አንድ ለአንድ፤ ከአቶ ልደቱ አያሌው ጋር
Description
ከ30 ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ጉልህ ተሳትፎ ሲያደርጉ ቆይተዋል። ዛሬም አልታከቱም። እሳቸው ኢትዮጵያውስጥ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ለማምጣት የተሻለ መንገድ ነው ያሉትን የትግል ስልት ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ለማስረዳት ይጥራሉ። መርኀቸው በሌሎች በርካታ ሃገራት ውጤት አስገኝቷል የሚሉት ሰላማዊ ትግል ነው። ፖለቲካዊ እሳቤያቸውን በመጽሐፍ ሳይቀር አሳትመው ለአንባቢያን አቅርበዋል። በተለያዩ ጊዜያት ደጋግመው ታስረዋል፤ አሁን ደግሞ ለስደት ተዳርገዋል።
በ1960ዎቹ መጀመሪያ የተወለዱት አቶ ልደቱ አያሌው በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ ከወጣትነታቸው አንስተው ለዓመታት የዘለቁ ታዋቂ ፖለቲከኛ ናቸው። አቶ ልደቱ ከሦስት አስርት ዓመታት በዘለለው የፖለቲካ ተሳትፏቸውም በተለያዩ ፓርቲዎች ውስጥ ከአባልነት እስከ መሪነትና መስራችነት የዘለቀ ተሳትፎ እንደነበራቸው መረጃዎች ያመለክታሉ። በተለይም በ1997 ግንቦት ወር ከተካሄደው ምርጫ ቅስቀሳ ጋ በተገናኘ ለበርካታ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች እንደአነቃቂ መንፈስ የተወሰዱበት አጋጣሚም በብዙዎች ይታወሳል።አቶ ልደቱ በዚያው ልክ አወዛጋቢ ሆነው የታዩባቸው አጋጣሚዎች ቢኖሩም እሳቸው ተገቢና ትክክል ነው ያሉትን የፖለቲካ አስተሳሰብ በአደባባይ ከመግለጽ ወደ ኋላ ባለማለትም ዛሬም ቀጥለዋል። በመገናኛብዙሃን ቀርበው ሃሳባቸውን ለማጋራት ወደ ኋላ አይሉም፤ ሞጋችና አከራካሪ ጉዳዮችን ይጽፋሉ፤ አልፈው ተርፈውም መጽሐፍትን ለንባብ አብቅተዋል። የአንድ ለአንድ እንግዳችን ናቸው፤ ሙሉውን ቃለመጠይቅ ለማድመጥ የምድጽ ማዕቀፉን ይጫኑ
ሸዋዬ ለገሠ
ታምራት ዲንሳ