DiscoverDW | Amharic - Newsየአጀንዳ ማሰባሰብ በአማራ ክልል
የአጀንዳ ማሰባሰብ በአማራ ክልል

የአጀንዳ ማሰባሰብ በአማራ ክልል

Update: 2025-04-04
Share

Description

የአጀንዳ ማሰባሰብ በአማራ ክልል ነገ ይጀመራል፡



ከነገ መጋቢት 27/2017 ዓ ም ጀምሮ በአማራ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ የሚሳትፉ 6000 ያክል ወኪሎች ባሕር ዳር መግባታቸውን የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ፣ በአማራ ክልል ከመንግሥት ጋር እየተዋጉ ያሉ ኃይሎች በአጋራዊ ምክክሩ እንዲሳተፉ ኮሚሽኑ ጠሪ አቅርቧል፡፡



ስድስት ሺህ ተወካዮች ባሕር ዳር ገብተዋል



የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከነገ ጀምሮ በአማራ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ ህዝባዊ መድረክ ማዘጋጀቱን አስታውቋል፣ በክልሉ ከሚገኙ 267 ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች መካከለ ከ263ቱ የተመረጡ 6000 ተወካዮች ባሕር ዳር መግባታቸውን የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ መላኩ ወ/ማሪያም ዛሬ ባሕርዳር ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አመልክተዋል፡፡



ከህብረተሰብ ክፍሎች፣ ከመንግሥት፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከተፀኖ ፈታሪ ግለሰቦችና ከማህበራትና ተቋማት የተውጣቱ 6 ሺህ ተሳታፊዎች ባህርዳር የገቡ ሲሆን ከወረዳዎች የተውጣቱት 2ሺህ 500 ተወካዮች በቅጣይ 4 ቀናት በአጀንዳ ሀሳቦቻቸው ላይ ሠፊ ውይይት ካደረጉ በኋላ ክልላዊና አገራዊ ፋይዳ ያላቸውን አጀንዳዎች እንደሚያጠናቅሩ ነው ኮሚሽነር መላኩ ያስረዱት፡፡



የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን የኦሮሚያ አጀንዳን አሰባሰብ ማጠናቀቁ



ሁሉም ኢትዮጵያዊ በምክክሩ እንዲሳተፍ ሁኔታዎች ተመቻችተዋል



ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአገራዊ የምክክር ሂደቱ እንዲሳተፍ ሁኔታዎች መመቻቸታቸውን ደግሞ ሌላው ኮሚሽነር ዶ/ር ዮናስ አዳዬ ተናግረዋል፡፡ ዜጎች በውክልና፣ በማህበራዊ ሚዲያዎችና በዲፕሎማቶች አማካኝነት ምክክሩን የሚሳተፉ እንደሚሆኑ ነው ያስረዱት፡፡



የፋኖ ታጣቂዎች በአገራዊ ምክክሩ እንዲሳተፉ በርካታ ጥረቶች ሲካሄዱ እንደነበር የተናገሩት ዶ/ር ዮናስ አዳዬ ሆኖም በይፋ የተሰጠ ምላሽ እንደሌለ ጠቁመው አሁንም ታጣቂዎቹ በምክክር መድረኩ ለመሳተፍ ፈቃደኛ ከሆኑ የኮሚሽኑ በር ክፍት ነው ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡



“ከፋኖ ታጣቂዎች እስካሁን ይፋዊ ምላሽ አላገኘንም” አገራዊ ምክክር ኮሚሽን



በ4ቱም ማዕዘን ያሉ ታጣቂዎች በቡድን ቀጥተኛ የሆነ ምላሽ አልተሰጡንም የሚሉት ዶ/ር ዮናስ “አብረን እንነጋገር” የሚል ይፋዊ ምላሽ እንዳላገኙ ግን አሁንም “መልካም ምላሽ እየጠበቅን ነው” ነው ያሉት፡፡ ታጣቂዎቹ ተወካዮቻቸውን አሁንም ወደ ምክክር መድረኩ መላክ ከቻሉ እንደሚቀበሏቸው ዶ/ር ዮናስ አስረድተዋል፡፡



የኮሚሽኑን ገለልትኛነት በተመለከት ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ኮሚሽነሩ አቶ መላኩ ወ/ማሪያም “የማንም ቅጥያ አይደለንም” ብለዋል፡፡የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ አስቸኳይ ሀገራዊ ጥሪ



አጋራዊ የምክክር ኮሚሽን ነፃና ገለልተኛ ስለመሆኑ



“...ከፖለቲካ ወገንተኝነት አኳያ ተቋሙ ከማንኛውም የመንግሥት ተፅዕኖ ነፃ የሆነ ተቋም ነው፣ አፌን ሞልቸ ነው ይህን የምናገረው፣ የማንንም አጀንዳ ተሸክመን የምንሄድ ሠዎች አይደለንም፣ የማንም “ፈረሶች” አይደለንም፣ ለኢትዮጵያ ህዝብና ለእውነት ነው የምንወግነው፣ ይች አገር ከገባችበት ውጥንቅጥ ወጥታ መጪው ትውልድ ብሩህ ተስፋ እንዲያይ ነው የምንሰራው፣ የማንም ተቀጥላዎች አይደለንም” ብለዋል፡፡



በአማራ ክልል አጀንዳ የማሰባሰብና በብሔራዊ ደረጃ የሚሳተፉ ወኪሎችን የመምረጥ ሂደት ከነገ መጋቢት 27/2017 እስከ ሚያዝያ 4/2017 ዓ ም እንደሚቀጥል በመግለጫው ተመልክቷል፡፡



የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተሰጠው የሥራው ጊዜ የተጠናቀቀ ቢሆንም ያላለቁ ቀሪ ሥራዎች በመኖራቸው ለቀጣይ አንድ ዓመት የቆይታ ጊዜው መራዘሙ ይታወሳል፡፡



ዓለምነው መኮንን



አዜብ ታደሰ



ሸዋዬ ለገሠ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የአጀንዳ ማሰባሰብ በአማራ ክልል

የአጀንዳ ማሰባሰብ በአማራ ክልል

ዓለምነው መኮንን