ሱሰኝነት ልጅነቱን ቢወስድበትም እጅ አልሰጠም፤ ታሪክ ቀያሪው ናቲ ባርበር
Description
ልጅነቱም ሱሰኝነት በብዙ መልኩ እንዳበላሸበት ያስባል፤ ስደትንበማይጨበጥ ተስፋ ድንብር አቋርጦ የሰው ሀገር እንዲናፍቅአድርጎታል፡፡ እድሜው በሀያዎቹ መጀመሪያ ላይ ሆኖ እሱ ግንየቀረውን የሱስ አይነት እና ከኢትዮጵያ እስከ ሱዳን ከዚያምየግብፅና ሊቢያ በርሃን ስቃይ አስመልክቶታል፡፡ ዛሬ ላይበኢትዮጵያ በወንዶች የፀጉር ውበት ቤት ሥራ ላይ ቀዳሚለመሆን የበቃው ወጣት ናትናኤል ተስፋዬ ናቲ ባርበር ሾፕየትናንት ህይወቱን እንዲህ ያስታውሰዋል፡፡
‹‹ሱስ እንደሚታወቀው ከብዙ ሰው ያራርቃል፡፡ ብዙ ነገርህንይገድላል፡፡ ልጅነትህን ይቀማል ልትደብቀውአትችልም ፊትህሰውነትህ፣ባህሪህ በደንብ ያስታውቃል፡፡ ሱስ መውጣት ሲጀምር የሙሉ ሰዓት ሆነና ለብዙ ችግርዳርጎኛል፡፡ ሥራ ላይ አክቲቭአትሆንም ፍላጎትህን አታሳካም፤ የማይጨበጡ ነገሮችንታስባለህ ሃሳብ ብቻ ነውየሚሆነው፡፡››
ከሱሰኝነት ተላቆ ለስኬት የበቃዉ ወጣት
ሱሰኝነት ያመላከተው ቀቢፀ ተስፋም በአንድ ጊዜ ከደሴ ተነስቶጣሊያን መግባትን ነበር፤ ከደሴም ተነስቶ በሱዳን በኩል ይህንን ሃሳብ ለማሳካት መንገድ ጀመረ፤ በማይጨበጥ ተስፋምየተጓዘበት መንገድ ግን ብዙ ችግርና ስቃይ ያለው ነበር፡፡
‹‹በጣም ቀላል አድርጌው አውሮፓ ጣሊያን ብለህ መድረስህንc ነው የምታስበው ስለመንገዱ እኔ መረጃ የለኝም እንዳልኩህ ሱስላይ ስለነበርን ተነሳንና ሄድን የደረሱ ሰዎች ይደውላሉ፤ ቀላልያደርጉብሃል፤ ከሄድኩ በኋላ ግንበጣም ዘግናኝ ነው፡፡››
ለ6 ወራት ያህል በሱዳን ከበረሃ መልስ ቆይታ ያደረገው ወጣትናትናኤል ተስፋየ በካርቱም አስቸጋሪ የጉልበት ስራን ለመስራት ተገደደ፣ ይህ አጋጣሚ ሀገሩን በድጋሜ እንዲመለከት አደረገው፡፡
‹‹ሱዳን 6 ወር የተለያዩ ስራዎችን ለመስራት ሞከርን ከባድ ነውየነበረው፤ ሌሎች ስራዎችን ለመሞከር የተለየሙያአልነበረኝም ከጉልበት ስራ ውጭ፤ ዘይት ማውረድ ስራአገኘሁኝ፤ በጣም ከባድ ነበር፡፡ ያን ቀን ነበርለመመለስያሰብኩት ይህንን መስራት ከቻልኩ ለምን አገር ቤት መስራትአልችልም አልኩ፡፡››
በስደት ዉስጥ ያለን መከራ ለመቀበልን ከቻልን በሀገር በሀገር መስራት ይቀላል
ከስደት ዳግም ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ በሀገር ውስጥ ዝቅ ብሎ ለመስራትማህበረሰቡ የነበረው አመለካከት የተሳሳተ መሆን እንደፈተነውየሚናገረው ናትናኤል ተስፋየ እሱ ግን ተመልሶ በኮንቴነሩ ውስጥየፀጉር ማስተካከሉን ስራ በሀገሩ ጀመረ፡፡
‹‹ስመጣ በጣም ከባድ ነው፡፡ የተሰናበትካቸው ጓደኞች ጣልያንሄደ ብለው ነው የሚጠብቁት እኛ ሀገር ያለውመመለስ ትልቅኪሳራ ነው፡፡ እኔ ግን ያንን አልፈለኩምና ተመልሼ ኮንቴነር ቤትውስጥ የጸጉር ስራ ጀመርኩኝ፡፡››
ከሱስ ጋር በየእለቱ ታግሎ ራሱን ለመለወጥ የተጋው ናትናኤል የፀጉር ስራን ዘመናዊ በማድረግ እና ሙሉ ጊዜውን ሰጥቶበመስራት በአዲስ አበባና ደሴ የናቲ ባርበር ሾፕ ቅርንጫፎችንበመክፈት ሙያውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የራሱን በጎ ድርሻተወጥቷል፡፡
‹‹ቆንጆ የምለውን ዘመናዊ የሆነ ቤት በትክክል የምንፈልገውንከፈትን ብዙ ሰራተኞች አሉት፡፡ ሉሲ ብቻ 17 ሰራተኞችአሉ፤ ትልቅ የሚባለውን የውበት ሳሎን ነው የከፍትነው፤ በአመቱአዲስ አበባም ሌላ የውበት ሳሎንከፈትን አዲስ አበባ ፉክክርአለ እዚህ ሰርተን ስለነበር በቀላሉ ነው ወደ ስራ የገባነው፡፡››
በኮንቴነር የጀመረዉ ስራ ለአለም አቀፉ ካምፖኒ ብራንድ አምባሳደርነት አድርሶታል
ወጣት ናትናኤል ተስፋየ አሁን ላይ 107 ዓመት የጸጉር መቁረጫማሽኖችን ለሚያመርተው ዋህል ለተሰኘው የአሜሪካ ካምፓኒብራንድ አምባሳደር በመሆን እየሰራ ነው፡፡
‹‹ዋህል አለም ላይ ትልቁ የፀጉር ማሽን አምራች ነው፡፡ ይህካምፓኒም አለም ላይ ተቀባይነት ያለው ነው፡፡በየሀገሩአምባሳደሮች አሉት፡፤ ይህ እድል ሲመጣ ባለሙያዎችእንዲገናኙ የተሻለ እውቀትን ለማገኘት አሰባሰበን፤በዚህአጋጣሚም እኛን መረጡን፡፡››
አሁን ላይ ማንኛውንም ስራ የዲጂታል ገበያው እየመራው ነውየሚለው ናትናኤል ተስፋየ በዚህ ተወዳዳሪ በበዛበት ገበያ ውስጥለራስ በቂ ጊዜና ቦታ ሰጥቶ ራስን ማስተዋወቅ ይገባል ይላል፡፡
‹‹አብዝሃኛው ስራ የሚሞተው ባለቤቱ ኩሩ ስለሆነ ነው፡፡ መሄድ ያለበት ቦታ ስለማይሄድ አሁን ላይ ቢዝነስ ድግድነው፡፡ ራስን ማስተዋወቅ አለብህ፤ ሶሻል ሚዲያ ላይ አክቲቭ መሆንአለብህ፤ ይህ ኢትዮጵያ ውስጥአልተለመደም፤፡፡››
ለ33 ወጣቶች የሥራ እድል የፈጠረው ናቲ ባርበር ሾፕ ዛሬለደረሰበት ስኬት የስራ ባልደረቦቹ አስተዋጽዖ የላቀ መሆኑንይናገራል፡፡
‹‹አሁን ላይ በአዲስ አበባና ደሴ 33 ባለሙያዎች አሉን፡፡ ከባለሙያዎቹ ጋር ያለን ግንኙነት በጣም ጥሩ ነው፡፡እኔንምደግፈውኛል፤ ነገሮች የተሳኩት በእነርሱ ድጋፍ ነው፡፡››
የናትናኤል ተስፋየ የስራ ባልደረቦችም ስራውን በመውደዱጊዜውን በሚገባ በመጠቀሙ ዛሬ የተሻለ ተቋም ለመመስረት እናመሪ ለመሆን በቅቷል ይላሉ፡፡
‹‹ናቲን ልጅ ሆኖ ነው የማውቀው፤ በጣም ጎበዝ ነው፤ ነገውንዛሬ የተሻለ ለማድረግ ነው የሚሰራው ለውጡንቀን በቀንእያየነው ነው ብልህ ነው ‹‹ ናቲሻ ለእኔ ወንድም፣ጓደኛ፣አለቃነው ለእኔ በህይወቴ ውስጥ ሥራያስፈልጋል የሚለውን ሃሳብያሳየኝ እሱ ነው፡፡››
ከብዙ ድካምና ጥረት በኋላ ለስኬት የበቃው ናትናኤል ተስፋ የሃላፊነትን በመወጣት በሱስ እና በስደት ያጠፋሁትን ጊዜ ማካካስአለብኝ በማለት በደሴ መቄዶኒያ የአረጋውያን እና የአእምሮህሙማን መርጃ ማዕከል በነፃ አገልግሎት የሚሰጥ ፀጉር ቤትከፍቶ ማህበራዊ ሃላፊነቱን እየተወጣ ነው፡፡
‹‹ደሴ መቄዶኒያ የራሳችን ፀጉር ቤት አለ ማንኛውም ባለሙያበነፃ እንዲሰራ ማቴሪያሎች አሉን፤ ፈቃደኛ የሆነሰው ቢሰራለነፍሱም ለስጋውም ነው፡፡ ፀጉር ቤቱም በነፃ ነውየሚሰራው፡፡››
ሱሰኝነት ያዋርዳል
ሱሰኝነት ያዋርዳል፣ከፍተኛ የሥነ-ልቦና ችግር ያመጣል የሚለውወጣት ከዚህ ጎጂ ልማድ ወጣቶች ራሳቸውን ማራቅ አለባቸውሲል ይመክራል፡፡
‹‹ሱስ ላይ ኖረህ የፈለገ ስራ ቢኖርህ በእያንዳንዱ ወንጀልየምትጠረጠረው አንተ ነህ፤ ወጣት ሆነህ መሳቀቅየለብህም፤ አትከበርም፤ አትናፈቅም፤ እኔ ያየሁት ነገር ነው ይህ ማለት ልክአይደለም፡፡››
በርካታ ፈተናዎችን ተሸግሮ ሱስንም፣ ስደትንም አሸንፎ ለስኬትየበቃው ወጣት ናትናኤል ተስፋየ ዛሬ ላይ የብዙዎች ምሳሌሊሆን ችሏል፡፡
ኢሳያስ ገላው
ታምራት ዲንሳ























