የደሞዝና ሌሎች ጥያቄዎችን ያነሱ የትግራይ ሐይሎች የተቃውሞ ትዕይንት በመቀለ
Update: 2025-10-13
Description
ዛሬ ሰኞ ጠዋት እነዚህ የትግራይ ሐይሎች አባላት ከካምፖቸው በመነሳት በሰልፍ ወደ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤት እና ሌሎች መንግሥታዊ ተቋማት አምርተው የነበረ ሲሆን፥ በቦታው ለጥያቄዎቻቸው ምላሽ አለማግኘታቸው ይናገራሉ።
የሠራዊት አባላቱ የደሞዝ ማሻሻያ እንዲደረግላቸው፣ ተለይቶ ለቀድሞ የክልሉ ልዩ ሐይል የተሰጠ ድጎማ ለእነሱም እንዲሰጣቸው እንዲሁም የመኖርያ ቤት እና ሌሎች ድጋፎች እንዲመቻችላቸው ይጠይቃሉ።
እነዚህ የትግራይ ሐይሎች አባላት መንገዶችመዝጋታቸውን ተከትሎ በርካታ የሕዝብ መጓጓዣ አገልገሎት የሚሰጡ ታክሲዎች፣ የጭነት መኪኖች እንዲሁም ሌሎች ተሽከርካሪዎች ወደ ኩሓ በሚወስድ መስመር ቆመው ይታያሉ። የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣና ወዳሉበት መጥተው እንዲያነጋግሩዋቸው የሚጠይቁት እነዚህ የሠራዊቱ አባላት፥ ይህ ካልሆነ መንገዶቹ ተዘግተው እንደሚቆዩ ተናግረዋል።
ሁኔታው ተከትሎ ከመቐለ አሉላ አባነጋ አየርመንገድ ጨምሮ በዛ መስመር ወደ መቐለ ማህል ከተማ የሚደረግ እንቅስቃሴ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ተስተጓጉሎ ይገኛል።
ጉዳዮን አስመልክቶ ከክልሉ ባለሥልጣናት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።
ሚሊየን ኃይለ ሥላሴ
ሸዋዬ ለገሠ
ታምራት ዲንሳ
Comments
In Channel