DiscoverDW | Amharic - Newsየተጽዕኖ ፈጣሪ ኢትዮጵያውያን ሽልማት በዩናይትድ ስቴትስ
የተጽዕኖ ፈጣሪ ኢትዮጵያውያን ሽልማት በዩናይትድ ስቴትስ

የተጽዕኖ ፈጣሪ ኢትዮጵያውያን ሽልማት በዩናይትድ ስቴትስ

Update: 2025-10-15
Share

Description



በተለያዩ ዘርፎች ተፅዕኖ ፈጣሪ ናቸዉ የተባሉ አራት ኢትዮጵያዊያን፣ዩናይትድ ስቴትስ ሜሪላንድ ውስጥ ተሸልመዋል።ሽልማቱን ያዘጋጀዉ ኖቫክ ኮኔክሺን የተባለዉ ድርጅት ነዉ።የድርጅቱ ኃላፊ ጋሻዉ አብዛ እንዳሉት ሽልማቱ ለማሕበረሰባቸዉና ለሐገራቸዉ ታላቅ ሥራ ላከናወኑ ግለሰቦች በየዓመቱ የሚሰጥ ነዉ።



የአፍሪቃ ታላቁ ሩጫ



የዘንድሮ መርሃ ግብር የተጀመረው፣ባለፈውቅዳሜ ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ለሰባተኛ ጊዜ በተካሄደው የአፍሪካ ታላቁ ሩጫ ውድድር ነበር።



ይህ ውድድር፣በህጻናት የአንድ ኪሎሜትር እንዲሁም በአዋቂዎች የአምስት ኪሎ ሜትር ሲሆን፣በሺዎች የሚቆጠሩ የዳያስፖራው ማኀበረሰብ አባላትና ከኢትዮጵያ የመጡ እንግዶች ተሳትፈውበታል።



የተጽዕኖ ፈጣሪዎች ሽልማት



በማግስቱ ደግሞ የኦሎምፒክና የዓለም ሻምፒዮና ሜዳሊያዎች ባለቤት አትሌት መሠረት ደፋር፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣አንጋፋው ድምፃዊ ማህሙድ አህመድ እና የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያው ሰይፉ ፋንታሁን ተሸላሚ የሆኑበት የላቀ አስታዋጽኦ የዕውቅና እና የምስጋና ፕሮግራም ተካሄዷል።



እውቅና የተሰጣቸው እነዚህ ተሸላሚዎች፣ በየተሰማሩበት ሙያ ተጽዕኖ መፍጠር የቻሉ መሆናቸውን፣የኖቫ ኮኔክሽን ዳይረክተር ዶክተር ጋሻው አብዛ ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል።



‘’የእኛ ሽልማት፣ኢምፓክት አዋርድ ነው የሚባለው። ኢምፓክት የሚለው ተጽዕኖ፣አስተዋጽኦ ተሻጋሪ ለውጥ ያመጡ ናቸው። እነዚህ ሰዎች ካየናቸው በዚህ ዙርያ ላይ ብዙ ሰዎች ላይ የማያሻሙ እንደሆኑ እንገምታለን። ''



ተሸላሚዎቹ፤ከዲሲ፣ሜሪላንድና ቨርጂኒያ ግዛትና ከተማዎች፣ተወካዮች የዕውቅና ሰርተፍኬታቸውን ሞቀ ባለ ስነስርዓት ተቀብለዋል።



ሩጫና ውድድሩን ወደፊት በአፍሪቃ ደረጃ የማዘጋጀት ወጥን እንዳላቸውም ዶክተር ጋሻው ተናግረዋል።



''እንደስሙ እንዲኖር ጥረት እናደርጋለን፤ እያደረግን ነው። ወደኋላ ስንል ከመጀመሪያው ሩጫ ጀምሮ።አንድም የፈተናችሁ ብትለን፣ይህን ዝግጅት ወደ አፍሪቃዊነት ስሜት ለማምጣት የምናደርገው ጥረት ፈታኝ ነበር። እና መቼም ተቋሙን አፍሪቃን መሰረት አድርጎ እንደቆመ ድርጅት ያላሳለሰ ጥረት እያደረግን ነው። ''



የመሰረት ደፋር አስተያየት



አትሌት መሰረት ደፋር፣ያገኘችውን ሽልማት በማስመልከት ለዶቼ ቬለ በሰጠችው አስተያየት፣ ሽልማቱ ላበረከተችው አስተዋጽኦ ዕውቅና ያገኘችበት በመሆኑ እንዳስደስታት ተናግራለች።



'' የአፍሪካ ኢምፖክት ሽልማት ለእኔ በሕይወቴ በጣም የተደሰትኩበትና የሰራሁት ሥራ ዋጋ እንዳለው ያረጋግጥኹበት ሽልማት ስለሆነ በጣም ተደስቻለሁ። ትልልቅ ቦታ ላይ በሙዚቃው፣የአየር መንገድ እንዲሁም ሰይፉ ከእነሱ ጋር ይህን ሽልማት በመጋራቴ በጣም ኩራት ተሰምቶኛል።



አትሌት መሰረት ደፋር፣ ሽልማቱ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን እያገለገለች ከመሆኗ አንፃር፣ለወደፊት ስራዋ ሽልማቱ የሚኖረውን አስተዋጽኦ በተመለከተ ጠይቀናት ስትመልስ፤



''እንግዲህ እኔ አንድ ነገር አድርጋለሁ ብዬ አስባለሁ። እኔ ወደ ሩጫው ዓለም የገባሁት በትምህርት ቤት፣በዞን፣በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተወዳደርኹት ውድድሮች ላይ ነው ይህንን ዕድል ያገኘኹት። በአሁኑ ሰዐት ግን፣የትምህርት ቤት ውድድርም፣ የዞንም በተለይ ደግሞ በክልልም ወረዳ የሚባሉ ውድድሮች ቀርተዋል። እነዛ ውድድሮች ቢመለሱና እኔም የእዛው አንድ አካል ሆኜ፣በተለይ ደግሞ አዲስ አበባ ላይ እኔም ከአዲስ አበባ እንደመገኘቴ፣የትምህርት ቤቶችን ውድድር መመለስና ቢያንስ አዲስ አበባ ላይ የተወሰኑ አትሌቶችን፣በእኔ ደረጃ የሚወጡ አትሌቶችን ለማፍራት በጣም ትልቅ ጉጉት አለኝ። ''ብላለች።



ታሪኩ ኃይሉ



ነጋሽ መሐመድ



ታምራት ዲንሳ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የተጽዕኖ ፈጣሪ ኢትዮጵያውያን ሽልማት በዩናይትድ ስቴትስ

የተጽዕኖ ፈጣሪ ኢትዮጵያውያን ሽልማት በዩናይትድ ስቴትስ

ታሪኩ ኃይሉ