DiscoverDW | Amharic - Newsየማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ አጠቃቀሞች ከማኅበረሰቡ እሴት ጋር ሲነጻጸር
የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ አጠቃቀሞች ከማኅበረሰቡ እሴት ጋር ሲነጻጸር

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ አጠቃቀሞች ከማኅበረሰቡ እሴት ጋር ሲነጻጸር

Update: 2025-12-12
Share

Description

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች ላይ ከማኅበረሰቡ ባህልና ወግ ያፈነገጡ ተግበራትን ፈጽመዋል ብሎ የጠረጠራቸውን በስፋት በቁጥጥር ስር እያዋለ እንደሚገኝ እያሳወቀ ነው።



የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች ትውልድን ለማነጽ ከመጠቀም ይልቅ ከሀገሪቱ ባህል፣ ወግና ሥነ-ምግባር የወጡ አላስፈላጊ ድርጊቶችን በሚፈጽሙ አካላት ላይ የሚወሰደው ሕጋዊ ርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ፍንጭ የሰጠው ሰሞነኛው የፌዴራል ፖሊስ መግለጫ መሰል ድርጊቶችን በመፈጸም የጠረጠራቸውን በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ስር እያዋላቸው እንደሚገኝ ዐሳውቋል።



ሰሞነኛው ተደጋጋሚ የፖሊስ መግለጫው "በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው አስነዋሪ አለባበስ ለብሰው በአደባባይ የታዩት አምስት ተጠርጣሪዎችን ጨምሮ ዕውቅና እና ገንዘብ ለማግኘት ብቻ በማሰብ ሚዲያዎችን ኃላፊነት በጎደለው አኳሃን በትውልዱ ላይ ርካሽ ባህልን ለመጫን ተንቀሳቅሰዋል” ያሏቸውንም በርካቶች በቁጥጥር ስር አውሎ በምርመራ እያጣራ እንደሆነ ጠቁሟልም፡፡



በማኅበራዊ መዲያ የተሰራጩ ይዘቶች



በቅርቡ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ይዘት ተብለው የሚቀርቡት ወጣቶችን ከፈጠራ፣ ከትምህርት እና ከመልካም ስነምግባር ጋር የሚያቃቅሩ እየሆኑ ነው በማለት አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ ሕስ እና ትችት በማቅረብ የሚታወቁት የሕግ ባለሙያ ሰመረ ከሳዬ፤ ድርጊቶቹ ተቆጣጣሪ የጠፋው እስኪመስል ድረስ በመጠን ከፍ እያለ መጥቷል ብለዋል፡፡ "ድርጊቶቹ የማህበረሰቡን እሴት የሚነኩ በርካታ ይዘቶች አሉት” ያው ሰመረ፤ በማህበረሰቡም ዘንድ እንዲህ ያለ ከመስመር የሚወጡ ልምዶችን ማስተዋሉንም አስረድተዋል፡፡ ወጣቶች በብዛት የተጋራውን ይዘት ብቻ ስለሆነው የሚመለከቱት ከዚያ ከማህበረሰቡ እሴት መስመር ስወጣ እምብዛም ትኩረት ስሰጡት አይስተዋልም ብለዋል፡፡ "ይዘትና ጥቅሙን ከመመርመር ይልቅ ይህን የተከታዮቹን ብዛት ብቻ ተከትሎ ሰሞኑን በርካቶችን የመሸለም ጉዳይም የዚሁ ነጸብራቅ ነው” ያሉት ባለሙያው፤ ድርጊቱንም "ተቆጪ የጠፋበት እብደት” ሲል ገልጾታል፡፡



የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ይዘት ከሕግ አንጻር ሲቃኝ



ተሰብሯል ለተባለው የማኅበረሰብ እሴት የሕግ ክፍተት ወይስ የማኅበረሰብ ኃላፊነት መላላት የታየበት ይሆን በሚል የተጠየቁት የሕግ ባለሙያው፤ "የሕግ ዘርፉ ከመስመር ያለፉትን ድርጊቶች ከመቅጣት ያለፈ የሚያደርገው የለም” በማለት ማህበረሰቡ ግን እንደ ማኅበረሰብ ከመስመር የሚወጡ ወጣቶችንም ሆነ ይዘቶች ለማረም ያደረጉት ነገር አናሳ ነው በማለት አስተያየታቸውን ሰትተዋል፡፡



የኢትዮጵያ ሕግ መሰል ተግባራትን የሚቀጣበት ግልጽ ድንጋጌዎች ያለው መሆኑንም አክለው የጠቆሙት ባለሙያው፤ አሁን እየተወሰደ ነው ያሉት የፖሊስ ርምጃዎች ከሰዎች ነጻነት ጋር መጋጨት እንደሌለበትም በአስተያየታቸው አብራርተዋል፡፡ "ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ የሆኑ ድርጊቶችን በአደባባይ ማድረግ ወንጀል መሆኑ በህግ በግልጽ ተደንግጓልም” ያሉት ሰመረ፤ ከሰሞኑ በፖሊስ የተያዙ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ጉዳይን ትርጓመ ሰጥቶ በምን አግባብ መታለፍ አለበት የሚለውን ውሳኔ መስጠት ያለበት ፍርድ ቤት ነው ብለዋልም፡፡ ይህ ድርጊት ከመብት ጉዳዮች ጋር መጋጨትም እንደማይኖርበት በአስተያየታቸው አንስተዋል፡፡



ሥዩም ጌቱ



ማንተጋፍቶት ስለሺ



ታምራት ዲንሳ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ አጠቃቀሞች ከማኅበረሰቡ እሴት ጋር ሲነጻጸር

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ አጠቃቀሞች ከማኅበረሰቡ እሴት ጋር ሲነጻጸር

ሥዩም ጌቱ