DiscoverDW | Amharic - Newsየትግራይ ኃይሎች አባላት ዛሬ ለ3ኛ ቀን መንገዶች ዘጉ
የትግራይ ኃይሎች አባላት ዛሬ ለ3ኛ ቀን መንገዶች ዘጉ

የትግራይ ኃይሎች አባላት ዛሬ ለ3ኛ ቀን መንገዶች ዘጉ

Update: 2025-10-15
Share

Description

የተለያዩ ጥያቄዎች በማንሳት ተቃውሞ እያደረጉ ያሉት የትግራይ ሐይሎች ሰራዊት አባላት ዛሬ ለተከታታይ ሶስተኛ ቀን በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች መንገዶች ዘግተው ውለዋል። የክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ የትግራይ ፀጥታ ሐይሎች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ያለው ረቂቅ ደንብ ለሚመለከተው አካል መምራቱ አስታውቋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በትግራይ ሐይሎች አባላት ከሞኾኒ እና ውቅሮ በኩል ወደ መቐለ የሚያስገቡ መንገዶች ተዘግተው ውለዋል።



ባለፈው ሰኞ መቐለ የጀመረው የትግራይ ሐይሎች አባላት የተቃውሞ ሰልፍ እና መንገዶች የመዝጋት እርምጃ ለተከታታይ ሶስተኛ ቀን በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ዛሬም ቀጥሎ ውሏል። ዛሬ ጠዋት ጀምሮ በትግራይ ደቡባዊ ዞን የሚገኙ የትግራይ ሐይሎች አባላት በሞኾኒ መንገድ በመዝጋት ወደ አላማጣ እንዲሁም ወደ መቐለ የሚደረግ የተሽከርካሪዎች ጉዞ አስተጓጉለው የዋሉ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ትላንት ሙሉቀን ተዘግተው የዋሉ ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ዓዲግራት፣ ውቅሮ እና አጉላዕ ከተሞች ወደ መቐለ የሚወስዱ መንገዶች ዛሬም ተዘግተው አርፍደዋል።



የደሞዝ ጭማሪ እና ሌሎች ጥቅማጥቅም ጥያቄዎች ያነሱ እነዚህ የትግራይ ሐይሎች አባላት ምላሽ እስኪሰጣቸው ድረስ በዚሁ ተቃውሞአቸው እንደሚቀጥሉም ሲናገሩ ቆይተዋል። የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት ፅሕፈት ቤት ትላንት ባሰራጨው መረጃ የፀጥታ ሐይሎቹ ጥያቄዎች እንደሚነዘብ በማስታወቅ የትግራይ ዓቅም በሚፈቅድ ሁኔታ የሰራዊቱ ጥያቄ ለመመለስ ጥረት እንደሚያደርግ ገልጿል።





የግዚያዊ አስተዳደሩ ምላሽ





ከዚህ በተጨማሪ የትግራይ ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ያሰራጨው መረጃ እንደሚያመለክተው ደግሞ የክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር ካቢኔ በዚሁ የትግራይ ሐይሎች ጥያቄዎች ጉዳይ ዛሬ ጥቅምት 5 ቀን 2018 ዓመተምህረት አስቸኳይ ስብሰባ ማድረጉ ያስታወቀ ሲሆን ሲዘጋጅ ቆየ የተባለ የትግራይ የፀጥታ ሐይሎች ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ረቂቅ ደንብ ወደሚመለከታቸው አካላት መምራቱ አመልክቷል።



ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ዛሬም በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች በሰራዊቱ አባላት መንገዶች ተዘግተው ውለዋል። ከውቅሮ እና ሞኾኒ ያነጋገርናቸው መንገደኞች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ሁኔታው ያስረዳሉ።



ከመኾኒ ያነጋገርናቸው ነዋሪ "ከሞኾኒ አላማጣ መስመር መውጫ ቻይና ካምፕ የሚባል አለ። እዛ ነው መንገዱን የዘጉት። ወደ አላማጣ ኩኩፍቶ የሚሄዱ መኪኖች ከዛ አካባቢ ተመልሰዋል። በተጨማሪም ከሞኾኒ ወደ መቐለ መስመር ገረብ አባ ሓጎስ የሚባል ድሮም ኬላ የነበረበት አከባቢ ሆነው መንገዱ ዘግተውታል" ብለዋል።



ተቃውሞው ቀጥሏል



የሰራዊት ከፍተኛ መሪዎች የመንገድ መዝጋት እርምጃው ለማስቆም ከመቐለ ቅርብ ርቀት በምትገኘው አጉላዕ ከተማ ተገኝተው የሰራዊቱ አባላቱ ማነጋገራቸው የተገለፀ ሲሆን፥ ይሁንና ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ መንገዶቹ ተዘግተው መቀጠላቸው ለማወቅ ችለናል።ይህ ሰሞኑን እየታየ ያለው የትግራይ ሐይሎች አባላት ተቃውሞ ከጥቅማጥቅም እና ደሞዝ በዘለለ በትግራይ ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ ማሳያ አድርገው የሚያቀርቡ ተንታኞችም በርካታ ናቸው። ከ2013 እስከ 2015 ዓመተምህረት ጥቅምት ወር ድረስ በትግራይ ሐይሎች እና የኢትዮጵያ መንግስት መካከል በነበረው ጦርነት የተዋጉት የትግራይ ሐይሎች አባላት፥ ከሰላም ስምምነቱ በኃላ ትጥቅ በማስፈታት እና ወደሰላማዊ ሕይወት በመመለስ ሂደት ወደ ማሕበረሰቡ የማቀላቀል ስራ ተጀምሮ የነበረ ቢሆንም፥ እነዚህ አሁን ላይ ተቃውሞ እያደረጉ ያሉት ግን በሂደቱ ያላለፉ እና አሁንም በመደበኛ የሰራዊት አደረጃጀት ውስጥ ያሉ ናቸው።



ሚሊዮን ኃይለሥላሴ



ነጋሽ መሐመድ



ታምራት ዲንሳ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የትግራይ ኃይሎች አባላት ዛሬ ለ3ኛ ቀን መንገዶች ዘጉ

የትግራይ ኃይሎች አባላት ዛሬ ለ3ኛ ቀን መንገዶች ዘጉ

ሚሊዮን ኃይለ-ሥላሴ