DiscoverDW | Amharic - Newsየቀጠለው የትግራይ ክልል ኃይሎች ተቃውሞ
የቀጠለው የትግራይ ክልል ኃይሎች ተቃውሞ

የቀጠለው የትግራይ ክልል ኃይሎች ተቃውሞ

Update: 2025-10-14
Share

Description

የደሞዝ እና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች ጥያቄ በመያዝ ትላንት በመቐለ የተቃውሞ ትእይንት ያደረጉት የትግራይ ሐይሎች የሰራዊት አባላት እስከ ማምሻው ድረስ መንገዶች ዘግተው የዋሉ ሲሆን፥ ይህ ተቃውሞ በሌሎች የትግራይ ሐይሎች አባላት ቀጥሎ ዛሬ ደግሞ ከመቐለ ቅርብ ርቀት ባለቸው አጉላዕ ጨምሮ በክልሉ ምስራቃዊ ዞን በርካታ ቦታዎች መንገድ በመዝጋት ቀጥሎ ውሏል። ይህ ተከትሎ ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ ከመቐለ ወደ ዓዲግራት የሚወስደው መንገድ ተዘግቷል፥ የህዝብ እና የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ተስተጓጉሏል።



የትግራይ ሐይሎች አባላት ተቃውሞ



በተለይም በመቐለ ተቃውሞ ያደረጉት የትግራይ ሐይሎች ሰራዊት አባላት ትላንት ማምሻውን በሐወልቲ ሰማእታት አደራሽ ከክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ከህወሓት መሪ ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን ይህ ውይይት ለሁሉም መገናኛ ብዙሐን የተከለከለ እና በዝግ የተደረገ ነው። የትግራይ ሐይሎችአባላቱ የደሞዝ ጭማሪ፣ ጥቅማጥቅሞች እንዲሁም ሌሎች ጥያቄዎች ማቅረባቸው ቀጥለዋል። እየቀጠለ ያለው ተቃውሞ ተከትሎ የድጋፍ መግለጫ ዛሬ ያወጣው የትግራይ ነፃነት ፓርቲ በበኩሉ፥ በትግራይ ያለው ስርዓት ለመገርሰስ ወጣቶች፣ ሴቶች እና ሌሎች የማሕበረሰብ ክፍሎች ጥያቄዎቻቸው ይዘው ተቃውሞው ይቀላቀሉ ሲል ጥሪ አቅርቧል።



ፖለቲካዊ ቀውስ



በሌላ በኩል በትግራይ ስርዓቱ የፈጠረው ከፍተኛ ፖለቲካዊ ቀውስ ተከስቶ ይገኛል ሲሉ የገለፁት የተቃዋሚው ትንሳኤ ስርዓት ቃንጪ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ደጋፊ ጎደፋይ በበኩላቸው የጦርነት እና የእርስበርስ ግጭት ስጋት እንዲሁም ስርዓት አልበኝነት መንገሱ እንደማሳያ ያነሱታል።



በዛሬው ዕለት ከመቐለ ዓዲግራት የሚወስደው ጎዳና የዘጉ የትግራይ ሐይሎችሰራዊት አባላት፥ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ ጎዳናው እንደዘጉ ናቸው። ትላንት የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ፣ የህወሓት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ጨምሮ ሌሎች የሰራዊቱ ከፍተኛ አዛዦች የተገኙበት እና ተቃውሞ ካደረጉ የሰራዊት አባላት ጋር በተደረገ ዝግ ስብሰባ ውጤት የተባለ ነገር የለም።



የህወሓት ክስ



ይህ በእንዲህ እንዳለ ሳምንታዊ መልእክት በማለት ትላንት መግለጫ ያሰራጨው ህወሓት፥ የኢትዮጵያ መንግስት 'ከሃዲዎች' ብሎ በጠራቸው አካላት በመጠቀም ፀረ ትግራይ፣ ህወሓት እና የትግራይ ሐይሎች ፕሮፖጋንዳ እያካሄደ ይገኛል ሲል ከሷል። አሁንም ምርጫችን ሰላም ነው የሚለው የህወሓት መግለጫ፥ የኢትዮጵያ መንግስት የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት የሚቃረን ተግባር ከመፈፀም ይቆጠብም ብሏል። የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት የሰላም ስምምነቱ በመጣስ እርስበርስ ይካሰሳሉ።



በቀጠለው ፖለቲካዊ ቀውስ ላይ አስተያየት የሰጡን ፖለቲከኛው አቶ ደጋፊ ጎደፋይ በበኩላቸው የሰላም ስምምነቱ ይዘት በትክክል መተግበር ለበርካታ ቀውሶች መፍትሔ ሊሆን ይችላል ብለዋል።



ህወሓት ባቀረበው ክስ ዙርያ ከኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት ባለስልጣናት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።



ሚሊዮን ኃይለሥላሴ



ኂሩት መለሰ



ታምራት ዲንሳ





Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የቀጠለው የትግራይ ክልል ኃይሎች ተቃውሞ

የቀጠለው የትግራይ ክልል ኃይሎች ተቃውሞ

ሚሊዮን ኃይለ-ሥላሴ