ኒኮላ ሳርኮዚ ፤ በፈረንሳይ ታሪክ ዘብጥያ የወረዱ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት
Update: 2025-10-22
Description
ፈረንሳይን ከጎርጎሮሳዊው 2007 እስከ 2012 ዓ.ም. የመሩት የቀድሞ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንትኒኮላ ሳርኮዚስልጣን ከመያዛቸው በፊት ለምርጫ ዘመቻ ከሊቢያ ገንዘብ ለማሰባሰብ በመመሳጠር ተወንጅለው ትናንት እስር ቤት ገብተዋል። በተፈረደባቸው የ5 ዓመት የእስር ቆይታ በሙሉ ከታሰሩበት ክፍል አጠገብ በቋሚነት ሁለት ፖሊሶች እንደሚጠብቋቸው የፈረንሳይ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ላውረን ኑኔስ ዛሬ ለአንድ የፈረንሳይ ራድዮ ተናግረዋል። ሳራኮዚ ፕሬዝዳንት የነበሩ በመሆናቸው ጥበቃ የማግኘት መብት እንዳላቸው የተናገሩት ሚኒስትሩ ዛቻም ስለሚሰነዘርባቸው በተያዙበት ጥበቃ ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል።ክሱ ፖለቲካዊ ተነሳሽነት ያለው ነው ሲሉ የሚሟገቱት ሳርኮዚ ጥፋተኛ አይደለሁም በማለት ሲያስተባብሉ ቆይተዋል። የሳርኮዚ የእስር ጊዜ እንዲያጥር ይግባኝ ያሉት ጠበቆቻቸው በአንድ ወር ውስጥ ሊፈቱ ይችላሉ ብለው ተስፋ ያደርጋሉ።
ስለ ሳርኮዚ እስር ፣ይግባኝ እና ወደፊት ስለሚጠበቀው፣የፓሪስዋን ዘጋቢያችንን ሃይማኖት ጥሩነህን በስልክ አነጋግረናል።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ
Comments
In Channel