DiscoverDW | Amharic - Newsዶናልድ ትራምፕ ባለ 1 ሚሊዮን «የትራምፕ ወርቃማ ካርድ» ቪዛን ይፋ አደረጉ
ዶናልድ ትራምፕ ባለ 1 ሚሊዮን «የትራምፕ ወርቃማ ካርድ»  ቪዛን ይፋ አደረጉ

ዶናልድ ትራምፕ ባለ 1 ሚሊዮን «የትራምፕ ወርቃማ ካርድ» ቪዛን ይፋ አደረጉ

Update: 2025-12-12
Share

Description

የዩናይትድስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣አንድ ሚሊዮን ዶላር የሚከፈልበት፣'ጎልደን ካርድ የተሰኘ የጉዞ ማለፊያ ፈቃድ /ቪዛ/ ይፋ አደረጉ።



በሌላ በኩል፣የበርካታ የአውሮፓ አገራት ጎብኚዎች፣ወደ አሜሪካ ለመግባት፣የአምስት ዓመታት የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ታሪካቸውን እንዲያቀርቡ የሚጠየቁበት የፖሊሲ ዐሳብ ቀርቧል።



ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ያስተዋወቁት 'ጎልደን ካርድ' ቪዛ፣ወደ አሜሪካ ለመምጣት፣ቢያንስ አንድ ሚሊዮን ዶላር መክፈል ለሚችሉ የውጭ አገር ዜጎች የሚሰጥ ነው። የዚህ ቪዛ አመልካቾች፣ ማመልከቻቸው ከመታየቱ በፊት፣ ሂደቱን ለማስጀመር የሚያስችል፣15 ሺህ ዶላር መክፈልም ይጠበቅባቸዋል።



ዶቼ ቨለ ስለጉዳዩ ማብራሪያ የጠየቃቸው፣በዋሽንግተን ዲሲና ፊላዴልፊያ አካባቢ የሕግ አማካሪና ጠበቃ አቶ አሳምን መኮንን፣'ጎልደን ካርድ' ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ አሰራር እንደሆነ ገልጸዋል። "ሌሎች ፕሬዚዳንቶች እንደዚህ አድርገው አያውቁም፤ ግን አሁን አሁን ያሉት ፕሬዝዳንት የዚህ ዓይነት ቪዛ አዘጋጅቼ በተለይ ብዙ መክፈል የሚችሉ ሰዎች፣ወደዚህ ሃገር እንዲገቡ ማድረግ እፈልጋለሁ ብለው በሴፕቴምበር 2025 ላይ በፕሬዚደንታዊት ትዕዛዝ ያወጡት እና ያንን ለማስፈፀም እየመጣ ያለ የቪዛ ዐይነት ነው።



ፍትሓዊ አይደለም



አሰራሩ፣ቱጃሮች ብቻ ወደ አሜሪካ እንዲመጡ በማድረግ፣ ገንዝብ የሌላቸውን የሚያገል ነው የሚሉት አቶ አሳምን፣በሕገ መንግስቱ የተደነገገውን በሕግ ፊት እኩል የመታየት መብት የሚጥስ እንደሆነ አብራርተዋል። በመሆኑም፣ተፈጻሚነቱ በፍርድ በፍርድ ቤቶች ተግዳሮት ሊገጥመው እንደሚችል የሕግ ባለሙያው እምነታቸውን ገልጸዋል።



የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን የሚጠይቀው የፖሊሲ ዐሳብ



በሌላ በኩል፣የአውሮፓ በርካታ አገራት ጎብኚዎች፣ወደ አሜሪካ ለመግባት የአምስት ዓመታት የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ታሪካቸውን እንዲያቀርቡ የሚጠይቅ የፖሊሲ ውሳኔ ዐሳብ ቀርቧል።



ይህ ፖሊሲ፣በርካታ የአሜሪካ አጋር ናቸው የሚባሉ አገሮችን የሚመለከት እንደሆነ የሕግ ባለሙያው አስረድተዋል። ''እነዚህ 42 ሃገሮች፣ከዚህ በፊት ወደ አሜሪካ ያለ ቪዛ የሚገቡ፣በጣም የአሜሪካ ጓደኛ ሊባሉ ሊባሉ የሚችሉ አገሮች፣ለምሳሌ እንደነ ብሪታኒያ፣ፈረንሳይ፣አውስትራሊያ እና ጀርመንን የመሳሰሉት ናቸው።"



ይህ የፖሊሲ ምክረ ዐሳብ፣የአሜሪካን ቱሪዝም ገቢ አደጋ ላይ ይጥላል የሚለውን ስጋት ውድቅ ያደረጉት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ቅድሚያ የሚሰጡት ለደህንነት ጉዳይ እንደሆነ ተናግረዋል። ይህ የፖሊሲ ዐሳብ ከመቅረቡ በፊትም ቢሆን፣ወደ አሜሪካ የሚመጡ ጎብኚዎች ቁጥር በመቀነሱ፣አገሪቱ እስካለፈው የጎርጎሮሳዊው ጊዜ አቆጣጠር መስከረም ወር ድረስ፣ ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን 12 ነጥብ አምስት ቢሊዮን ዶላር ማጣቷን ዘገባዎች ያሳያሉ።



የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር፣ ስደተኞችን አስመልክቶ አሰራሩን ከእለት ወደ ዕለት እያጠበቀ የመጣበትን ምክንያት በተመለከተ ዶቼ ቬለ የጠየቃቸው፣በሚኒሶታ ግዛት የስደተኞች ጉዳይ ጠበቃ፣ አቶ ሙሉአለም ጌታቸው እንደሚከተለው አብራርተዋል።



«ፖለቲካ ነው»



"ፖለቲካው አሁን የጋለበት ሁኔታ ነው። ብዙ ጊዜ ይሄን ነገር ከፖለቲካ ውጭ ባናየው በጣም የምንረዳው ይመስለኛል። የኢሚግሬሽን ሂደት ፖለቲካ ነው፣ በጣም ብዙ ነገሩ ለምን? አንደኛ፣ትራምፕ የምርጫ ዘመቻ አድርገው የመጡበት ዋነኛው ጉዳይ፣ ኢሚግሬሽን ነው።'' ሌላው ምክንያት ደግሞ፣ በአሜሪካ በቅርቡ የተካሄዱ የአካባቢና ማዘጋጃ ቤታዊ ማዘጋጃ ቤታዊ ምርጫዎች ውጤት፣ ወደ ዲሞክራቲክ ፓርቲው ማዘንበላቸው እንደሆነ የሕግ ባለሙያው ጠቁመዋል።



"ባለፉት ሁለት ወራት የተመለከትነው ፖለቲካዊ ለውጥ አለ አሜሪካ ውስጥ፣ ከፍተኛ የሆነ የዲሞክራቶች ወጀብ እየመጣ ነው። አሁን ብዙ ማኅበረሰብ፣ትራምፕ ቃል የገቧቸውን ነገሮች ባለመፈጸማቸው፣ ስልጣናቸውን ራሳቸውንና እዛው አካባቢ ያሉትን ሰዎችን ብቻ ጠቀመ በሚል እምነት ኑሮ ውድነቱ ባለመቀነሱ፣ ቃል የተገቡ ነገሮች ሁሉ ባለመተግበራቸው፣ ስደተኛው ማኅበረሰብ ከሚፈልገው ገደብ በላይ በመሄዱ የፖለቲካ ድጋፋቸው ቀንሷል። ስለዚህ ይሄን መሰረቱን እንደገና ለመሰብሰብ እና አንድ ለማድረግ መሰረቱ የሚስማማበትን አጀንዳ ማራገብ ያስፈልጋል፣ ይኸውም የስደተኞች ጉዳይ ነው'' ብለዋል።



ከሁለት ሳምንት በፊት አንድ አፍጋናዊ ስደተኛ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በሁለት የአሜሪካ ብሔራዊ ዘብ አባላት ላይ በፈጸመው ጥቃት፣ አንዷ ስትሞት፣ ሌላኛው ደግሞ ክፉኛ መቁሰሉም፣ የትራምፕ አስተዳደር ስደተኞች ላይ የተጠናከረ እርምጃ እንዲወስድ አድርጎታል።



ታሪኩ ኃይሉ



ማንተጋፍቶት ስለሺ



ታምራት ዲንሳ

Comments 
loading
In Channel
loading
00:00
00:00
1.0x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

ዶናልድ ትራምፕ ባለ 1 ሚሊዮን «የትራምፕ ወርቃማ ካርድ»  ቪዛን ይፋ አደረጉ

ዶናልድ ትራምፕ ባለ 1 ሚሊዮን «የትራምፕ ወርቃማ ካርድ» ቪዛን ይፋ አደረጉ

ታሪኩ ኃይሉ