቴትስ፣ ለሚኖሩኢትዮጵያዉያንበጊዜያዊ የሕግ ጥበቃ በአገሪቱ ውስጥ እንዲኖሩ የፈቀደበትን አሠራር ማገዱን አስታዉቋል። የትራምፕ አስተዳደር ይህን ያስታወቀዉ ባለፈዉ ሳምንት አርብ እለት ነበር ። የሃገር ውስጥ ደህንነት ዋና ጸሐፊ ክሪስቲ ኖኤም እንደተናገሩት፤ የሃገራቱን ሁኔታ ከገመገምን በኋላ እና አግባብነት ካላቸው የአሜሪካ መንግስት ተቋሞች ምክክር ካደረግን በኋላ፤ የደኅንነት ዘርፍ ቢሮ፤ ኢትዮጵያ ከዚህ በኋላ ለጊዜያዊ ጥበቃ ሁኔታ ቅድመ ሁኔታዎችን አታሟላም። » ማለታቸዉ የመንግሥት ውሳኔዎች በሚወጡበት የፌደራል መንግሥቱ መድረክ ላይ በተለጠፈዉ ማስታወቂያ ላይ መነበቡን የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ይህ ማለት በኢትዮጵያ አስጊ ሁኔታ ስለሌለ በአሜሪካ በጊዜያዊነት የመኖርያ ፈቃድ የተሰጣቸዉ ኢትዮጵያዉያን በሦስት ወር ጊዜ ዉስጥ እንዲያሳዉቁ እና ወደ ሃገራቸዉ እንዲመለሱ ይጠይቃል።



የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ከሦስት ዓመታት በፊት ኢትዮጵያውያን በጊዜያዊ የሕግ ጥበቃ በአገሪቱ ውስጥ እንዲኖሩ የፈቀደበት አሰራር እንዲያበቃ አድርጓል። ይህ በጊዜያዊ የሕግ ጥበቃ የመኖርያ ፈቃድ ስር አሜሪካ ዉስጥ እንዲኖሩ ይፈቀድላቸዉ የነበሩት ዜጎች በአገራቸው ግጭት፤ ጦርነት የተፈጥሮ አደጋ ወይም ሌላ ለደኅንነታቸው አስጊ የሆነ የተለየ ክስተት ለመጡ ስደተኞች ወይም ተገን ጠያቄዎች ነበር። በዚህ በጊዜያዊ ሕግ ከለላ የመኖርያ ፈቃድ የሚሰጣቸዉ ሰዎች በአሜሪካ ዉስጥ እንዲኖሩ ፤ እንዲሰሩ ከአገር እንዳይባረሩ ከለላ የሚሰጥ ነበር።



ለሁለት ዓመታት ግድም በትግራይ የተካሄደዉን የእርስ በእርስ ጦርነት ተከትሎ ፤ ብሎም በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚታዩ ግጭቶች እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ተከትሎ ቀደም ሲል የነበረዉ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የጆ ባይደን አስተዳደር ለኢትዮጵያውያን የሰጠዉን ሕጋዊ ጊዜያዊ ከለላ የአሁኑ የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ሕጋዊዊ ጊዜያዊ ከለላዉን አንስቷል፤ አልያም እንዲያበቃ አድርጓል።



በዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ ጊዜያዊ ሕጋዊ ከለላ የነበራቸዉ እና አሁን የትራምፕ አስተዳደር ከአሜሪካ እንዲወጡ የሚፈልገዉ ኢትዮጵያዉያን ቁጥር ምን ያህል ነዉ? የኢትዮጵያዉያኑ ስሜት ምን ይመስላል? በካሊፎርኒያ የሚገኘዉን ወኪላችን በስልክ አነጋግረነዋል።



ታሪኩ ኃይሉ / አዜብ ታደሰ



ሸዋዬ ለገሠ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የትራምፕ አስተዳደር ከአሜሪካ እንዲወጡ የሚፈልጋቸዉ ኢትዮጵያዉያን ሁኔታ

የትራምፕ አስተዳደር ከአሜሪካ እንዲወጡ የሚፈልጋቸዉ ኢትዮጵያዉያን ሁኔታ