DiscoverDW | Amharic - Newsየዶቼ ቬለ ዲጅታል ጉዞ፤ ከሬዲዮ ሞገዶች ወደ ሳተላይት እና ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች
የዶቼ ቬለ ዲጅታል ጉዞ፤ ከሬዲዮ ሞገዶች ወደ ሳተላይት እና ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች

የዶቼ ቬለ ዲጅታል ጉዞ፤ ከሬዲዮ ሞገዶች ወደ ሳተላይት እና ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች

Update: 2025-10-22
Share

Description

ከ60 ዓመታት በላይ በአጭር ሞገድ ስርጭቱን ሲያስተላልፍ የቆየው ዶቼ ቤለ የአማርኛው ክፍል ከጥቅምት 16 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ጀምሮ የአጭር ሞገድ ሥርጭቱን ያቋርጣል።የዛሬው የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዝግጅት የዶቼ ቤለ የአማርኛው ክፍል ላለፉት 60 ዓመታት ከአጭር ሞገድ ወደ ሳተላይት እና ማኅበራዊ መገናኛ መገናኛ ዘዴዎች ባደረገው ዲጅታል ሽግግር ላይ ያተኩራል።

በጎርጎሪያኑ 1953 የተመሰረተው ዶይቸ ቬለ (DW) ዜናን፣ ባህልን እና የጀርመንን አመለካከት ለተቀረው አለም ለማሰራጨት ነበር በአጭር ሞገድ የራዲዮ አገልግሎቱን የጀመረው።በቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን መረጃ የማግኘት ለማይችሉ ሰዎች በተለይም የፕሬስ ነፃነት በተገደበባቸው ቦታዎች DW ወሳኝ የመረጃ ምንጭ በመሆን አገልግሏል።አማርኛን ጨምሮ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን እና በድረገጽ በ32 ቋንቋዎች የሚያሰራጨው ዶይቸ ቬለ ዘመኑ የወለዳቸውን ቴክኖሎጅዎች በመጠቀም ከአጭር ሞገድ እስከ ሳተላይት እና ዲጂታል መድረኮች ሽግግር በማድረግ ላይ ይገኛል።



የአጭር ሞገድ ሬዲዮ ዘመን



በጎርጎሪያኑ 1965 ዓ/ም የተጀመረው እና ከ60 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የዶቼ ቬለ የአማርኛ አገልግሎትም በዚሁ የቴክኖሎጂ ሽግግር ውስጥ እያለፈ ነው።ዶይቸ ቬለ የአማርኛ አገልግሎት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የውጭ ሀገር ሬዲዮ ጣቢያ ሲሆን፤በጊዜው በሀገር ውስጥ የነበሩት መገናኛ ዘዴዎችም በጣም ጥቂት ነበሩ ። ጣቢያው በአጭር ሞገድ የአለም አቀፍ ዜናዎች፣ ወቅታዊ ጉዳዮች እና ትምህርታዊ ዝግጅቶችን በማቅረብ ታማኝ ምንጭ ለመሆን በቅቷል።ጣቢያው በአጭር ሞገድ ስርጭቱ ለብዙ የኢትዮጵያውያን ዓለምን የሚመለከቱበት ብቸኛ መስኮት እና ከድንበር እና ከመንግስት ሳንሱር ያለፈ ድምጽ ሆኖ አገልግሏል።



የቴክኒክ ባለሙያው እና የዶቼ ቬለ የለንደን ዘጋቢ ድልነሳው ጌታነህ።የአጭር ሞገድ ስርጭትን«መልዕክተኛ» ይለዋል።ለመሆኑ የዶቼ ቬለ የአማርኛው ክፍል የአጭር ሞገድ ዘመን የቴክኒክ ሁኔታ እና አሰራር ምን ይመስል ነበር?አንጋፋው ጋዜጠኛ ነጋሽ መሀመድ ፤እንዲህ እንደዛሬው ፅሁፍ የሚተየበው በኮምፒዩተር ሳይሆን በታይፕ መሆኑን ያስታውሳል። መረጃም በኢሜል ሳይሆን በስልክ እና በደብዳቤ እንደነበር ገልጿል። ነጋሽ እንደሚያስታውሰው ቀጣዩ የጣቢያው ለውጥ የተጀመረው ከበይነመረብ እና የኮምፒዩተር ቴክኖሎጂ መምጣት ጋር ተያይዞ ነው።ነጋሽ እንደሚለው የኮምፒተር እና የበይነመረብ መምጣት ሁሉም ነገር ዲጅታል እንዲሆን አድርጓል። ስራንም በተቀላጠፈ ሁኔታ መስራት ተችሏል።ያኔ ታዲያ ጋዜጠኛው ፀሀፊም ቴክኒያሻንም ሆኖ መስራት ጀመረ ይላል።



የበይነመረብ እና ኮምፒዩተር መምጣት



ቀጣዩ የጣቢያው ለውጥ የተጀመረውከበይነመረብ እና የኮምፒዩተር ቴክኖሎጂ መምጣት ጋር ተያይዞ ነው። የኮምፒዩተር እና የበይነመረብ መምጣት ጋዜጠኞች የሚሰሩበትን ብቻ ሳይሆን፤ አድማጮች ሬዲዮ የሚጠቀሙበት መንገድ በእጅጉ ለውጧል። በዚህ ጊዜ ዶቼቬለ የአማርኛው ክፍል የዜና መፅሄቶችን፣ቃለመጠይቆችን እና የድምጽ ዘገባዎችን በበይነመረብ ተደራሽ የሚያደርግ የራሱን ድረ-ገጽ ከፍቷል።ይህ እርምጃ በብዙ ምክንያቶች ጠቃሚ የነበረ ሲሆን፤ የጣቢያውን ዝግጅቶች መርጦ ለማድመጥ እና በውጪ ላሉ ኢትዮጵያውያን የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ አግዟል።ባለብዙ መገናኛ ዘዴ /multimedia storytelling / በመሆን፤ድምፅን ምስሎችን እና ፅሁፎችን በማጣመር ዝግጅቶችን ለታዳሚያን ማቅረብ ተችሏል።

የበይነመረብ መምጣት በመልክዓምድራዊ እና አካባቢያዊ ርቀት ይወሰን የነበረውን የሬዲዮ ስርጭት መሰናክሎችን አስቀርቷል። ይህም ተጠቃሚዎች ከመላው ዓለም የሚመጡ ስርጭቶችን እንዲከታተሉ አስችሏቸዋል። የስማርት ስልኮች እና የሞባይል መተግበሪያዎች መምጣት ደግሞ አድማጮች የድምፅ ይዘት የሚያገኙበትን መንገድ የበለጠ እንዲሻሻል አድርጓል። በተለይም የኢንተርኔት ሬድዮ በአንድ ጊዜ ዓለምአቀፋዊ ተደራሽነት እንዲኖር በማድረግ፤በተለያዩ የባህል አውዶች እና ዝግጅቶች አድማጮች እንዲዝናኑ አስችሏቸዋል።



በይነመረብ እና የሬድዮ ይዘት



የሬድዮ የይዘት ገጽታም እንዲሁ በበይነመረብ ምክንያት በከፍተኛ ደረጃ ተቀይሯል። ባህላዊ ራዲዮ ሙዚቃ፣ ዜና፣ ድራማ እና ውይይቶችን ጨምሮ ብዙ ተመልካቾችን ለመሳብ ሰፋ ባሉ ዝግጅቶች ላይ ያተኩሯል። ነገር ግን፣ በይነመረብ የተወሰኑ ታዳሚያንን ዒላማ ያደረጉ ሳቢ እና ልዩ ይዘት እንዲፈጠር ፈቅዷል። እንደ Spotify እና Apple Podcasts ያሉ የበይነመረብ መድረኮች በመምጣታቸው ደግሞ አድማጮች ለፍላጎቶቻቸው የሚቀርቡ ምቹ ይዘቶችን ማግኘት እንዲችሉ አድርጓል።ቀደም ባሉት ጊዜያት የሬድዮ ፕሮግራሞች በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ማስተካከልን የሚጠይቅ የታቀደ ዝግጅት ነበር፣ አሁን ግን ታዳሚያን በፈለጉት ጊዜ ማዳመጥ ይችላሉ። ይህም ዶቼቬለው ማንተጋፍቶት ሲለሺ እንደሚለው በይዘት እና በተጠቃሚ መካከል ያለውን ግንኙነት ቀርጿል።



የሳተላይት ሬድዮ እና ኤፍኤም አጋርነት



በጎርጎሪያኑ 1990ዎቹ እና 2000ዎቹ ባሉት አመታት DW የአማርኛው ክፍል ስርጭቱን ከሬዲዮ ወደ ሳተላይት በማስፋት ጥራት ያለው ሰፊ ሽፋን እንዲኖረው አድርጓል።DW በኢትዮጵያ ከሚገኙ የሀገር ውስጥ የኤፍ ኤም ጣቢያዎች ጋር በመተባበር ፕሮግራሞቹን በድጋሚ በማስተላለፍ ብዙ የከተማ አድማጮችን - የአጭር ሞገድ ሬዲዮ የሌላቸውንም ጭምር ለመድረስ ችሏል። ይህ የሳተላይት ስርጭት DW ፣ ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች እና በስደተኛ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ኢትዮጵውያን ስደተኞች ሳይቀር ዝግጅቶቹን እንዲያደምጡ ዕድል ሰጥቷል።በዚህ ሁኔታ ለአስርተ አመታት የዶይቸ ቬለ የአማርኛ አገልግሎት በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የሚታመን ድምጽ ሆኖ ቆይቷል። በአጭር ሞገድ የሬዲዮ ስርጭት የተጀመረው የዶይቸ ቬለ የአማርኛ አገልግሎት አሁን፤በሳተላይት ፣ በስማርት ስልኮች እና በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ተደራሽ የሚሆን ዘመናዊ፣ ባለብዙ መድረክ ሆኗል።



ሽግግር ወደ ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች



ሌላው የዶቼቤለ ለውጥ ከማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች መምጣት ጋርየተያያዘ ነው።ሌላው የዶቼቤለ ለውጥ ከማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች መምጣት ጋር የተያያዘ ነው።ማንተጋፍቶት ይህንን ዘመን የአዲስ መገናኛ ዘዴ ዘመን ይለዋል።በአሁኑ ጊዜ የሬዲዮ ጣቢያዎች ከታዳሚዎቻቸው ጋር ለመገናኘት የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ወሳኝ ሆነዋል። እንደ ትዊተር፣ ኢንስታግራም እና ፌስቡክ ያሉ መድረኮች ጣቢያዎች ይዘታቸውን ለማስተዋወቅ ብቻ ሳይሆን ከአድማጮች ጋር እንዲገናኙ ያስችላቸዋል። ይህ ተሳትፎ በአድማጮች እና በአሰራጮች መካከል የመቀራረብ እና የቤተሰብነት ስሜትን ያዳብራል። ይህም አስተያየታቸውን እንዲያካፈሉ፣ ሙዚቃዎችን እንዲመርጡ፣ ጥያቄዎችን እንዲጠይቁ ወይም በቀጥታ ውይይቶች ላይ መሳተፍ እንዲችሉ አድርጓል። በተጨማሪም፣ የማህበራዊ መገናኛ መድረኮች አዲስ ይዘትን ለማግኘት ጠቃሚ መሳሪያ ሆነው ያገለግላሉ። ብዙ አድማጮች ከፍላጎታቸው ጋር የሚጣጣሙ ፖድካስቶችን እና የቀጥታ ስርጭቶችን ለማግኘት በእነዚህ ቻናሎች ላይ ይተማመናሉ። ይህም ከነባሩ የሬዲዮ ተደራሽነት በላይ ስርጭቱን ያሰፋል። ይህ የእርስ በርስ መተሳሰር ደግሞ ሬዲዮን ከአንድ ወገን የመገናኛ ዘዴ ወደ አሳታፊነት ይቀይራል።ያም ሆኖ ነጋሽ እንደሚለው እነዚህ መድረኮች ስጋቶችን ይዘው ነው ብቅ ያሉት።የድምጽ ይዘት ከተለምዷዊ ሬዲዮ ወደ ሳተላይት እና ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሚደረገው ሽግግር፤ ከጠቅላላ ስርጭት በዲጂታል ቴክኖሎጂ እና በበይነመረብ አማካኝነት በፍላጎት ተመርጠው ወደ ሚደመጡ ግላዊ ዝግጅቶች መሻገርን ያካትታል። ይህ ሽግግር፣ ከታቀደ የስርጭት ይዘት በተጠቃሚዎች ቁጥጥር ስር ወደ ሆኑ እና ንቁ ተሳትፎ ወደሚደረግባቸው መድረኮች በመቀየር በአድማጮች እና በአሰራጮቹ መካከል ቀጥተኛ መስተጋብር እንዲኖር ያስችላል።ማንተጋፍቶት ይህንን ዘመን የአዲስ መገናኛ ዘዴ ዘመን ይለዋል።



የአጭር ሞገድ ስርጭት ማብቂያ



በዚህ ሁኔታ የዶቼቬለ ራዲዮ አማርኛው ክፍል ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋርእራሱን እያዘመነ መጥቷል። የቴክኖሎጂ እድገት የጣቢያው ዝግጅቶች የሚዘጋጁበትን እና የሚሰራጩበትን መንገድ የቀረጸ ሲሆን፤በተለይ የማህበራዊ መገናኛ መድረኮች የዜና ስርጭትን የተቀላጠፈ እንዲሆን አድርገውታል።እንደ ፌስቡክ፣ቴሌግራም፣ቲዊተር፣ ኢንስታግራም እና ቲክ ቶክ ያሉ ዲጅታል መድረኮች ደግሞ ነባሩን የመረጃ ፍሰት በመቀየር ላይ ናቸው።ዶይቸ ቬለ የአጭር ሞገድ ስርጭቶችን ቀስ በቀስ በማቋረጥም በአሁኑ ዘመን የሰዎችን የመግባቢያ ዘዴ በቀየሩት ዘመናዊ ዲጅታል መድረኮች ላይ መዋዕለንዋይ ማፍሰሱን ቀጥሏል።ዶቼቬለ የአማርኛው ክፍልም ከጥቅምት 16 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ጀምሮ የቀጥታ ሥርጭቶቹን በአጭር ሞገድ ማስተላለፉን በማቋረጥ በሳተላይት እና የዘመኑ ቴክኖሎጂ በወለዳቸው እንደ ፌስቡክ ፣ዩቱዩብ እና ቴሌግራምን በመሳሰሉ ዲጅታል መድረኮች እንዲሁም @dwamharic በሚለው አድራሻችን በዶቼቬለ ድረገፅ እና መተግበሪያም ስርጭቱን ይቀጥላል።

ምንም እንኳን ዶቼ ቬለ ዝግጅቶቹን ለአድማጮቹ የሚያደርስበት መንገድ በዚህ ሁኔታ ቢቀየርም ገለልተኛ፣ ታማኝ እና ሚዛናዊ መረጃ የማቅረብ ልዕኮው ግን ያው ሆኖ ይዘልቃል። አንጋፋው ጋዜጠኛ ነጋሽ መሀመድ እንደሚለው ግን ያለበይነመረብ ዝግጅቱን ለሚያደምጡ ርምጃው ይጎዳል።«በተለይ ቀውስ በሚፈጠርበት ጊዜ ያቀውስ ለተፈጠረበት አካባቢ መረጃ የምታሰራጭው በአጭር ሞገድ ነው።»ካለ በኋላ ኢንተርኔት ከ30 በመቶ በማይበልጥበት ኢትዮጵያም አጭር ሞገድ መቋረጥ ጉዳት መሆኑን ገልጿል።የሳተላይት ስርጭትም በኤለክትሪክ ላይ ጥገኛ በመሆኑ የተሻለ አማeŀXe መሆን እንደማይችል ገልጿል።



ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማዕቀፍ ተጭነው ያድምጡ።



ፀሐይ ጫኔ

አዜብ ታደሰ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የዶቼ ቬለ ዲጅታል ጉዞ፤ ከሬዲዮ ሞገዶች ወደ ሳተላይት እና ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች

የዶቼ ቬለ ዲጅታል ጉዞ፤ ከሬዲዮ ሞገዶች ወደ ሳተላይት እና ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች

ፀሀይ ጫኔ