DiscoverDW | Amharic - Newsበጠለምት ወረዳ በመኖ እጥረት ከ3ሺህ በላይ እንስሳት መሞታቸውን ወረዳው አስታወቀ
በጠለምት ወረዳ በመኖ እጥረት ከ3ሺህ በላይ እንስሳት መሞታቸውን ወረዳው አስታወቀ

በጠለምት ወረዳ በመኖ እጥረት ከ3ሺህ በላይ እንስሳት መሞታቸውን ወረዳው አስታወቀ

Update: 2025-08-15
Share

Description

በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን በጠለምት (ደጃች ሜዳ) ወረዳ የዝናብ እጥረት ባስከተለው ችግር በሽዎች የሚቆጠሩ እንስሳት በርሀብ መሞታቸውን የወረዳ አስተዳደሩ አስታውቋል፣ ሞት በሠዎች ላይ ባይከሰትም በችግሩ ምክንያት ብዙዎቹ አካባቢያቸውን እየለቀቁ እየተሰደዱ እንደሆነም ተግልጧል፡፡ የሰሜን ጎንደር ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት ጉዳዩ በትክክል ከተጠና በኋላ ምላሽ እንደሚሰጥ አመልክቷል፡፡



በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት (ደጃች ሜዳ) ወረዳ በክረምቱ በለምዝነቡ በወረዳው 11 ቀበሌዎች በግጦሽና በእንስሳት ምግብ እጦት ሠዎችና እንስሳት መቸገራቸውን ወረዳ አስተዳደሩ አመልክቷል፡፡ የጠለምት ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግዛው ዘነበ በወረዳው 5ሺህ 669 ሔክታር መሬት በዘር ተሸፍኖ የነበረ ቢሆንም መብቀል አልቻለም፣ በርካታ እንሳሳት በመኖ እጥረት ህይወታቸው አልፏል ብለዋል፡፡ በአጠቃላይ በወረዳው 24 ቀበሌዎች ከሚኖረው 132 ሽህ ህዝብ መካከል የዝናብ እጥረት ባለባቸው ቆላማዎቹ 11 ቀበሌዎች የሚኖሩ ከ52ሺህ በላይ ዜጎች ለምግብ እጥረት መጋለጣቸውን አመልክተዋል፡፡



“በመኖ እጥረት 3ሺህ 500 እንስሳት ሞተዋል” የወርዳው ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ ግዛው ዘነበ



“... 411 የዳልጋከብቶች 172 የጋማ እንስሳት፣ 2912 ፈየሎችና በጎች በተከሰተውየዝናብ እጥረት ተከትሎ መኖ በመጥፋቱ ህይወታቸው አልፏል” ብለዋል፡፡

የወረዳው አደጋ መከላከልና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ቡድን መሪ አቶ መሠረት ጥላሁን በተልይ በዝናብ እጥረቱ 3ሺህ ያክል እንሰሳት ህይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ከሞት የተረፉት 71ሺህ 500 እንስሳትም ከፍተኛ የመኖ እጥረት ላይ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡



“ወጣቶች እየተሰደዱ ነው” የጠለምት ወረዳ አደጋ መከላከል ጽ/ቤት



አብዛኛው የአካባቢው ወጣቶች ወደ አጎራባች አካባቢዎች መሰደዳቸውን ያስረዱት አቶ መሠረት፣ ደካሞችና መንቀሳቀስ የማይችሉት ብቻ ናቸው ቦታቸውን ያልለቀቁት ብለዋል፡፡

ኮሚቴ ተቋቁሞ በከፋ ሁኔታ የተጎዱ አካባቢዎችን እንዲመለከት መደረጉንና ግኝቱ ወደ ዞን መላኩን ነው ቡድን መሪው ያሰርዱት፡፡



የጠለምት ወርዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጋሻው እንግዳውየዝናብ እጥረቱበበርካታ የወርዳው ቀበሌዎች መከሰቱን ጠቁመው፣ ሁኔታውን የሚከታተል ኮሚቴ ከተለያዩ ጽ/ቤቶች ተዋቅሮ እየሰራ እንደሆነ አመልክተዋል፡፡

የሰሜን ጎንደር ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰላምይሁን ሙላት የዝናብ እጥረቱ ያስከተለው ችግር ግኝት ከተገመገመ በኋላ አስፈላጊው እገዛ እንደሚደርግ ገልተዋል፡፡ በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን 7 ወረዳዎች በሚገኙ 57 ቀበሌዎች በተከሰተ የዝናብ እጥረት 175ሺ 915 ሠዎች ለችግር መጋለጣቸውን ቀደም ሲል የደቡብ ጎንደር ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽ/ቤት ለዶይቼ ቬሌ መግለፁ ይታወሳል፡፡



ዓለምነው መኮንን

ኂሩት መለሰ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

በጠለምት ወረዳ በመኖ እጥረት ከ3ሺህ በላይ እንስሳት መሞታቸውን ወረዳው አስታወቀ

በጠለምት ወረዳ በመኖ እጥረት ከ3ሺህ በላይ እንስሳት መሞታቸውን ወረዳው አስታወቀ

ዓለምነው መኮንን