DiscoverDW | Amharic - Newsዶይቸ ቬለ ከአጭር ሞገድ ወደ ሳተላይት ፤የኢሠመኮ መግለጫ፤ የኒዩክሌር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሹመት የማኅብራዊ መገናኛ አውታሮች ቅኝት ዝግጅት
ዶይቸ ቬለ ከአጭር ሞገድ ወደ ሳተላይት ፤የኢሠመኮ መግለጫ፤ የኒዩክሌር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሹመት የማኅብራዊ መገናኛ አውታሮች ቅኝት ዝግጅት

ዶይቸ ቬለ ከአጭር ሞገድ ወደ ሳተላይት ፤የኢሠመኮ መግለጫ፤ የኒዩክሌር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሹመት የማኅብራዊ መገናኛ አውታሮች ቅኝት ዝግጅት

Update: 2025-10-16
Share

Description

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ ክትትል እና ምርመራ ባከናወነባቸው ቦታዎች በተለይም በአማራ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ እና በኦሮሚያ ክልሎች በሚጣሉ የሰዓት እላፊ ገደቦች፣ በየአካባቢው በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎች እና በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በመንገዶች ላይ በሚጣሉ ኬላዎች፣ የመንገድ መዝጋት ትዕዛዞች እንዲሁም በመንገዶች ላይ በሚደርሱ ጥቃቶች፣ እገታዎች፣ የንብረት ዘረፋዎች እና ውድመቶች የሰዎች ከቦታ ቦታ የመዘዋወር ነጻነት መብት አደጋ ላይ ወድቋል ሲል አስታውቋል።ኢሰመኮ እነዚህ እርምጃዎች እና ጥቃቶች ከመዘዋወር ነጻነት መብቶች ባሻገር በሕይወት የመኖር፣ የአካል ደህንነት መብቶችን አደጋ ላይ ጥሏል።



የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ድኤታ ከበደ ደሲሳ ለዶቼ ቬለ በሰጡት ምላሽ ኢሰመኮ የመንቀሳቀስ መብት በጣም የተገደበ አድርጎ፣ መንግሥት የሚያደርገውን እርምጃም እውቅና ሳይሰጥ ማለፉ ትክክል አለመሆኑን ገልፀዋል።መንግስት እርምጃ እየወሰደ ነው።ያሉት ሚንስትር ድኤታው ሁኔታው እየተሻሻለ መምጣቱንም አመልክተዋል። ይህንን ተከትሎ፤«አንዋር ዋሴ፤ከክልል ክልል ሳይሆን ከአንድ ከተማ ወደ ጉረቤት ከተማ 20 እና 30 ኪሎሜትር ለመጓዝ ምንም ዋሰትና የለም።» ብለዋል።ተመስገን ጉነርስ፣በበኩላቸው«ከክልል አይደለም ከዞን ዞን አይደለም ከወረዳ ወረዳ ከአንድ ሰፈር ወደ ሌላ መጓዝ ከባድ ሁኗል።»ሲሉ፤«እንኳን ህዝብ የመንግሥት ወታደር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው የሚያመላልሳቸው »ያሉት ደግሞ ገብረሂወት ሀብቴ ናቸው።ሲቪል ሶሳይቲ በሚል የፌስቡክ ስም የሰፈረው አስተያየት ደግሞ፤«ከቤት ወደሱቅ ለመንቀሳቀስ ተቸግረናል ኦረ የመንግስት ያለህ።»የሚል ነው።ቴዴ ማንአለ ደግሞ፤«እንኳን ሲቢል ማህበረሰቡ መከላከያው በአየር ነው የሚነቀሳቀሰው።»ብለዋል።ሳኒ ሳኒ በሚልስም የሰፈረው አስተያየት ደግሞ፤«መንግስትን ከመተቸታችሁ በፊት እስኪ በየሰፈራችሁ ያለውን ሽፍታ ኮንኑ በመጀመሪያ።»ይላል።አባይነህ መኩርያ በበኩላቸው፤«ከክልል ክልል ብቻ አይደለም ከወረዳ ወረዳ አይቻአልም የፌድራአሉ ዋና ከተማ ከናፈቀን ብዙ አመት ሆነዉ ።« ብለዋል።ፈረጃ ነኝ በሚል ስም የሰፈረው አስተያየት ደግሞ፤«መንግስት የጀመረውን የፀጥታ ማስከበር መደገፍ እንጅ ምንም ሳይሰሩ መንግስትን መተቸት አያዋጣም።» የሚል ነው።የሳቸውን ሀሳብ በሚደግፍ መልኩ፤ቢኒ የአርሰናል ደግሞ «ልክ ነው ሰላም እና ፀጥታ ያለማኅበረሰቡ ድጋፍ በመንግስት ብቻ አይመጣም።»ብለዋል። ዳዊት ለገሰ፤«የእውነት እጅግ አሳሳቢነው በሁሉም ክልሎች የሚፈፀሙ ግድያዎች ወንጀሎች ጥፋት ፈፃሚዎም ደበዛቸው አይታወቅም ሕግም እየተከበረ አይደለም።»ብለዋል።



ዶይቸ ቬለ ከአጭር ሞገድ ወደ ሳተላይት የሚያደርገው ሽግግር



ዶይቸ ቬለ ከአጭር ሞገድ ወደ ሳተላይት የሚያደርገው ሽግግር ሌላው በዚህ ሳምንት በተለይም በግጅቶቻችን ታዳሚዎች ዘንድ በውስጥ መስመር ጭምር ብዙ አስተያየቶችን አድርሰውናል።

አማርኛን ጨምሮ በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን እና በድረገጽ በ32 ቋንቋዎች የሚያሰራጨው ዶይቸ ቬለ ከአጭር ሞገድ ወደ ሳተላይት እና ሌሎች ዲጂታል መድረኮች ሽግግር እያደረገ ነው ።

የዘመኑ ቴክኖሎጂ ሽግግር በርካቶችን ከራዲዮ ይልቅ ወደ ሳተላይት እና የዲጂታል አማራጮች ላይ እንዲያተኩሩ አድርጓል ። ዶይቸ ቬለ በኢትዮሳት ሳተላይት ማሠራጨቱን የሚቀጥ ሲሆን፤ ከጥቅምት 16 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ጀምሮ ግን በአጭር ሞገድ የሚተላለፈው የቀጥታ ሥርጭት የሚቋረጥ ይሆናል።ከሳተላይት ባሻገር የቀጥታ ሥርጭቶቹን በፌስቡክ፤ ቴሌግራም እና ዩቱዩብም ያስተላልፋል ።



ይህን ተከትሎ ዳንኤል ማሜ የተባሉ አስተያየት ሰጪ «ግን ለምን? » ሲሉ ጠይቀዋል።አቤል ዳኛው በበኩላቸው፤ «አዝናለሁ የምር የገጠሩ ገበሬ ካሁን በኋላ እንዴት አንደሚሆን እኔን ጨምሮ ሁላችንም ንን የምናዝነው። ትልቅ አዛውንት እንደሞተ ነው የምቆጥረው።ቻው ሰላሙን ያብዛላችሁ!!!» የሚል አስተያየት አስፍረዋል። ሙለታ ዳርጌ«ጥሩ»ብለዋል በእንግሊዥኛ።

ሃና ሳሙኤል «ይሁን ዘመኑ ያመጣው ነው» ሲሉ፤ አለማሽ ነኝ ደግሞ፤«ታክሲ ላይ ቤት ውስጥ ያሉ እናቶች ስራ እየሰሩ የሚያዳምጡት በሬዲዮ ነበር።ያሳዝናል። ብለዋል። ዘቢባ ማሩ ደግሞ፤ከመፃህፍት ንባብ ወጣን አሁን ደግሞ ስራ እየሰራን ከምናዳምጠው ሬዲዮ ልንርቅ ነው።አይ ዘመን ።ሁሉም ነገር ወደ ሶሻል ሚዲያ። »የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።«የገጠሩ ህዝብ አያሳዝናችሁም።ሳተላይት የምትሉ እንኳን ሳተላይት ሬዲዮ ያለው ሰው ጥቂት ነው።»ያሉት ደግሞ አስተዋይ ማሞ ናቸው።ዳዲ ዳዲሞስ በሚል ስም የሰፈረው አስተያየት ደግሞ፤«ከዶቼ ቬለ ራዲዮጋር ብዙ ትዝታ አለኝ። አሁን ያን መልካም ትዝታ ይዞብኝ የሄደ መሰለኝ ።» ይላል።አበበልኝ ማሩ፤ እኔ እንኳ እኔኳ ከ1997አም ጀምሮ ነዉ የምከታተለው! 'የመሃበራዊ ሚዲያ ቅኝት' እና በነጋሽ መሐመድ የሚቀርበው 'መሃደረ-ዜና' የእስፖርት ዝግጅት እና የዓለም ዜና ልዩ ነበሩ!ብለዋል።ማንከልክሎት የተባሉ አስተያየት ሰጪ ደግሞ፤«በጣም ደስ ይላል ።ሰዉ በሁሉም አማራጭ እዉነተኛና ወቅታዊ መረጃዎችን ብያገኝ።ብለዋል።አብዱ ፍቅር ፤ደግሞ ወደ ቴሌቨዥን አሣድጉልን። የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።



ኡመድ አፔክ ኦኬሎ በበኩላቸው፤«ቢ ያንሰ ከ25 አመት በላይ DW አዳምጫለዉ (ተከታትያለሁ )በዘመነ ሬድዮ በጣም ነበር የሚከታተለዉ።የማልረሳው መንግሥት የማይወደዉ ፖሮግራም ከሆነ ጃም ሲያደርግ ከሆነ እንደት እንደሚያበሳጭኝ ትዝ ይለኛል።ያነ ከ11:00 ሰዓት የነበረው ፕሮግራም ተለወጦ አሁን የ1:00 ሰዓት ዜና በሞባይል ጃም የማይደረግበት እንዲሁም ዜና ና ሌላ ፕሮግራም ቢያመልጥም ተመልሶ ማዳመጥ የምትችልበትን ሁኔታ መኖሩ በጣም ያስደስታል ።«»የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።ሙስጠፋ ሙዜየም አብዱልከሪም፤«ምንም እንኳን ትንሽ ልጅ ብሆንም በደርግ ዘመን በተለይ የደርግ ማብቅያ የመጨረሻ አመታት ላይ ይደረግ ስለነበረው ጦርነት ታማኝ ምንጭ የጀርመን ድምፅ እና ቪኦኤ ነበሩ። አቤት ጣቢያውን ፈልጎ ለማግኘት ይደረግ የነበረው ውጣ ውረድ እንዴት ከበድ እንደነበረ ትዝ ይለኛል። ጋሽ ነገሽ ያኔ የኢትዮጵያ ሬድዮ ላይ ነበር የሚሰራው።»እስቲ ጋሽ ነጋሽ መሐመድን ጠቁልኝ እሱም እንደኛ ታማኝ ምንጭ ፍለጋ ዲ ዴብልዩን ይከታተል ነበር? ሲሉ ጠይቀዋል። የዝግጅታችን ተከታታይ መልሱን በሚቀጥለው ሳምንት በምናቀርበው ልዩ ዝግጅት ላይ ይጠብቁ።



የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር ሹመት



የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር ሹመት ፤ሌላው በዚህ ሳምንት በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች መነጋገሪያ የሆነ ጉዳይ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቶ ሳንዶካን ደበበን የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር አድርገው ጥቅምት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጥቅምት 4 ቀን 2018 ባካሄደው 49ኛ መደበኛ ስብሰባ በኮሚሽኑ ማቋቋሚያ ደንብ ላይ በመወያየት ደንቡ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ውሳኔ አሳልፏል።ይህንን ተከትሎ ካሳ ያለው «ኮንግራ!!!መልካም ስራና ውጤት እንመኛለን!!! ብለዋል።ሰውለሰው ቢኖር፤«ሠላም ሚኒስትር ከመጣ ወዲህ ሰላም ጠፋ ኒውክለር ኮሚሽነር ሲሾምስ?ደግሞ እንጃ,»ብለዋል።ኖካፕሽን ኒድድ በሚል ስም ደግሞ፤«ፓሊስ ጣቢያ እና ጤና ጣቢያ የተምታታበት አገር።»ብለዋል።ገብረመድህን ኪዳኑ፤«መልካም የስራ ዘመን ይሁንሎት ኢ/ ያ ችን ወደፊት።»አሸናፊ አስራ፤«ሀገር (ህዝቧ) የምትፈራው የምትከበረው ባላት የጦር አቅም ነውና በምንችለው ሁሉ እናግዛለን።»ብለዋል።



ዩሀንስ ገላው፤«በችግር አናልቅ ስንላችሁ በሳቅ ልገሉን ይሆን።»ብለዋል።ቤዛዊት ያሬድ ግን ፤Food science የተማረውን ልጅ ኑክሌር ትንሽ አይከብድም?በማለት ተሿሚው ላይ አንስተዋል።ገነት ዳኛው፤«ሐሳቡ ጥሩ ነው ግን እንደዚህ በመሸፈን እሳትን ማጥፋት ይቻላል ወይ።አሁን የሚያስፈልገው ከገባንበት እልቂት ማትረፍ የሚችል እውነተኛ ተቋም ነው።» ሲሉ፤ዜድ የሼባው፤ «ኒውክሊየር ምንድ ነው የምግብ አይነት ነው »ብለዋል። ፍራ ጀማል፤«ኢትዮጵያ የኒውክሊየር ጦር መሣሪያ መያዝን ማምረትንና መጠቀምን የሚከለክለው አለምአቀፋዊ ህግ ፈራሚ ናት። አንዳንዴ ያንቀለቅለናል ልበል? ያስቸኩለናል ልበል?በነገራችሁ ላይ የፃፍኩት ነገር ከሠላማዊው የኒውኪለየር ሃይል ጋ አይገናኝም። » ብለዋል።

ሳሚያ የእናቷ ደግሞ፤«ስለጦርነት ስለማፈንዳት የምታወሩ ሰዎች ግን፤ምናችሁን ነው ያመማችሁ ኑክሌር ለሰላም ነው የተባለው።ለህክምና ለኤለክትሪክ እና ለሌሎችም።ለምን መከራ ትጠራላችሁ ።»ብለዋል።





ፀሐይ ጫኔ

ታምራት ዲንሳ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

ዶይቸ ቬለ ከአጭር ሞገድ ወደ ሳተላይት ፤የኢሠመኮ መግለጫ፤ የኒዩክሌር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሹመት የማኅብራዊ መገናኛ አውታሮች ቅኝት ዝግጅት

ዶይቸ ቬለ ከአጭር ሞገድ ወደ ሳተላይት ፤የኢሠመኮ መግለጫ፤ የኒዩክሌር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሹመት የማኅብራዊ መገናኛ አውታሮች ቅኝት ዝግጅት