DiscoverDW | Amharic - Newsየቀጠለው የሩስያ ዩክሬን ጦርነት እና አዲሱ የሰላም ሐሳብ
የቀጠለው የሩስያ ዩክሬን ጦርነት እና አዲሱ የሰላም ሐሳብ

የቀጠለው የሩስያ ዩክሬን ጦርነት እና አዲሱ የሰላም ሐሳብ

Update: 2025-12-16
Share

Description

አመቱን ሙሉ ዋና የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ የዘለቀው የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት

አመቱን ሙሉ ያውሮፓ ህብረት ዋና አጀንዳና ችግር ሆኖ የቆየው የየዩክሬን ጉዳይ በዚህ ሳምንትም የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት አምባሳደሮች፣ ሚኒስትሮችና መሪዎች ስብሰባዎች ዋና አጀንዳ ሆኖ እንደቀጠለ ሲሆን፤ በሳምንቱ ማብቂያ ላይ በሚደረገው ያመቱ መጨረሻ የመሪዎች የሁለት ቀን ጉባኤ ትኩረትም ይኸው የሩሲያና የዩክሬን ጦርነትና የቀረቡት የሰላም ዕቅዶች እንደሆኑ ታውቁል።



በብራስልስና በርሊን የተካሄዱ ስብሰባዎች ትኩረትና ውጤት



በትናንትናው እለት እዚህ ብራስልስ የህብረቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፤ በበርሊን ደግሞ የዩክሬን ፕሬዝዳንትና የአሜሪካ መልዕክተኖች ከተወሰኑ ግን ከዋናዎቹ የአውሮፓ መሪዎች ጋር መክረዋል። የበራስልሱ ስብሰባ ዩክሬን ጠንካራ ተደራዳሪ ልትሆን በምትችልበት የወታደራዊና የፋይናንስ እርዳታ ላይ ያተኮረ ሲሆን፤ በበርሊኑ ስብሰባ ለመጀመሪያ ግዜ አሚሪካ ዩክሬንና አውሮፓ በጋራ የሰላም ዕቅድ ላይ እንደተስማሙ ተገልጿል። በአሜሪካ የተደገፈ የአውሮፓ የሰላም አስከባሪ ሀይል በዩክሬን ሊሰፍር እንደሚችል በአሚሪካ ተደራዳሪዎች፤ ዩክሬንና ያውሮፓ መሪዎች ከስምምነት የተደረሰ መሆኑን ያስተናጋጇ ጀርመን፤ የብርታኒያ፤ ፈርንሳይና ሌሎች ተሳታፊዎችና የህብረቱ መሪዎች በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።



ከበርሊን የወጣው መግለጫ ይዘት



በመግለጫው አውሮፓና አሜሪካ ጭምር ዩክሬን እስከ 800 ሺ ያህል ወታደራዊ ሀይል ለመገንባት የሚያስችል ድጋፍ እንደሚያደርጉ፤ አውሮፓና አሜርካ ለዩክሬን የድህረ ሰላም ስምምነት ዋስትና ለመስጠት እንደሚሰሩና የሰላም ስምምነቱን ተግባራዊነት በመቆጣጠር በኩል አሚሪካ እንድትሳተፍ የተስማሙ መሆኑ ተገልጿል።

ሆኖም ግን ሩሲያ ዩክሬን ልትለቅ በጠየቀችው ግዛት ላይ ብዙ የተባለ የለም ። ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ይህ ጉዳይ አስቸጋሪ ግን ገና ያልተፈታ መሆኑን በመግለጽ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ከሩሲያ ጋር ከፍተኛ ልዩነት ያላቸው መሆኑን ግልጽ አድርገዋል።



የብራስልሱ የሚኒስትሮች ስብሰባ ውጤት



በብራስልስ የተካሄደው የ27ቱ የህብረቱ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባም ምንም እንኳ መካከለኛ ምስራቅን ጨምሮ ሌሎች በርክታ አጀንዳዎች እንደነበሩት ቢታወቅም፤ በጥልቀት የተወያየው ግን የውጭ ጉዳይ ሀላፊ ወይዘሮ ካይ ካላስ እንደገለጹት ሩሲያ በዩክሬን ላይ በከፍተችው ጦርንትና ወረራ ላይ ነበር። የውጭ ጉዳይ ሀላፊ ካያ ካላስ ከስብሰባው በኋላ በሰጡት መግለጫ፤ በህብረቱ በኩል በሩሲያና ዩክሬን ጦርነት ላይ የሚደረገው ውይይት ግቦች እንዳሉት ነው የገለጹት፤ “በውይይታችን ሁልግዜ ቅድሚያ የምንሰጣቸው ሁለት ግቦች አሉ፤ በሩሲያ ላይ ግፊትና ጫና ማሳደር ለዩክሬን የሚሰጠውን እርዳታ አጠናክሮ መቀጠል”፤ በማለት አውሮፓ በዚህ አመት ብቻ 27 ቢሊዮን ኢሮ የለገሰ መሆኑን አስታውቀዋል።



በዚሁ ስብሰባ በሩሲያና ከሩሲያ ጋር በሚሰሩ ደርጅቶችና ለሩሲያ ይሰራሉ በተባሉ ተቋማትና ግለሰቦች ጭምር ተጨማሪ የማዕቀብ ውሳኒዎች የተላለፉ መሆኑን ወይዘሮ ካላስ አክለው አስታውቀዋል።

የውጭ ጉዳይ ሀላፊዎዋ ዩክሬን በድርድሩ ጠንካራ ሆና እንድትቀርብ ለማድረግ የመከላክያ ሀይሏን ማጠናከር ወሳኝ ቢሆንም፤ ዋስትና ግን የሚያስፈልጋት መሆኑንን ሚኒስትሮቹ እንዳመኑበትም ገልጸዋል “ሚኒስትሮቹ ለማንኛውም የሰላም ስምምነት መከበርና መጠበቅ ዋስትና የሚያስፈልገው መሆኑን አምነውበታል› ዩክሬን የኔቶ አባልነት ጥያቄዋን እንድትተው ግፊት እየተደረገባት በመሆኑ ከሩሲያ ዳግም ወረራ የሚከላከልላት ዋስትና ያስፈልጋታል”፤ በማለት ህብረቱ የዩክሬንን ወታደሮችን በማሰልጠንና የመካላከያ እንዱስትሪያዋን እንድታስፋፋ የበኩሉን እንደሚያደግ ገልጸዋል።



በኮሚሽኑ የዩክሬን የእርዳታ ዕቅድ ላይ የተነሱ ጥያቄዎችና ቀጣዮቹ የህብረቱ ጉባኤ አጀንዳዎች



በሌላ በኩል ዩክሬን ከመቼውም ግዚ ይብልጥ የገንዘብና ወታደራዊ ቆሳቁስ የሚያስፈልጋት ቢሆንም ድጋፍና እርዳታው ግን በሚፍለገው መጠን እየተገኘ አለመሆኑ አሳስቢ እንደሆነ ነው ተደጋግሞ የሚገለጸውና የሚሰማው። ኮሚሽኑ ይህን ችግር ለማቃለል በአውሮፓ ባንኮችታግዶ የሚገኘውን የሩሲያ ንብረት ለመጠቀም ያቀረበውን ዕቅድ ቤልጅየም በሀላፊነትና ባለዕዳነት የሚያስጠይቃት መሆኑን በመግለጽ እንደተቃወመችው የሚታወቅ ሲሆን፤ ለሎች ጣሊያንን የመሳሰሉ አገሮችም የቤልጀየምን ተቃውሞና ጥያቄ እንድሚጋሩ እየገለጹ በመሆኑ፤ የኮሚሽኑ የዩክሬን የእርዳታ እቅድ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል እየተባለ ነው። ሁሉም ከዩክሬን ጋር የተያያዙ አጀንዳዎች፤ የሰላም ዕቅዱ፣ የሩሲያን ገንዘብ የመጠቀም ዕቅድና በአሜሪካ የደህንነትስታሬቴጅ ሰነድ ላይ ጥያቄ ውስጥ የገባው የትራንስ አትላንቲክ ግንኑነት በሙሉ በሚቀጥሉት ሀሙስና አርብ በሚካሄደው የመሪዎች ጉባኤ በዋናነት የሚቀርቡ አጀንዳዎች ናቸው። በዚህም ምክኒያት ይህ ጉባኤ የአመቱ ወሳኝ ጉባኤ ሆኖ እየተጠበቀ ነው።

ገበያው ንጉሴ

ታምራት ዲንሳ

ሸዋዬ ለገሰ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የቀጠለው የሩስያ ዩክሬን ጦርነት እና አዲሱ የሰላም ሐሳብ

የቀጠለው የሩስያ ዩክሬን ጦርነት እና አዲሱ የሰላም ሐሳብ

ገበያው ንጉሤ