DiscoverDW | Amharic - Newsየአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ የምግብ እርዳታ ለተረጂዎች በትክክል አይደርስም ተባለ
የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ የምግብ እርዳታ ለተረጂዎች በትክክል አይደርስም ተባለ

የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ የምግብ እርዳታ ለተረጂዎች በትክክል አይደርስም ተባለ

Update: 2025-11-22
Share

Description

የምርመራ ቡድኑ በምርመራው ያተኮረባቸው አካባቢዎች



የኮሚሽኑ ምርመራ በተለይ ኢትዮጵያ ን ኬንያንና ሌሎችን ከስሀራ በታች ያሉ የህብረቱ ዕርዳታ ተጠቃሚ አገሮች ላይ ያተኮረ ሲሆን፤ የሚላከው እርዳታ በተለይ በረሀብ ክፉኛ ለተጠቁ ህዝቦችና አካባቢዎች ያለመድረስ ወይም ቅድሚያ ያለመሰጠት ሁኔታ በብዙዎቹ አገሮች የተስተዋለ መሆኑን ገልጿል። ሪፖርቱ ለምሳሌም በኢትዮጵያ (አካባቢዎችን ባይጠቅስም) እ እ እ በ2022 የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተላከ እርዳታ ቅድሚያ ሊሰጠው ለማይገባ አካባቢ የተላከ መሆኑን ጠቅሷል።



ህብረቱ ለምግብ እርዳታ እስካሁን የለገሰው መጠን



የአውሮፓ ህብረት የመንግስታቱ ድርጅትን ረሀብን ለማስወገድና ለሚላኒየም ዘላቂ የልማት ግቦች መሳክት ዋና ለጋሺና እርዳታ አቅራቢ በመሆን የሚጠቀስ ሲሆን፤ እ እ ከ2014 እስከ 2020 17 ቢሊዮን ኢሮ፤ እንደገናም ከ 2021 እስከ 2024 ተጨማሪ 6.2 ቢሊዮን ኢሮ እንደለገሰና ከዚህ ውስጥም 11 ቢሊዮኑ ከስሀራ በታች ላሉ የአፍርካ አገራት የተላከ መሆኑን ሪፖርቱ ጠቅሶ፤ ሆኖም ግን እርዳታው ሙሉ በሙሉ ለተጎጂዎችና እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ደርሷል ማለት እንደማይቻልና በዚህም ምክኒያት በብዙዎቹ አካባቢዎች ረሀብን ለማስወገድና የምዕተ አመቱን የልማት ግቦች ለማሳክት አስቸጋሪ እንደሚሆን አስታውቋል።



የምርምራው ዋና ዋና ግኝቶች





DW የመርመሪ ቡድኑን አባልና የበላይ ሀላፊ ወይዘሮ ቤቲና ጃኮብሰንን ስለ ምርመራው ግኝትና በሪፖርቱ ስለቀረቡ ምክረ ሀሳቦች ወደ ቢሯቸው ሉክዘምበርክ ስልክ በመደወል ጠይቋቸው ነበር። ወይዘሮ ጃኮብሰን የምርመራቸውን ግኝቶች በመዘርዘር ነው ማብራሪያቸው የጀመሩት፤ “ የአውርፓ ህብረት እርምጃዎች ብዙ ግዜ ዋና እርዳታ ፈላጊዎችን ኢላማ እንደማይደርግ አረጋግጠናል። ይህም በዋናነት ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ አካባቢያዎችን መለያ መሰፈርት ባለማበጅቱ ነው። ሁለተኛ ናሙና ፕሮጀክቶቹ በህብረቱና በመንግስታት ፖሊስዎች ላይ የተመሰረቱ እንጂ ህብረቱ በዝርዝር ያያቸውና የመረመራቸው አይደሉም። በተጨማሪም ብዙዎቹ ፖርጀክቶች ህዝቡን ሳያማክሩና ሳያሳትፉ የሚዘጋጁ መሆኑን እንደረሱበት ገልጸዋል።



በእነዚህ በተጠቀሱትና ሌሎች በሪፖርቱ በስፋት በተዘረዘሩ ምክኒያቶች ክህብረቱ የሚላኩ የምግብ እርዳታዎች ለተጠቃሜዎች በወቅቱ የማይደርስባቸው ሁኒታዎች መኖራቸውን ያረጋገጡ መሆናቸውንም ዋና መርማሪዋ ለዲደብሊው በሰጡት ቃለ መጠይቅ አብራርተዋል።፡

ዲደብሊው ከሰሀራ በታች ባሉትና ምርመራቸውን ካካሄዱባቸው አገሮች ችግሩ ጎልቶ የታየባቸውን አገሮች እንዲጠቅሱለትም ጠይቋቸው ነበር። እሳቸው ግን በደፈናው ባጠቃላይ በዓለም ከ295 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ለከፍተኛ የምግብ እጥረት የተጋለጠ መሆኑን ጠቅሰው፤ በተለይ ከስሀራ በታች ያሉ የአፍርካ አገሮች በኮቪድ ወረርሽኝ፣ የአየር ንብረትና ጦርነቶች ምክኒያት ለከፍተኛ ችግር የተጋለጡ መሆኑን ነው የጠቀሱት።





የቀረቡ ምክረ ሀሳቦችና አስተያየቶች



ወይዘሮ ጃኮብሶን ከዲደብሊው ጋር በነበራቸው አጭር ቆይታ መደረግ ይኖርባቸዋል በማለት በሪፖርቱ የጠቀሱትን ምክረ ሀስቦችንም ዘርዝረዋል፤ “ በመጀመሪያ ኮሚሽኑ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ተረጂ ወገኖችን የመለያ መስፈት ሊያበጅና በስራ ላይ ሊያውል ይገባዋል። የቁጥጥር ስልቶችንም ሊዘረጋና በስራ ላይ ሊያውል ይገባል፤ እርዳታዎቹ ከሰው ኋይል እድገትና ከሰላም ጋር ያላቸውን ቁርኝትና ዘላቂነታቸውንም ማረጋገጥ ይኖርበታል” በማለት ኮሚሽኑ እነዚህንና ሌሎቹንም ምክረ ሀሳቦች እንደተቀበለና እሳቸው ያሉበት የቁጥጥር ኮሚቴም የምክረ ሀስቦቹን ተግባራዊነት የሚከታተል መሆኑን አስታውቀዋል።

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ የምግብ እርዳታ ለተረጂዎች በትክክል አይደርስም ተባለ

የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ የምግብ እርዳታ ለተረጂዎች በትክክል አይደርስም ተባለ

ገበያው ንጉሤ