በአማራ ክልል ለአመታት ተቋርጦ የነበረዉ የመምህራን ዝዉዉር ሊጀመር ነዉ
Description
መምህር ተስፋየ አየለ ኢትዮጵያውስጥ በመምህርነት ሙያ የ22 ዓመት አገልግሎት እንዳላቸው ይገልፃሉ፡፡ በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን የሚያስተምሩት መምህር ያለፉትን 3 ዓመታቶች የመምህራን የሥራ ቦታ ዝውውር በመታገዱ ምክንያት ከባለቤታቸው እና ልጆቻቸው ጋር ተለያይተው መቆየታቸውን ይናገራሉ፡፡
‹‹የእኔ ደግሞ ይለያል ምክንያቱም 2015 ነው ዝውውሩ የቆመው ከባለቤቴ እና ከልጆቼ ጋር ተለያይቼ ነው ለ3 ዓመታት የኖርኩት የ22 ዓመት የሥራ ልምድ አለኝ፡፡ አንጋፋ መምህር ነኝ ዘንድሮ ፈጣሪ ካለ እንገናኛለን፡፡›.
ለሦስት አመታት ተቋርጦ የነበረዉ የመምህራን ዝዉዉር ሊጀመር ነዉ
ሌላው ለ10 ዓመታት የመምህራን ዝውውር ጥያቄ የነበራቸው መምህር ግሩም መኮንንም በተመሳሳይ ለአመታትየመምህራንዝውውር በመቋረጡ ከቤተሰቦቻቸው መገናኘት መቸገራቸውን ያነሳሉ፡፡
‹‹እኔን ምሳሌ ልበል እና ባልቴት እናት ናት ያለችኝ ጧሪ የላትም እንደዛ ያላቸው አሉ፡፡ ከቤተሰብ የተለያዩ 10 ዓመት ሆኖኛል ደሴም፣ ተሁለደሬም እሞላለሁ ሁልጊዜ የመምህራን ህይወትእኮ ትልቁ ነገር ዝውውር ነው፡፡››
ባለፉት 3 ዓመታት በክልሉ ተፈጥሮ በቆየው የፀጥታ ችግር ምክንያት የመምህራን ዝውውር ለማካሄድ አስቸጋሪ መሆኑን የሚገልፁት የደቡብ ወሎ ዞን ትምህርት መመሪያ ኃላፊ አቶ አለምነው መኮነን በሰላም ቀጠናም ሆነ የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ያሉ መምህራን ዝውውሩን አጥብቀው ሲሹት ነበር ይላሉ፡፡
‹‹በሰላም ቀጠና ያለውም ፀጥታ ችግር ውስጥ ያለውም ሁለቱም ያነሳሉ ጥያቄውን ሰላም ቀጠናውም ወደ ተሻለለ መሄድ ፤ የፀጥታ ችግር ያለበትም ወደ ሰላም ቀጠና ለመምጣት ይፈልጋል፤ እና መዘጋቱ ትልቅ እንቅፋትሆኖ ቆይቷል፡፡ ጀማሪመምህራን ከተማ ይቀጠራሉ፤ ሰው ጡረታ ሲወጣ ትምህርትማ ቋረጥ ስለማይገባ በጊዜያዊነት ትቀጥራለህ፤ አገልግሎትያለው፤ ገጠር እያለ በአገልግሎቱ መጠቀም ሲገባው፡፡››
በአማራ ክልል ያለው የፀጥታ ችግር መምህራንን ከቦታ ቦታአዛውሮ ለማሰራት አመች አልነበረም ያለው የክልሉ ትምህርት ቢሮ መምህራን ከቦታ ቦታ የመዘዋወር መብታቸው መገደቡ እና ከፍተኛ የሆነ የመልካም አስተዳደር ችግር መፍጠሩን አቶ ደምስ እንድሪስ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ሃላፊ ይገልፃሉ፡፡
‹‹ለ3 ዓመታት ሲቋረጥ መምህራን ለከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ችግር ተጋልጠዋል፡፡ ምክንያቱም ከቦታ ቦታመዛወርመብታቸው፤ በአገልግሎታቸው መሰረት ተደርጎ መዛወር አለባቸው፡፡ ነገር ግን በዚህ የፀጥታ ችግር ቢዛወሩ ከቦታ ቦታሲንቀሳቀሱ ጉዳት ይደርስባቸዋል፡፡ በዚህም ምክንያትተቋርጧል፡፡ በዚህ ዓመት ግንእንደምንም ብለን ብንሰራው ጥሩ ነው ብለን ተወያይተን ወሰንን፡፡››
በክልሉ ያለዉ የፀጥታ ችግር ለመምህራን ዝዉዉር መቋረጥ ምክንያትነት ነዉ መባሉ
በያዝነው የትምህርት ዘመን ከጥር 10/2018 ዓ/ም ጀምሮ መምህራን የዝውውር ፍላጎታቸውን በሚያስተምሩበት ትምህርት ቤት ይሞላሉ ያለው የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሁን ላይ በፀጥታችግር ምክንያት የመማር ማስተማር ተግባሩ የተቋረጠባቸውትምህርት ቤት ውስጥ የሚያስተምሩ መምህራን የዝውውሩ አካልይሆናሉ ተብሏል፡፡
‹‹ትምህርት ቤት ላይ ሆኖ ስለሆነ የሚሞላው ትምህርትቤታቸው ዝግ የሆኑ አካባቢዎች ተከታታይ የሙያማሻሻያመርሃ ግብር መስራት አስገዳጅ ማድረግ አስፈላጊ አይደለም፡፡ ከአስገዳጅነት ይውጣ ብለን ወስነናል፡፡ አሁን በፀጥታ ችግርምክንያት ያልተከፈቱ ትምህርት ቤቶች ስላሉ ይህንን ማሻሻል ያስፈልጋል፡፡ ትምህርት ቤታቸው ከተዘጋ ወረዳ ላይ ሆነው መሙላት ይችላሉ ። በትምህርት ቤቱ ማህተም ስለሆነ የሚረጋገጠው፡፡››
ዝውውሩም ከክልል ጀምሮ እስከ ወረዳ እንደሚቀጥል ያወሱትአቶ ደምስ እንድሪስ ጥራትና ተጠያቂነት ያለው ዝውውር መስራት የመምህራንን ጥያቄ በተገቢው መንገድ ምላሽ ይሰጣል ብለዋል፡፡
ኢሳያስ ገላው
ታምራት ዲንሳ
ሸዋዬ ለገሰ























