DiscoverDW | Amharic - Newsዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: ባህሎቻችን በአዳጊ ሴቶች አይን
ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: ባህሎቻችን በአዳጊ ሴቶች አይን

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: ባህሎቻችን በአዳጊ ሴቶች አይን

Update: 2023-09-01
Share

Description

በሀዋሳ ከተማ ነዋሪ የሆኑት የ15 ዓመቷ ታዳጊ ረድኤት አበራ እና የ17 ዓመቷ ናዝራዊት ከበደ በሚኖሩበት ማህበረሰብ ውስጥ የሚገኙ ባህላዊ ልማዶች ሁለት አይነት መልክ አላቸው ይላሉ፡፡ ረድኤት እና ናዝራዊት ዶቼ ቬለ DW በሚያዘጋጀው የዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዝግጅት ጋር በነበራቸው አጭር የውይይት ቆይታ ባህላቸው በጎ ሊባሉ የሚችሉ ተግባራት የሚበዙበት ሥለመሆኑ ጠቅሰዋል ፡፡ በተለይ በዓላትን በጋራ ማክበር ፣ እቁብ በመሰብሰብ በኢኮኖሚ መደጋገፍ ፤ እንዲሁም ለቅሶ የመሳሰሉ ችግሮች ሲያጋጥሙ በዕድር አማካኝነት ሐዘንን መጋራት አብሮነትን የሚያጠናክሩ እሴቶች እንደሆኑ ታዳጊዎቹ ገልጸዋል ፡፡ ያም ሆኖ ሊቀሩ ወይም ሊሻሻሉ የሚገባቸው ልማዶች አሉ የምትለው ታዳጊረድኤት “ በተለይ በማህበረሰቡ ውስጥ ለሴት ልጅ ያለው ያልተገባ አመለካከት፣ እንዲሁም የግርዛትና የጠለፋ ድርጊቶች በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው “ ብላለች ፡፡አንደ ባህል ሊሻሻሉ የሚገባቸው ልማዶች መኖራቸውን የምትናገረው ናዝራዊት በበኩሏ “ በጊዜ አጠቃቀም ላይ ያለን ዝቅተኛ ግንዛቤ እንዲሁም ደካማ የሥራ ባህል ይስተዋልብናል ፡፡ ይህ ሊለወጥ የሚገባ አስተሳሰብ ነው “ ብላለች ፡፡



ሊሻን ዳኜ / ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ልደት አበበ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: ባህሎቻችን በአዳጊ ሴቶች አይን

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: ባህሎቻችን በአዳጊ ሴቶች አይን