የአንድ ለአንድ እንግዳ ወ/ሮ ራኬብ መሰለ
Update: 2025-04-04
Description
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ወ/ሮ ራኬብ መሰለ ቀደም ባሉት ዓመታት ሕጻናት አድን በተባለው መንግሥታዊ ያልሆነ ዓለም አቀፍ ድርጅት በእስያ፣ ምዕራብ እና ማዕከላዊ አፍሪቃ ውስጥ ባሉ ከ16 የሚበልጡ ሃገራት በልጆችን መብት አማካሪነት አገልግለዋል። በዚሁ ዘርፍ የአቅም ግንባታ ሥራዎችንም ሢሠሩ ቆይተዋል። ደቡብ አፍሪቃ በፕሪቶሪያ ዩኒቨርሲቲ ግሎባል ካምፓስ አፍሪቃ ተቋም በሰብአዊ መብቶች እና በአፍሪቃ ዴሞክራሲዊነት መርኀግብር ከመጀመሪያዎቹ ተመራቂዎች አንዷ ናቸው። እንግዳችን ወ/ሮ ራኬብ መሰለ ሰኔ 18 ቀን 2013 ዓ,ም በምክር ቤት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽን ሆነው ተሹመዋል። ካለፈው ዓመት ሐምሌ አንስቶ እስከ ጥር 22 ቀን 2017 ዓ,ም ድረስም ኢሰመኮን ሲመሩ ቆይተው በሌላ ኃላፊ ተተክተዋል።
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ
Comments
In Channel