DiscoverDW | Amharic - Newsአንድ ለአንድ፤ ከ«የትግራይ የሰላም ሃይሎች መስራች» አቶ ተስፋይ ንጉሰ ጋር
አንድ ለአንድ፤ ከ«የትግራይ የሰላም ሃይሎች መስራች» አቶ ተስፋይ ንጉሰ ጋር

አንድ ለአንድ፤ ከ«የትግራይ የሰላም ሃይሎች መስራች» አቶ ተስፋይ ንጉሰ ጋር

Update: 2025-08-15
Share

Description

የህወሐት መከፋፈልን ተከትሎ በትግራይ የጸጥታ ሃይል እራሱን «ከኮር በላይ ያሉ አመራሮች» ብሎ ያደራጀው ወታደራዊ ክንፍ በህወሐት ፖለቲካ በቀጥታ በመሳተፍ ከተልዕኮው ውጭ እየሰራ ነው በሚል በተቃዋሚዎችና በትግራይ ስቪክ ማሕበረሰብ በተደጋጋሚ ትችቶች ሲሰነዘሩ ተደምጠዋል። ወታደራዊ ክንፉ ከህወሐት ጉባኤ እስከ የሕዝብ አደረጃጀቶች ውስጥ በመግባት በቀድሞው የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት በአቶ ጌታቸው ረዳ የተሾሙ የከተማ ከንቲባዎች፣ የዞን፣ የወረዳና የቀበሌ አስተዳደሮችን በጠብመንጃ አፈሙዝ በተደገፈ የማህተም ነጠቃና የቢሮ ሰበራ እያከናወነ መሆኑን በመቃወም የደቡብና የደቡብ ምሥራቅ ትግራይ ክልል ነዋሪዎች በተደጋጋሚ ሰላማዊ ሰልፎችን አድርገው ድምጻቸውን አሰምተዋል። የመረጧቸውን የሀገር ሽማግሌዎች በመላክም በተደጋጋሚ ከክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ ጋር ውይይቶች ተደርገዋል። ሰላማዊ ሰልፎቹና ውይይቶቹ ግን መፍትሔ እንዳላመጡ የአካባቢው ነዋሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተውና በመገናኛ ብዙሃን ጭምር ቅሬታቸውን ሲገልጹ እየተደመጡ ነው።

በተለይ የወታደራዊ ክንፉ በፖለቲካ ውስጥ እየፈጸመ ነው ያሉትን ጣልቃ ገብነት በመቃወምም በዓፋር ክልል እራሱን «የትግራይ የሰላም ሃይሎች» ብሎ የሚጠራው ስብስብ የትጥቅ ትግል ለማድረግ እየተንቀጣቀሰ እንደሚገኝ መረጃዎች ያመላክታሉ። የትግራይ የጸጥታ ቢሮ ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ በእነዚህ ሃይሎች አንድ አባሉ እንደተገደለበት አስታውቋል። የትግራይ የሰላም ሃይሎች መስራቹ ግን ይህን ያስተባብላሉ። በሌላ ወገን የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት ከነዚህ ሃይሎች ጋር ሽምግልና ለማከናወን እቅድ እንዳለ ተናግረዋል።

እነዚህን ወቅታዊ ጉዳዮችን መነሻ በማድረግ የ«የትግራይ የሰላም ሃይሎች» መስራች የሆኑት አቶ ተስፋይ ንጉሠን አነጋግረናል።

አቶ ተስፋይ ነዋሪነታቸው በስዊድን አገር የነበረ ሲሆን በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን «ተስፋይ ራያ» በሚል መጠሪያ በትግራይ ፖለቲካ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ይታወቃሉ። በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ ቀደም ሲል ከመሰረቱት የትግራይ የሰላም ሃይሎች ጋር በትግል ላይ እንዳሉ ገልጸውልናል።

ከእሳቸው ጋር የተደረገውን ሙሉውን ቃለ ምልልስ የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን እንድታደምጡ በአክብሮት እንጋብዛለን።



ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

ሽዋዬ ለገሠ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

አንድ ለአንድ፤ ከ«የትግራይ የሰላም ሃይሎች መስራች» አቶ ተስፋይ ንጉሰ ጋር

አንድ ለአንድ፤ ከ«የትግራይ የሰላም ሃይሎች መስራች» አቶ ተስፋይ ንጉሰ ጋር