DiscoverDW | Amharic - Newsየደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ዓለም አቀፍ ችግሮችን ለመፍታት በጋራ መተባበር እንደሚያስፈልግ አሳስሰቡ
የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ  ዓለም አቀፍ ችግሮችን ለመፍታት በጋራ መተባበር እንደሚያስፈልግ አሳስሰቡ

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ዓለም አቀፍ ችግሮችን ለመፍታት በጋራ መተባበር እንደሚያስፈልግ አሳስሰቡ

Update: 2025-11-22
Share

Description

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ዓለም አቀፍ ችግሮችን ለመፍታት በጋራ መተባበር እንደሚያስፈልግ አሳስሰቡ። ራማፎሳ ይህንን ያሉት ዛሬ በደቡብ አፍሪካ አስተናጋጅነት መካሄድ የጀመረውን የቡድን 20 ጉባኤ መክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ ነው። ራማፎሳ አክለውም በበለጸጉ እና በድሃ አገሮች መካከል ያለው ልዩነት ለዘለቄታማ እድገት እንቅፋት ከሆኑት ነገሮች አንዱ እንደሆነ በመግለፅ አውግዘዋል። አለመመጣጠኑ "ኢ-ፍትሃዊ እና ተቀባይነት የሌለው" ነውም ብለዋል።



በአፍሪቃ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው እስከ ነገ የሚዘልቅ ሲሆን በኢንዱስትሪ የበለጸጉ እና በመበልፀግ ላይ ያሉ በኢኮኖሚዎች መሪ የሆኑት የቡድን 20 ጉባኤ አባላት የሚሳተፉበት ይሆናል። ይሁንና በጉባኤው ላይ የዩናይትድ ስቴትስ፣ ቻይና እና የሩሲያው ፕሬዚዳንት አልተገኙም።

በጉባኤው ላይ የተገኙት የጀርመኑ መራሔ መንግሥት ፍሪድሪሽ ሜርስ "ለጠንካራ አጋርነት፣ ለቀውስ ዲፕሎማሲ እና በሕግ እና በአስተማማኝነት ላይ ለተመሠረተ ሥርዓት በአንድነት እንቆማለን" ሲሉ ዛሬ ቅዳሜ ጠዋት በኤክስ ማህበራዊ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል። ሜርስ በጉባኤው ላይ ባሰሙት ንግግር ደግሞ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የምታካሂደውን ወረራ ታቁም ሲሉ አሳስበዋል።



ዶናልድ ትራምፕ በጉባኤው ባለመሳተፋቸው እንደማይቆጩ የተናገሩት የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮ የእሳቸው አለመገኘት «ሊያግደን አይገባም» ብለዋል። "ግዴታችን በቦታው መገኘት፣ መሳተፍ እና አብረን መስራት ነው ምክንያቱም ብዙ ተግዳሮቶች አሉብን።" ብለዋል ማክሮ። ያም ሆኖ በትናንትናው ዕለት የደቡብ አፍሪቃው ፕሬዚዳንት ሲርል ራማፎዛን ዩናይትድ ስቴትስ በG20 ስብሰባ እንደምትገኝ አሳውቀው ነበር። ራማፎሳ ዩናይትድ ስቴትስ ጆሃንስበርግ በሚደረገው የቡድን 20 ስብሰባ ላይ ለመገኘት በትራምፕ አስተዳደር “የአስተሳሰብ ለውጥ” መጥቷል ማለታቸውም ተዘግቦ ነበር።



የዋሽንግተንና የደቡብ አፍሪቃ ግንኙነት በተለያዩ ምክንያቶች ሻክሯል። ዩናይትድ ስቴትስ ባለፈው የካቲት በዩ ኤስ ኤ አይ ዲ በኩል የሚደረጉ ርዳታዎችን ቀንሳለች። ደቡብ አፍሪቃ ላይም ከፍተኛ ታሪፍ ጥላባታለች። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያለአንዳች ተጨባጭ መረጃ በደቡብ አፍሪቃ በነጭ ደቡብ አፍሪቃውያን ላይ ያነጣጠረ «የዘር ማጥፋት» ይካሄዳል ብለው ደምድመዋል። የደቡብ አፍሪቃ መንግሥት ይህን ሐሰት ሲል አስተባብሏል።



ደቡብ አፍሪካ የጉባኤ አስተናጋጅ እንደመሆኗ "አንድነት፣ እኩልነት እና ዘላቂነት" የሚሉትን ዋና ዋና ጉዳዮች በአጀንዳነት አስቀምጣለች።



አርታኢ ፀሀይ ጫኔ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ  ዓለም አቀፍ ችግሮችን ለመፍታት በጋራ መተባበር እንደሚያስፈልግ አሳስሰቡ

የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ዓለም አቀፍ ችግሮችን ለመፍታት በጋራ መተባበር እንደሚያስፈልግ አሳስሰቡ

ልደት አበበ/ Lidet Abebe