በዓለም ላይ የሚገኝ የጦር መሳርያ ኢንዱስትሪ ከፍተኛ የጦር መሳርያ ንግድ ማካሄዱ ተነገረ
Update: 2025-12-01
Description
የዓለም ጦር መሳርያ ኢንዱስትሪ ከፍተኛ የጦር መሳርያ ንግድ ማካሄዱ ተነገረ
በዓለም ዙርያ በበርካታ ግጭቶች በሚታዩበት በአሁኑ ወቅት ጦር መሳሪያ ኢንዱስትሪዉም ከፍተኛ የጦር መሳርያ ንግድን ማስመዝገቡ ተዘገበ። የዓለማችን ትልልቅ የሚባሉት 100 የጦር መሳሪያ አምራቾች ከትጥቅ እና ጦር መሳርያዎች ሽያጭ በጎርጎረሳዉያኑ 2024 ከሚያገኙትን ገቢ በድምሩ 5.9 በመቶ መጨመሩን በስቶክሆልም የሚገኘዉ ዓለም አቀፉ የሰላም ምርምር ተቋም (SIPRI) ይፋ ባደረገዉ ዓመታዊ መግለጫ አስታዉቋል። የጦር መሳርያ ኢንዱስትሪዉ ባካሄደዉ ከeተኛ የጦር መሳርያ ሽያጭ የምንዛሪ መለዋወጥንም ማስከተሉ ተመልክቷል።
የጦር መሳርያ አምራች ኩባንያዎች በዓመት ዉስጥ ባካሄዱት የጦር መሳርያ ሽያጭ ወደ 679 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወይም (586 ቢሊዮን ዩሮ አካባቢ) አግኝተዋል። ዓለም አቀፉ የሰላም ምርምር ተቋም ይፋ እንዳደረገዉ የጦር መሳርያ ግዥ ፍላጎት የጨመረዉ በዩክሬን እና በጋዛ ሰርጥ በሚታየዉ ጦርነት፣ በዓለም አቀፍ እና በክልል ደረጃ በተከሰተዉ የጂኦፖለቲካዊ ውጥረት እና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመጣው ወታደራዊ ወጪ ምክንያት መሆኑን አብራርቷል።
Comments
In Channel























