DiscoverDW | Amharic - Newsከኦፌኮ አመራር አባልነት ወደ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ መስመር - ደስታ ዲንቃ
ከኦፌኮ አመራር አባልነት ወደ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ መስመር - ደስታ ዲንቃ

ከኦፌኮ አመራር አባልነት ወደ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ መስመር - ደስታ ዲንቃ

Update: 2025-12-16
Share

Description

ከኦፌኮ በመውጣት አዲስ መንገድ በማማተር ላይ ያሉ ፖለቲከኛ



በኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) በከፍተኛ አመራርነት ለዓመታት ያገለገሉ ፖለቲከኛ ደስታ ዲንቃ ከፓርቲው መውጣታቸውን አረጋገጡ፡፡



ፖለቲከኛው ከሌሎች የትግል አጋሮቻቸው ጋር በመሆን በሌላ የፖለቲካ ድርጅት ለመምጣት መንገድ ስለመጀመራቸውም ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡



የፖለቲካ አመለካከት ልዩነት..



ከአንጋፋውየኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረንስ (ኦፌኮ)የመውጣት ውሳኔያቸው እራሳቸውን ከፖለቲካው ዓለም የማራቅ ፍላጎት ተደርጎ እንዳይወሰድ የገለጹት ፖለቲከኛ ደስታ ዲንቃ፤ ለዓመታት በትላልቅ ኃላፊነቶች ካገለገሉት የፖለቲካ ድርጅት ለመውጣት የገፋቸው ዋናው ምክንያት በእርሳቸው እና በኦፌኮ መካከል ያለው የፖለቲካ አመለካከት አለመግባባት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡



“የእኔ የፖለቲካ አመለካከትና የፖለቲካ አስተዳደር ከሌሎች የተለየ እንደሆነ እረዳለሁ” ያሉት ፖለቲከኛ ደስታ ባሁን ወቅት በአገሪቱ “ከጫፍ ጫፍ የሚስተዋሉ አለመረጋጋቶች” እንቅልፍ እንደሚነሱአቸው በመግለጽ ከሳቸው ጋር ተመሳሳይ ሃሳብ ካላቸው ዜጎች ጋር በመሆን በተለየ አቀራረብና አያያዝ በአዲስ የፖለቲካ ድርጅት ለመምጣት ማቀዳቸውንም አስረድተዋል፡፡



የፖለቲካው ውጣ ውረድ



በኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረንስ ውስጥ ከሌሎች ጓዶቻቸው ጋር በመሆን በርካታ የፖለቲካ ስራዎችን መስራታቸውን የሚያምኑት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ምሩቅና የቀድሞ ጠበቃና የህግ ባለሙያ የአሁኑ ፖለቲከኛ አቶ ደስታ ዲንቃ፤ በፖለቲካው ህይወታቸው ከአካላዊ ጥቃት እስከ ቤተሰብ ስቃይ ያደረሳቸው አባጣ ጎባጣ መንገድ ላይ ማለፋቸውንም ያስታውሳሉ፡፡





ፖለቲከኛው ከምስረታው ጀምሮ አባልና አመራር ከነበሩበት ኦፌኮ በተለየ መንገድ ላይ እንዲቆሙ ካደረጉአቸው ጉዳዮች ከ2013 ዓ.ም. ስድስተኛው ብሔራዊ ምርጫ የመገለል ውሳኔ እና ሌሎችም መኖራቸውን ጠቃቅሰዋል፡፡ “መድረክ ውስጥ የተፈጠረው ልዩነትና በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ይመራ የነበረው የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ከመድረክ መውጣት ደስተኛ አልነበርኩም” ያሉት አቶ ደስታ ፓርቲው ከስድስተኛ ብሔራዊ ምርጫ መውጣቱን እና ባላብራሩዋቸው ሌሎች የፖለቲካ ሁኔታ ደስተኛ አለመሆናቸው ከፓርቲው እራሳቸውን ለማግለል እንዳበቃቸውም ጠቁመዋል፡፡



ፖለቲካው ለህብረተተሰቡ ትክክለኛ እልባት አላመጣም የሚል እምነትም መያዛቸውን የገለጹት አቶ ደስታ፤ በዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስም ጊዜ ወስደው በሰፊው ስለማሰባቸው አስረድተዋል፡፡



በአዲሱ የፖለቲካ መንገዳቸው “የተከፋፈለውን ፖለቲካ በማደስ ለተቃዋሚውም ሆነ ለገዢው ፓርቲ አስተማሪ ሊሆን በሚችል አካኋን ለአሁናዊው የአገሪቱ ሁኔታ አስተማሪ ሊሆን የሚችል ፓርቲ ይዘው ለመምጣትም እንደሚሰሩ” በአስተያየታቸው ጠቁመዋል፡፡



ከፖለቲከኛ ደስታ ዲንቃ ጋር ኦፌኮን የለቀቁ ስለመኖራቸው



አቶ ደስታ ከእርሳቸው ጋር ሌሎች ሁለት የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረንስማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ኃላፊነታቸውንና አባልነታቸውን ለቀው በመውጣት በአዲሱ ፓርቲ ምስረታ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡ የግለሰቦቹን ስም ግን ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡



ፖለቲከኛ ደስታ ድንቃ በኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ ውስጥ ከፓርቲው በመውጣት ኃለፊነታቸውን ለመልቀቅ እስከወሰኑበት ጊዜ ድረስ የፓርቲውን ማዕከላዊ ኮሚቴና ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አሰራር የመከታተልና የመቆጣጠር ኃላፊነት ያለውና ተጠሪነቱም ለጠቅላላ ጉባኤ የሆነው የኦዲትና ኢንስፔክሽን ዋና ጸሃፊ ሆነው ስያገለግሉ ነበር፡፡ ፖለቲከኛው የፖለቲካ ድርጅቶች ጥምረት የሆነው መድረክን በዋና ጸሃፊነት ከማገልገል እስከ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤት ሊቀመንበር ኃላፊነትም አገልግለው ያውቃሉ፡፡



አቶ ደስታ ከኦፌኮ ስለለቀቁበት አግባብና ውሳኔ ላይ ዶይቼ ቬለ በፓርቲው ጽህፈት ቤት በኩል ማረጋገጫ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ግን በኃላፊዎቹ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆን ሃሳባቸውን ማካተት አልተቻለም፡፡



ሥዩም ጌቱ



ታምራት ዲንሳ



ሸዋዬ ለገሰ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

ከኦፌኮ አመራር አባልነት ወደ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ መስመር - ደስታ ዲንቃ

ከኦፌኮ አመራር አባልነት ወደ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ መስመር - ደስታ ዲንቃ

ሥዩም ጌቱ