DiscoverDW | Amharic - Newsኤርትራና ሕወሓት ኢትዮጵያን ለመውጋት እየተዘጋጁ ነው ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት ከሰሰ
ኤርትራና ሕወሓት ኢትዮጵያን ለመውጋት እየተዘጋጁ ነው ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት ከሰሰ

ኤርትራና ሕወሓት ኢትዮጵያን ለመውጋት እየተዘጋጁ ነው ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት ከሰሰ

Update: 2025-10-08
Share

Description

የኤርትራ መንግሥት እና ሕወሓት "ፅምዶ" ብለው በጠሩት ሕብረት "በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ለመክፈት በዝግጅት ላይ ናቸው" ሲል የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ በጻፈው ደብዳቤ ላይ ከሰሰ። "በኤርትራ መንግሥት እና በሕወሓት መካከል ያለው ሽርክና ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ በጉልህ እየታየ መጥቷል" የሚለው ይህ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌድዮን ጢሞትዮስ የተጻፈው ደብዳቤ እነዚህ አካላት "እንደ ፋኖ ያሉ የታጠቁ ቡድኖችን በገንዘብ እየደገፉ፣ እያስተባበሩ እና እየመሩ ይገኛሉ" ሲልም ይወቅሳል። በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ አንድ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኝ ሁለቱ ሀገራት "አሁን ወደ ድርድር የሚገቡበት ዕድል የለም፤ ወደ ግጭትም ያመራሉ የሚል እምነት የለኝም" ብለዋል ሰሎሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ ተጨማሪ ዘገባ አለው



የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የላኩት ደብዳቤ ይዘት



የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ላይ ከፍተኛ አደጋ እየፈጠረ ያለውን ውጥረት ለመፍታት፣ ግጭትም እንዳይፈጠር ጠንካራ ቁርጠኝነት ማሳየቱን የሚያወድሰው በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞትዮስ የተጻፈው ደብዳቤ እስካሁን በተቋሙ በይፋ የተለቀቀ ባይሆንም ትክክለኛ መሆኑን ግን ከመሥሪያ ቤቱ ምንጮች አረጋግጠናል።

ደብዳቤው የኤርትራ መንግሥት ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት የምታደርገው ጥረት ሥጋት እንደፈጠረበት በመግለጽ ይህንን የጦርነት ዝግጅት የሚያደርገውም ኢትዮጵያን "ለማተራመስ" መሆኑን በመጥቀስ ይከሳል።



ሁለቱ ሀገራት "ጦርነት ውስጥ ይገባሉ የሚል እምነት የለኝም" ተንታኝ



በዚህ ጉዳይ ላይ ከዓለም አቀፍ ሕግ እና የዲፕሎማሲ ግንኙነት መርሆች መነሻ አስተያየት የጠየቅናቸው የዘርፉ ተንታኝ፣ የፀጥታው ምክር ቤት እነዚህን ኢትዮጵያ በተከታታይ የላከቻቸውን ደብዳቤዎች ተመልክቶ ኤርትራ ጥፋተኛ ከሆነች ርምጃ ሊወስድ እንደሚችል ጠቁመዋል። ይህ ማለት ግን የሀገሪቱን እውቅና የሚያስነፍግ አይደለም ብለዋል።



"ምናልባት ይህንን የፀጥታው ምክር ቤት መርምሮ እንደተባለው [ኤርትራ] ጥፋተኛ እንኳን ሆና ብትገኝ ወደ ማዕቀብ ነው የሚሄደው እንጂ ከዚህ በኋላ ሀገር የለሽም የሚል ውሳኔ ላይ ይደርሳል የሚል እምነት የለኝም" ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደብዳቤ "የኤርትራ መንግሥት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት በማክበር በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት መቆጠብ አለበት" ይላል። የሁለቱ ሀገራት ያለፉት ዓመታት መልካም ግንኙነት "በሕግ፣ በአሠራር፣ በዝርዝር ውይይት እና ድርድር ላይ የተመሰረተ ተቋማዊ አለመሆኑ" ውጥረቱን ማባባሱን የገለፁት ተንታኙ እንዲያም ሆኖ ጦርነት ውስጥ ይገባሉ የሚል እምነት እንደሌላቸው ገልፀዋል። "አሁን ወደ ድርድር የሚገቡበት ዕድል የለም። ምክንያትም ወደ ግጭት የሚወስዳቸውን መንገድ እየጠረጉ ነው ያሉት።"



ርዕሠ ብሔር ታዬ አጽቀ ሥላሴ በዚህ ዙሪያ ምን ብለው ነበር?



ኢትዮጵያ "ዕጣ ፋንታዋ እና መጻዒ እድሏ" ከዓባይ እና ከቀይ ባሕር ጋር በእጅጉ የተገናኘ ነው ሲሉ ሰኞ ዕለት የተናገሩት ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ "ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ፍትሕን ባልተከተለ መንገድ እና ሕዝብን ባላማከለ፣ ባላሳተፈ አግባብ ተገልላ ቆይታለች ብለዋል። መንግሥት ይህንን ለማስተካከል በመሥራት ላይ ይገኛል ያሉት ርእሠ ብሔሩ "ከሦስት ዐሥርት ዐመታት በኋላ" የባሕር በር ጉዳይ የዓለም አቀፍ የመነጋገሪያ ሀሳብ ማድረግ ተችሏል" ብለዋል።



አክለውም "የቀጣናችንን የጋራ የመልማት ፍላጎት ያገናዘበ ትብብር እና ትስስርን ለማጠናከር ዲፕሎማሲያዊ እና ሰላማዊ ጥረቶች ይደረጋሉ" ሲሉ "የአካባቢያችንን ሰላም ለማረጋገጥ አለመግባባቶችን በዲፕሎማሲያ መንገድ ለመፍታት መንግሥት አበክሮ ይሠራል" ብለው ነበር።

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደብዳቤ "ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ገንቢ ግንኙነት እና ትብብር እንዲኖር ለማድረግ የሚያደርገውን ጥረት እንዲቀጥል" ሲልም ጥሪ አቅርቧል።



በፕሬዝዳንቱ ንግግር ላይ የኤርትራ ምላሽ



የኤርትራ መንግሥት የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በኤክስ በሰጡት ምላሽ የፕሬዝዳንት ታዬን ንግግር "ግራ የሚያጋባ" እና "ለማሰብ የሚከብድ" ሲሉ አጣጥለውታል። ከዚህም አልፎ የኢትዮጵያን በቀይ ባህር በር የማግኘት ፍላጎት "ቅዠት" በሚል ገልፀውታል። ጉዳዩ በብዙ ነውጦች እና ችግሮች በሚታመሠው ያሉት የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ላይ "አላስፈላጊ" እና "ሊወገድ የሚችል" ግጭት የሚቀስቀስ ይዘት እንደሚኖረው ጠቅሰዋል።





የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኝ አስተያየት



የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተንታኙ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት የመሆን እና የባህር በር የማግኘት መብትን መደበላለቁን ገልፀው የባለቤትነት ሀሳብ ለውዝግብ መነሻ ከሆኑ ጉዳዮች እንዱ መሆኑን ገልፀዋል። የባህር በር ማግኘት ግን በዓለም አቀፍ ሕግ መብት ነው ይላሉ። "ወታደራዊ ላልሆነ የንግድ ተግባር ወደብ አልባ ሀገራት እንዳይከለከሉ ዓለም አቀፍ አሠራርም አለ ልምድም አለ።" ጦርነት ምንም አማራጭ ሆኖ የሚቀርብ አይደለም ያሉት ባለሙያው የሁለቱ ሀገራት መንግሥታት የየሃገራቱን ታጣቂዎችን፣ በትጥቅም፣ በሰው ኃይልም የመደገፍ ሁኔታ ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉ ግን አመልክተዋል።



ከ4 ዓመታት በፊት ሁለቱን ሀገራት ወደ ሰላም ለማንጣት የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ጥረት ማድረጓ አይዘነጋም። አሁንስ መሰል ኃላፊነት ማን ሊወጣ ይችላል? የሚለውን የጠየቅናቸው ተንታኙ በቅድሚያ የአካባቢው ሰላም አለመሆን ጥቅሙን ሊጎዳበት የሚችል አካል ማን ነው የሚለው ሊመለስ ይገባል በማለት ምላሽ ሰጥተዋል። ከአውሮፓ ባለፈ ተንታኙ እንደሚሉት አዳዲስ የቀጣናው ተዋንያን የሆኑት እና በፉክክር ጎራ ውስጥ የሚገኙት ሳውዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ጥቅማቸውን በማሰብ እና በአካባቢው የበላይ ሆኖ የመውጣት መሻታቸውን በማለም ይህንን አካባቢ "የጦርነት ሜዳቸው እንዳያደርጉት ሥጋት አለኝ" ሲሉም መልሰዋል።



ሰሎሞን ሙጬ

ኂሩት መለሰ

ፀሐይ ጫኔ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

ኤርትራና ሕወሓት ኢትዮጵያን ለመውጋት እየተዘጋጁ ነው ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት ከሰሰ

ኤርትራና ሕወሓት ኢትዮጵያን ለመውጋት እየተዘጋጁ ነው ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት ከሰሰ

ሰለሞን ሙጬ