DiscoverDW | Amharic - Newsጤፍ ወይስ ስንዴ? የአርሲ ገበሬዎች
ጤፍ ወይስ ስንዴ? የአርሲ ገበሬዎች

ጤፍ ወይስ ስንዴ? የአርሲ ገበሬዎች

Update: 2023-12-20
Share

Description

የምዕራብ አርሲ ዞን ገበሬዎች እስካሁን በብዛት የሚያመርቱትን ስንዴ ችላ እያሉ እርሻቸዉን ወደ ጤፍ እምራችነት እየቀየሩት ነዉ።ምዕራብ አርሲ ለረጅም ጊዜ የሚታወቀዉ በስንዴ አምራችነቱ ነዉ።ይሁንና የአካባቢዉ አርሶ አደሮች እንደሚሉት ከስንዴ ጋር ሲነፃፀር የጤፍ ዋጋ በማሻቀቡ፣ለስንዴ ምርት የሚያስፈልገዉ ማዳበሪያና ፀረ ተባይን የመሳሰለዉ ግብዓት ከጤፍ ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ በመሆኑ ወደ ጤፍ ምርት እያዘነበሉ ነዉ።



ከስንዴ ይልቅ የጤፍ ምርት



ጃላኔ ሀላኮ በምዕራብ አርሲ ዞን የነጌሌ አርሲ ወረዳ ሰዮ መጃ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ፤ ጤፍን አጭደው በማሽን ወደ መውቃት ይባትላሉ፡፡ በዚህ አከባቢ ለዘመናት አርሶ አደሩ ትኩረት የሚሰጠው፤ ብሎም አከባቢውም በስንዴ አምራችነት ብቻ ነበር የሚታወቀው፡፡ ጃሌኔ እና ቤተሰቦቻቸው ግን ለጤፍ ምርት ስራ አይነተኛ ትኩረት የሰጡ ይመስላል፡፡

ስንዴን በቀላሉ በትራክተር በታረሰ መሬት ላይ ዘርቶ በኮምባይነር መሰብሰብ ለዚህ አከባቢ አርሶ አደር እንግዳ ነገር አይደለም፡፡ ይህ ደግሞ ድካምን በእጅጉ ያቀልላል፡፡ ከዚህ ቀላል የስተራረስ መንገድ ጋር የተዋወቁት አርሶ አደሮች ታዲያ ከአድካሚው የጤፍ ምርት ጋር መላመድ ቀላል አልሆንላቸውም፡፡



እነ ጃሌኔ ግን ለዚህም መላ ያጡ አይመስልም፡፡ በሰው እጅ የታጨደውን ጤፍ ምርትን ከገለባ የሚለየውን በአገር በቀል እውቀት የተሰራን ማሽን ተጠቅመው ሒደቱን በተወሰነ መልኩ አቅልለውታል፡፡“የጤፍ ስራ በጣም አድካሚ ነው፡፡ በእጃችን ነው የምናጭደው፡፡ ያጨድነውን ጤፍ የሚወቃው ማሽነሪ ባይኖር ደግሞ ስራውን አድካሚና አሰልቺ ያደርገዋል፡፡ አሁን ግን ያጨድነውን ጤፍ ስናስገባበት ማሽኑ ገላባውን እየተፋ ምርቱን ለብቻ ይለይናል” ብለዋል ጤፍ አምራች አርሶ አደሯ ጃሌኔ ሃላኮ፡፡



ጃሌኔ እንደሚሉት በነሱ አከባቢ አሁን ከአንድ ሄክታር መሬት ከ20 ኩንታል የበለጠ የስንዴ ምርት አይገኝም፡፡ በዚህ መሬት ላይ ጤፍ ተዘርቶ 10 ኩንታል እንኳ ቢገኝ ግን ይበልት ያዋጣል ሲሉም ሞግተዋል፡፡ “ያው የጤፍ ጥቅም ብዙ ነው፡፡ ለምግብነት ይመረጣል፡፡ ለገቢም እጅግ ትርፋማ ያደርጋል፡፡ አንድ ኩንታል ስንዴ ገቢያ ብናወጣው 4000 ብር ነው አሁን የምንሸጠው፡፡ ጤፍ ግን 12 ሺኅ ብር ነው፡፡ ስለዚህ አንድ ኩንታል ጤፍ እና ሶስት ኩንታል ስንዴ እኩል ትቅም አላቸው ማለት ነው፡፡ እናም የጤፉ ስራ አድካሚ ቢሆንም ይብልጥ ውጤማ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ በዚያ ላይ ማዳበሪያ እና ሌሎች ግብዓት አጠቃቀም ላይ ጤፍ ከስንዴ እጅግ ያነሰ ወጪ ነው የሚጠይቀው” ይላሉ፡፡



ጤፍን ማምረት ከገቢያው ጥቅምም ባሻገር ሌላ ትቅም አለው



በዚሁ ተመሳሳይ ቀበሌ በጤፍ አጨዳ ላይ አግኝቶአቸው ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው ጀማል አብደላም ከዳመኔ የአየር ጠባይ ጋር እየተጋፈጡ በጤፉ አጨጃ ይባትላሉ፡፡ እሳቸው ደግሞ በዚህ ባረሱት መሬት ላይ ጤፍን መዝራት ምርጫቸው ያደረጉበትን ምክኒያት ሲያስረዱ ጤፍ መዝራት ከጥቅሙም ባሻገር ሌላ ነው ብለዋል፡፡



“በርግጥ አሁንም የስንዴ ምርት ጥቅሙ የተሸለ ነው፡፡ በቀላሉ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ስለምመረትና ድካም ስለሚያስቀርም ጭምር፡፡ አሁን በዚህ መሬት ላይ ጤፍ የዘራሁት ግን መሬቱ ተግረጋማ በመሆኑ ውሃ ይቋጥራል፡፡ መሰል መሬት ላይ ስንዴ ምንም አይወጣም፡፡ የጤፍ ትልቁ ጥቅም እዚህ ጋ መሬት አለመምረጡ ነው” ይላሉ፡፡



የስንዴ ምርት ግብዓቶች መናርና እየተለዋወጠ የመጣው የአየር ጠባይ



በዚህ ወረዳ በተለይም በአከባቢው በስፋት ስንዴን በማምረት የሚታወቁት አርሶ አደር አብዱሮ መሃመድም የጤፍ ምርት ላይ ፊታቸውን ስለማዞር ያልማሉ፡፡ አርሶ አደሩ የስንዴን ምርትም ከጊዜ ወደ ጊዜ አድካሚ እየሆነ የመጣ ይሉታል፡፡



“የዘንድሮን እንኳ ላውጋህ! ለዘመናት ስንዴ አምርተናል፡፡ እንደ ዘንድሮ የተፈተንበት ጊዜ ግን የለም፡፡ ፈተናው የጀመረን ከማዳበሪያው አቅርቦት ነው፡፡ ዋጋውም ጨምሮ ማግኘቱ ፈታኝ ነበር፡፡ ከዚያን የአረም የዋጋ መድሃኒት ስንል ስንቴ ወጪ አውጥተናል፡፡ በተለይ ዋግ ዘንድሮ ከፍቶ አራት-አምስት ጌዜ ረጭተንበታል፡፡ ጤፍ ግን የስንዴን ያህልማዳበሪያ አይፈጅም፡፡ በዋግና መሰል የእህል በሽታ የመጠቃት እድሉም ዝቅ ያለ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ እናም ለወደፊቱ በዚህ ላይ ለማተኮር እንትራለን፡፡ እኔ አሁን ዘንድሮ እጅግ ከፍተናኛ ወጪ ያወጣሁበት አንድ ሄክታር ስንዴ 30 ኩንታል ብቻ ነው ያገኘሁበት” ብለዋል፡፡



የወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊው አቶ ጀማል መሃመድም አርሶ አደሩ ከስንዴም ባሻገር እንደ ጤፍ ላሉ ምርቶች አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን እንዲጠቀም ጥረት እየተደረገ መምጣቱን ያወሳሉ፡፡



“ዘንድሮ እንዳጋጠመን ጊዜውን ያልጠበቀ ዝናብ በደረሰ ምርት ላይ ስመጣ ምርቱን ቶሎ ለመሰብሰብ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ውጤቶች መጠቀም አይነተኛ ሚና አለው” ያሉን አቶ ጀማል ከዚህ ረገድ ከጥቃቅን የፈጠራ ውጤቶች ጀምሮ ለግብርናው በግብዓትነት ለማቅረብ ጥረቶች አሉ ሲሉ አብራርተውልናል፡፡



የጤፍ ዋጋ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለይም ከባለፈው የምርት ዘመን ጀምሮ በእጅጉ ንሯል፡፡ አዲስ አበባን ጨምሮ በአገሪቱ ትላልቅ ከተሞች አንድ ኩንታል ጤፍ ከ13 ሺህ ብር ጀምሮ ነው የሚሸጠው፡፡



ሥዩም ጌቱ



ነጋሽ መሐመድ



እሸቴ በቀለ

Comments 
loading
In Channel
loading
00:00
00:00
1.0x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

ጤፍ ወይስ ስንዴ? የአርሲ ገበሬዎች

ጤፍ ወይስ ስንዴ? የአርሲ ገበሬዎች