DiscoverDW | Amharic - Newsመንግስት አስገዳጁን የቦንድ ጊዢ መንሳትና ገቢን የማሳደግ አማራጭ መንገድ
መንግስት አስገዳጁን የቦንድ ጊዢ መንሳትና ገቢን የማሳደግ አማራጭ መንገድ

መንግስት አስገዳጁን የቦንድ ጊዢ መንሳትና ገቢን የማሳደግ አማራጭ መንገድ

Update: 2025-07-03
Share

Description

የመንግስት አስገዳጁን የቦንድ ጊዢ መንሳትና ገቢን የማሳደግ አማራጭ መንገድ



የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በአገሪቱ ውስጥ በሚገኙ የንግድ ባንኮች ላይ ለሁለት ዓመት ከስምንት ወራት ግድም ጥሎት የነበረው አስገዳጅ የግምጃ ቤት ቦንድ አነሳ፡፡ መንግስት ከጎርጎሳውያን 2022 ጀምሮ እንደ ገቢ ማግኛ ሲጠቀም የቆየው ይህ የቦንድ አሰራር ያነሳው በዓለምአቀፉ የገንዘብ አስተዳደር አሰራር በፋይናንስ ዘርፉ ላይ ያለፍላጎት የሚጣለው የትኛውም አሰራር ነጻነትን የሚጋፋ ነው ተብሎ በመታመኑ ነው ተብሏል፡፡ በሌላ መንገድ ግን ለሚቀጥለው የበጀት ዓመት መንግስት ገቢውን ለመጨመር አበክሮ እንደሚሰራ እየገለጸ ነው፡፡



ሰኞ ሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም. በበጀት ዓመቱ ሦስተኛ ስብሰባውን የተቀመጠው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ፤ በሁሉም የንግድ ባንኮች ላይ በአስገዳጅነት ተጥሎ የቆየውን የረጅም ጊዜ የመንግስት ቦንድ ግዢ ውሳኔን ያነሳው በገንዘብ ፖሊሲ ለውጥ ምክንያት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡



የመንግስት ቦንድ እንደ በጀት መሙያ



ከጥር ወር የጎርጎሳውያን 2022 ጀምሮ የመንግስት በጀት ጉድለት ማሙያ ስልት ተደርጎ የተቀመጠው ይህ አቅጣጫ በንግድ ባንኮቹ ዘንድ ምቾች ሳይፈጥር መቆየቱ ነው በባለሙያዎች የሚነገረው፡፡ የፋይናንስ አስተዳደር ባለሞያው አቶ አብዱልመናን መሀመድ በዚህ ጉዳይ ላይ ለዶይቼ ቬለ በሰጠጡት አስተያየት፤ “የግምጃ ቤት የሚሉት በግዴታ በንግድ ባንኮቹ ላይ የተጣለው ይህ የቦንድ ግዢ በጎርጎሳውያን 2022 ሲጣል ባንኮች ብድር በሚሰጡበት ጊዜ 20 በመቶውን ቦንድ እንዲገዙበት ይገደዱ ነበር” በማለት ዓለማውም የኢትዮጵያ መንግስት የብድር ምንጭ ሆኖ ማገልገል መሆኑን አመልክተዋል፡፡ ይህም የኢትዮጵያ መንግስት ከሚኖሩበት ወጪ አኳያ የበጀት ክፍተቱን ለመሸፈን የሚጠቀምበትነው ተብሏል፡፡ ባንኮችም በዚህ ጉዳይ ከመንግስት ጋር ስጨቃጨቁ ነበር ያሉት ባለሙያው በዓለማቀፍ የገንዘብ ተቋማት ህግ አስገድዶ ቦንድ መሸጥን ስለማያበረታታ፤ እንዳውም ነገሩን በፋይናንስ ተቋማት ስራ ጣልቃ በመግባት ነጻነታቸውን እንደመገደብ ነው ብሎ ስለሚመለከተው አሰራሩን አይደግፍም በማለት ገልጸዋልም፡፡የኢትዮጵያ የዩሮ ቦንድ ዕዳ ጉዳይ አነጋጋሪ ሆኗል



ከዚያም በፊት ከጎርጎሳውያን 2011 እስከ 2019 ድረስ በኢትዮጵያ ስራ ላይ የነበረው 27 በመቶ የተሰኘው ቦንድ በኋላም በዓለማቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጫና እንዲነሳ እስከተደረገበት ጊዜ ድረስ ስራ ላይ ይውል እንደነበርም ያነሱት የገንዘብ አስተዳደር ባለሙያው፤ አሰራሩ የፋይንንስ ተቋማቱን ነጻነት የሚገድብና የኢኮኖሚ ሪፎርምም ጋር እንደማይሄድ ታምኖበት ነው የተነሳው ብለዋል፡፡



የቦንድ ግዢው አስገዳጅነት መነሳት አንድምታ



አሁን ከዚህ ከተያዘው ሐምሌ ወር ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ይነሳል የተባለው ከሦስት ዓመታት በፊት ተጥሎ የቆየው የመንግስት አስገዳጅ የቦንድ ግዢው ከፍ ያለ አንድምታ ያለውም ነው ብለዋል፡፡ “አንደኛው አንድምታው የባንኮች የማበደር አቅምን ይጨምራል” ያሉት አብዱልመናን ባንኮች የሚገዙት ቦንድ ስለሌለ አሁን ማበደር የሚችሉት የገንዘብ አቅማቸው ይጨምራል ነው ያሉት፡፡ ሁለተኛው አንድምታው ባንኮች የብድር ምጣኔያቸውን ከፍ ስያደርጉ ገቢያን የማነቃቃት እድላቸው ከፍ ማለቱ አይቀረ ሆኖ ምናልባት ጥብቅ ሆኖ የሚቀጥለው የመንግስት የገንዘብ ቁጥጥር ፖሊሲ ግን በዚህ ላይ እንቅፋት ሊሆን እንደሚችልም ጠቆም አድርገዋል፡የግል ባንኮች ቦንድ እንዲገዙ ያስገድድ የነበረው መመሪያ ምን አሳካ?



ግብር እንደ አማራጭ የመንግስት ገቢ ማሳደጊያ ትኩረት



መሰል የመንግስት በጀት ጉድለትን መሙያ ቁልፍ ስልቶች በሚቀንሱበት በዚህ ዓመት መንግስት በከፍተኛ ሁኔታ ገቢውን ለመጨመር እንደሚሰራ እየገለጸ ይገኛል፡፡ እንደ ገንዘብ አስተዳደር ባለሙያ ይህ ማለት የአገር ውስጥ ገቢ በተለይም ግብር በከተኛ ሁኔታ ይሰበሰባል ማለት እንደሆነ ይጠቁማሉ፡፡ “ዘንድሮ የመንግስት ወጪ ጨምሯል፡፡ ይህ ማለት ደግሞ መንግስት ገቢውን ለመጨመር በከፍተና ሁኔታ ይንቀሳቀሳል ማለት ነው፡፡ ከዚህ በፊት መንግስት በጀት ስቸግረው ከብሔራዊ ባንክ መበደር ገንዘብ ወደማሳተም ነበር የሚሄደው፡፡ ካሁን በኋላ ግን ያ ስለሌለ መንግስት መፍትሄ አድርጎ የሚወስደው ከሚገኝ የተወሰነ ብድር በተጨማሪ ወደ ተለመዱት የአገር ውስጥ ታክስ ነው ለመሄድ የሚገደደው” በማለትም ከተለመዱትም የታክስ አሰባሰብ ዘዴ በተጨማሪ አዳዲስ እንደ ነብረት ታክስ በአይነትም በመጠንም ርብርብ በማድርግ ገቢን ለማሰባሰብ አቅዷልም ብለዋል፡፡ እንደ ባለሙያው አስተያየት ይህ ደግሞ በማህበረሰቡ ላይ ሌላ ጫና ይዞ መምጣቱ አይቀረ ነው፡፡ “በተዳከመ ኢኮኖሚ ላይ ይህን ሁሉ የግብር ጫና መጨመር የሚጎዳው ኢኮኖሚውን ብቻ ሳይሆን የህብረተሰቡንም ብሶት ነው የሚጨምረው” በማለትም መንግስት በትንሽ የግብር ስህተት እንኳ ከፍተኛ ቅጣት መጣሉ ለዚህ ቁርጠኝነት ማሳያ ነው ብለዋል፡፡





ሥዩም ጌቱ



አዜብ ታደሰ



ነጋሽ መሐመድ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

መንግስት አስገዳጁን የቦንድ ጊዢ መንሳትና ገቢን የማሳደግ አማራጭ መንገድ

መንግስት አስገዳጁን የቦንድ ጊዢ መንሳትና ገቢን የማሳደግ አማራጭ መንገድ

ሥዩም ጌቱ