DiscoverDW | Amharic - Newsየድኅነት መባባስ፣ ቅጡ ያለየው የኢትዮኤርትራ ግንኙነት፣ የሙቀት ማዕበል
የድኅነት መባባስ፣ ቅጡ ያለየው የኢትዮኤርትራ ግንኙነት፣ የሙቀት ማዕበል

የድኅነት መባባስ፣ ቅጡ ያለየው የኢትዮኤርትራ ግንኙነት፣ የሙቀት ማዕበል

Update: 2025-07-03
Share

Description

የድኅነት መባባስ፣



ግጭት እና አለመረጋጋት ኢትዮጵያን ጨምሮ በ39 ሃገራት ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ የዓለም ባንክ አስታውቋል። የዓለም ባንክ መረጃ በሃገራቱ ግጭት እና አለመረጋጋቱ ከየትኛውም የዓለም ክፍል በባሰ ሁኔታ ድህነት እና አስከፊ ረሐብ ማባባሱን እና በርካታ ቁልፍ የልማት ግቦች ወደ ማይደርሱበት ደረጃ መግፋቱንም ጠቁሟል።



ይህን መረጃ ከተመለከቱት መካከል፤ ባዬ ጌታው በፌስቡክ፤ «ትክክለኛ ዘገባ ነው እኔ ኢትዮጵያ እያደገች ነው የሚለውን አልቀበለም ምክንያቱም 80 በመቶው የኢትዮጵያ ሕዝብ በቀን ሁለት ጊዜ ለመመገብ ተቸግሯል» ብለዋል። በላይነህ አፕ በበኩላቸው፤ «አልታወጀም እንጂ በሌበራል ዲምክራሲ ስርአት ውስጥ ስላለን ነው። ይህ ማለት አጠቃላይ ስርዓቱ በሀብታምች የበላይነት የሚመራ ማለት ነው።» ባይ ናቸው።



የውብነህ ዋይ ለማ የተባሉት የፌስቡክ ተጠቃሚ ግን፤ «እኛ ሚራክል ላይ ነን አይመለከተንም» ሲሉ፤ የእሳቸውን የሚጋሩት ደግሞ ሞሀ ለስላሳ፤ «አብይ አድገናል ብሏል፤ ብሏል በቃ» ብለዋል።



አማረ ዶርና፤ «አሁን እውነቱ ይፋ ሆነ በውሸት ሪፖርት ሕዝብን ሲያተራምሱና ሲያወዛግቡ ነበር! ለዚህ ነው ከመፈክሩ ይልቅ በተግባር እናሳይ የምንለው። ቡና አንድ ሲኒ 100 ብር ገብቶ በለፀግን ነው የሚባል? እዩት ትዝብቱን።» ይላሉ።



ጌታቸው መለኬ፤ እንዲህ አሉ፤ «እኔ የመንግሥት ሠራተኛ ነኝ የዛሬ አምስት ዓመት ደሞዜ 8,017 የሚደርሰኝ 5,925 ነበር። ፓስታ የምገዛው አንዱን 40 ብር ነበር አሁን ግን ከ 100 ብር በላይ ነው መንግሥት የኢኮኖሚ ማሻሻያ አደረግሁ ብሎ አሁን በእጄ የሚደርሰኝ 6445 ነው። እንግዲህ በትንሹ የፓስታውን ነገር ስናነፃፅር በጣም ይከብዳል ። አሁን ደግሞ የጤፍ ዋጋን ከአምስት ዓመት በፊት ከነበረው ጋር ስናነፃፅር አንድ ፈረሱላ ጤፍ 560 ብር ነበር አሁን 1900 ብር በላይ ነው። ይህ ነው እንግዲህ ለመኖር በጣም የተቸገርነው መንግሥት ደግሞ እድገታችን ሚራክል ነው እያለ ይደሰኩርብናል።» ብለዋል። ጌቾ የማ ልጅ ደግሞ፤ «መንግሥት እኮ ኢኮኖሚው አድጓል ሕዝቡ ነው እንጅ ደሃ» ነው የሚሉት። ይህም ያልፋል በበኩላቸው፤ «የኛ ሀገር እኮ ሚራክል ስለሆነ ስለማይታይ ነው እንጅ በጣም በጣም ነው ያደግነው... እየው ኑሮ ከመርከሱ የተነሳ እርስ በእርሳችን እየተዋጋን አደል።» ብለዋል። ዘመን ማረው ደግሞ፤ «የኢትዮጵያ እድገት አፈሳ፡ እገታ፡ ጦርነት፡ ዘረኝነት፡ ለሥልጣን መጋጋጥ፡ ባህልን፡ ቅርስን፡ እምነትን ከሀገር ማጥፋት ሲሆን በዚህ ሁሉ መከራ ግን እግዚአብሔር ሁሌም ከጎናችን ነው» የሚል አስተያየታቸውን አጋርተዋል።



እኔም አየሁ የተባሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ፤ «ዐይናችሁን ግለጡ ኢትዮጵያ እያደገች ነው።» አሉ፤ ለእሳቸው አስተያየት ምላሽ የሰጡት ዮርዲ ካፕቲመር ደግሞ፤ «ሰው እንደቀጥል እየረገፈ ነው እንዴ ምታድገው አረ እንደ ሰውኛ እናስብ» ሲሏቸው፤ ስለሺ ነዝጋም፤ «መንግሥት ብቻውን ያድጋል ማለት ነውውውውውውው?» በማለት ነውን በጣም አስረዝመው ጠየቁ።



ገመቹ ለታ ደግሞ፤ «ለዚህ ትልቁ IMF ነው ሚናውን የተጫወተው» አሉ። ከፌ ኃይሉም፤ «ይኼ የዓለም ባንክ ራሱ አደኽይቶን ራሱ ደግሞ ድህነት እየተስፋፋ ነው ይለናል እንዴ ?» ነው የሚሉት። የጥንት የጥዋቱ የተባሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ ግን፣ «ተውን ባካችሁ በልፅገናል» ሲሉ አስተያየታቸውን በሳቅ አጅበው አካፍለዋል። አብነት አለማየሁ ደግሞ « ይሄን መርዶ የብልፅግና ደሴት ነዋሪዎች ሰምተውት ይሆን» በማለት ጠይቀዋል።





ቅጡ ያለየው የኢትዮ- ኤርትራ ግንኙነት፣



የኢትዮ-ኤርትራ የሕዝብ ለሕዝብ የድንበር ግንኙነት በትግራይ በኩል እንደ አዲስ መጀመሩ ሰሞኑን ተሰምቷል። በሌላ በኩል በያዝነው ሳምንት ደግሞ የአሜሪካ የሰብአዊ መብት ተመልካች ተቋም ኤርትራ ወታደራዊ ኃይሏን እያጠናከረች ለጎረቤት ሃገራት ስጋት በተለይም ለኢትዮጵያ የውስጥ አለመረጋጋት አስተዋጽኦ እያደረገች ነው የሚል ዘገባ አውጥቷል።



ዳዊት ለጊ ፈንታው፤ «የኤርትራ ወገን ሕዝብ ከትግራይ ወገን ሕዝብ ጋር የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ማድረጋቸው በመርህ ደረጃ ችግር የለውም መልካም ነው። በፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና በጠ/ሚር አብይ አህመድ መካከል የሐሳብ አለመግባባቶች ይታያሉ በየሀገራቸውም ኡሉታዊ ተፅኖ እየፈጠረ በቃላት ጦርነት ወንጀላዎች እየተስፋፉ ነው። ከዚህ አኳያ ሀገር ከክልል ጋር ግንኙነት መፍጠሩ ጤንኝነት የለውም ወይም ሕጋዊ አሰራሩን ሉአላዊነትን ያከበረነው ብየ አልወስድም።» ሲሉ አስተያየታቸውን አጋርተዋል። አሌክስ ተቻል ደግሞ፤ «ሕዝብ ለሕዝብ ሰላም ሲፈጥርና ሲገናኝ ደስ የማይለው በውስጡ ክፉ መንፈስ የወረሰው ሰው ብቻ መሆን አለበት:: በሁሉም አቅጣጫ ሕዝቦች ከአጎራባች ሕዝቦች ጋ እንዲህ ቢገናኙ ሰላምና እድገት ይፈጠራል::» ባይ ናቸው። ሀገሬ ጥሎብኝ እወድሻለሁ የተባሉ የፌስቡክ ተጠቃሚ ግን፤ «ግንኙነቱ ባልከፋ በውሥጡ ያዘለው ከሳተ ገሞራ የላቀ ቂም በቀል ፈንድቶ የእልቂት ማአበል ባላጥለቀለቀን?!» ይላሉ።



ፈኬሲቱ ፊ ሀቱቲ ቶልቴ ደግሞ፤ «ለመልካም ነገር ቢሆን ጥሩ ነበረ። 27 ዓመት ሙሉ ስለ ጠላትነት ሲያወሩ የነበሩ ሰዎች ዛሬ ምን ሰምተው ነው ይህንን የጀመሩት ነው ዋናው ጥያቄ።» ሲሉ አሊ ሃሙድ ግን፤ «መጠፋፋት እንደገና ወዳጅነት የተለመደ ነው፤ ለእነሱ አዲስ አይደለም።» ነው ያሉት።



የኤርትራ ሠራዊቷን እያጠናከረች ነው የሚለውን በተመለከተ አሊ ፒካሶ አላዝ፤ «የራሳቸውን ሠራዊት ማጠናከር መብት አላቸው። እንዲያ ከተባለ ደሞ አብይም የሚገነባው ሠራዊት ለኤርትራ ስጋት ይሆናል ማለት ነው።» ሲሉ አስተያየታቸውን አጋርተዋል። እልፍነሽ ዘውዴ ደግሞ፤ «ወይ የድሀ ልጅ አለቀለት» ነው ያሉት። ሴፊየስ 16 በበኩላቸው፣ «ሕዝባችን ተሰቃየ ኃላፊነት በጎደላቸው መሪዎች። ጦርነት ምንም ጊዜ ቢሆን ዘለቄታዊ መፍትሄ አያመጣም/ አያስገኝም።» ሲሉ መሀመድ አብደላ ደግሞ፤ «አትረበሹ ! ሴራቸው ይታወቃል ። ወንድም ሕዝቦች ነን ። አንዋጋም» ብለዋል።



የሙቀት ማዕበል



ሰሞኑን የሙቀት ማዕበል ብዙዎችን እያስጨነቀ ነው። በበርካታ የአውሮጳ ሃገራት 40 እና ከዚያ በላይ ዲግሪ የደረሰው የሙቀት መጠን ሰዎችን ላብ በላብ እያደረገ ነው። ዶክተሮች እንደገለጹት ከሆነ ከሙቀት ጋር በተያያዙ ችግሮች በድንገተኛ ክፍል የታከሙ ሰዎች ቁጥር በ 10 በመቶ ጨምሯል።





ሙቀቱ ያንገሸገሻቸው የሚመስሉት ፀጋዬ በለጠ፤ «በጣም ከብዷል» ሲሉ መኪን መሃመድ፤ «አቦ ይሙቃችሁ ለምን እኛ ብቻ ?!» ብለውናል፤ ደስታው መንግሥተአብ አሰግድ፤ «ዋይይይ የሰሞኑ ሙቀት ሳኡዲዎች እንዴት ነው ከእናንተ?» በማለት ጠየቁ፤ ሙኤ ፈክር ደግሞ፤ «40 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ብርቅ ነው እንዴ? እኛ ጋ እራሱ አረብ ሀገር፤ 50 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ነው» አሉ፣ በእርግጥ እዚህ 37 እና 38 ዲግሪውን ለጥቂት ቀናት ብዙዎች መቋቋም እንዳቃታቸው አስተውለናል፤ 50 ዲግሪውን ለማሰብ ይከብዳል። ዓመቱን ሙሉ ከፍተኛ ሙቀት ባለባቸው ሃገራት ለሚኖሩ ጽናቱን ይስጣቸው። ከእነዚህ ወገኖች አንዱ የሚመስሉት መቼ ነው በቃ የሚለን የሚል የፌስቡክ ስም ያላቸው አስተያየት ሰጪ፣ «አረብ አገር አይወራ ተቃጠልን ወይ አገሬ መቼ ነው የምትጠሪኝ» ነው ያሉት። ሄለን ዘማሪያ ግን፤ «ከከባድ ብርድ ሙቀት ይሻላል ልብስ መቀነስ ነው» ባይ ናቸው። ግን ከከባድ ሙቀትና ከኃይለኛ ብርድ የቱ ይሻል ይሆን? በዚህ መሀል ግን አቤል ካህሳይ፤ «እኔ ደግሞ እዚህ ኑሮ ውድነት ላብ በላብ እያደረገኝ ነው» ብለውናል።



ሸዋዬ ለገሠ



ነጋሽ መሐመድ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የድኅነት መባባስ፣ ቅጡ ያለየው የኢትዮኤርትራ ግንኙነት፣ የሙቀት ማዕበል

የድኅነት መባባስ፣ ቅጡ ያለየው የኢትዮኤርትራ ግንኙነት፣ የሙቀት ማዕበል