ቃለ መጠይቅ፣ የወደብ ጥያቄ፣ የዉጪ ጣልቃ ገብነት፤ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የህወሓት መሪዎች ባሕሪ---
Description
ኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ህወሓት የገጠሙት ዉዝግብ እየተከራረ ነዉ።የኢትዮጵያ መንግሥት የአሥመራና የመቀሌ ገዢዎች ኢትዮጵያን ለመዉጋት እየተዘጋጁ ነዉ በማለት ሲወቅስ፣ ሁለቱ ወገኖች ደግሞ የኢትዮጵያ መንግሥትን ይከሳሉ።ሶስቱም ኃይላት ከቃላት መወቃቀሱ በተጨማሪ ወታደራዊ ዝግጅት እያደረጉ ናቸዉ የሚሉ ወገኖችም አሉ።ግብፅና የተባበሩት አረብ ኤሚሮቶችም የአሥመራና የአዲስ አበባን መሪዎች በመደገፍ ጠቡን እያባባሱት መሆናቸዉ እየተነገረ ነዉ።የአፍሪቃና የመካከለኛዉ ምሥራቅ ጉዳይ የፖለቲካ ተንታኝ አብዱረሕማን ሰይድ እንደሚሉት የአዲስ አበባና የአሥመራ መሪዎች ባሕሪም ልዩነቶችን በድርድር ለማስወገድየሚመች አይመስልም።የጠቡን ምክንያት፣ ያለበትን ደረጃ፣አጥማሚያዉን በተመለከተ አቶ አብዱረሕማንን አነጋግረናቸዋል።ሙሉ ቃለ መጠይቁን ያድምጡ።
የጥቅም ጋብቻ- marriage of convenience
«በሁለቱ መካከል ያለዉ ግንኙነት በሰላም ተደራድሮ የመፍታት አቅሙም ፍላጎትም ያላቸዉ አይመስልም።---የ(ጠቅላይ ሚንስትር) ዓብይ አሕመድና የፕሬዝደንት ኢሳያስ ስምምነት በ2018 በፈረንጆች አቆጣጠር የተደረገዉ---ያኔ ሥጋት ነበር።የጥቅም ጋብቻ እንዳይሆን፣ በእንግሊዝኛ marriage of convenience ይላል የሚል ሥጋት ነበር----ጥቅሙ ምንድነበር በዚያን ጊዜ ያገናኛቸዉ የህወሓት ኃይል ለሁለቱም ሥጋት ሆኖ ሥለቀረበ ነበር።»
«---Infact ወደ 80% የኢትዮጵያ አቅም ትግራይ ዉስጥ እንደነበር ይታወቃል።ይሁንና ሥምምነቱ ራሱ marriage of convenience ቢሆንም ወደዛ የገፋቸዉ፣ ለሁለቱ ሐገሮች ጥቅም መዋል ይችል ነበር።»
የፖሊሲ ስሕተት
«ከዚያ ቀጥሎ ግን (የኢትዮጵያ መንግሥት) ለፋኖም ብዙ ጊዜ ሳይሰጥ፣ ሳይደራደር ትጥቅ ማስፈታት በሚል ወደ ግጭት ተገባ ማለት ነዉ በጠቅላይ ሚንስትሩ ከኤርትራ ጋርም ያልነበሩ ጉዳዮች እንደ የወደብ ጉዳይም----እያነሱ ናቸዉ።»
«-እዚሕ ላይ እንግዲሕ የፖሊሲ ስሕተት አለ።እሱን ለማስተግበር ደግሞ ወደ ወታደራዊ ግጭት ለመግባት እንደሚፈለግ----የዉጪ አጀንዳ እዚሕ ጉዳይ ላይ ኃይለኛ ቦታ እንዳለዉ የሚያሳይ ነዉ።በተለይ በኢማራቶቹ፣ ቀጥሎም በእስራኤሎች---ኢማራቶች እዚያ አካባቢ ያሉ ስትራቴጂክ ወደቦችን አደን፣ ጅቡቲ፣ አሰብን ለመቆጣጠር ብዙ እንደሚፈልጉ-- ሱዳን፣ ሊቢያና ሶሪያ ላይም ----»
የአቡዳቢዎች ጣልቃ ገብነትና ጥቅም
«---በኢትዮጵያና በኤርትራ ባለዉ ግንኙነት፣ እነሱ (UAE)ባሁኑ ጊዜ ምናልባት ጠቅላይ ሚንሥትር ዐብይ አሕመድ የኛ ነዉ፣ የኛ ልጅ ነዉ።እንደ,ፈለግን ወደ ቀኝና ግራ ልናዞረዉ እንችላለን።በዚያ ላይ ደግሞ ኢትዮጵያ ከአፍሪቃ ቀንድ ሴንትራል ናት፣ ኢትዮጵያን ተቆጣጥሮ የአፍሪቃ ቀንድን መቆጣጠር እንችላለን በሚል ሊሆን ይችላል።»
የኢትዮጵያና የኤርትራ መሪዎች አንድም-ሁለትምነት
«አካዳሚካሊ ሲታይ፣ ከደጋ የሚመጡት መሳፍንት ሲከተሉት የቆዩት ዚሮ-ሰም ጌም፣ አንዱን አንዱ አሸንፎ ሥልጣን የመጨበጥ ባሕል አለ።ይኸ ባሕል የኢትዮጵያም ይሁን የኤርትራ ደገኞች ሥለሚቆጣጠሩት ከዚሕ ባሕል የወጡ (የተላቀቁ) አይደሉም።---»
«---ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ሲመጡ፣ የፕሬዝደንት ኢሳያስ መልዕክት ለወያኔዎች ጌም ኦቨር የሚል ነዉ።እኔ አሸንፌያችኋለሁ፣ ካሁን በኋላ እኔነኝ ሱፐር ፓወሩ።ዐብይም የኔ ተላላኪ ሆኖ ሊሰራ ይችላል የሚል ተስፋ አ,ድርጎ ነበር መሰለኝ ፕሬዝደንት ኢሳያስ---ዐብይም ባንድ ጉብኝታቸዉ አሥመራ ዉስጥ እኔ የኢትዮጵያና የኤርትራ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ሆኜ እሰራለሁ፣ ኃላፊነቱን (ፕሬዝደንትነቱን) ላንተ ሰጥተንሐል ብሎ---»
የወደብ ጉዳይ
«በዓለም ሕግ አንድ ወደብ የሌላት ሐገር (በቅርቧ) ያለ ወደብን የመጠቀም መብት አላት።ኢትዮጵያም የ,ኤርትራ፣ የጅቡቲ፣ የኬንያ ይሁን የሱዳን ---ወደብ የመጠቀም መብት አላት---ኢትዮጵያ ወደብ ስትጠቀም ተጠቃሚዋ ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን ወደብ ያላቸዉም ሐገራት ናቸዉ።---»
«---ኤርትራ ነፃ እንደወጣች ኢትዮጵያ አሰብን በነፃ እንድትቀም የሚል አዝማሚያም ነበር።---ኢትዮጵያ ከጎረቤት አገሮች በተለይም ከኤርትራ፣ ጅቡቲና ሶማሊያ ጋር አብራ ማደግና መጠቀም ትችላለች።አንድ የጥምረት ኮንፌደሬሽን ነገር---የሆርን ኦፍ አፍሪቃን ዩኒየን መመሥረት ትችል---»
ነጋሽ መሐመድ
ታምራት ዲንሳ