DiscoverDW | Amharic - Newsየወሎ ላሊበላ የባህል ሙዚቃ ቡድን ከትናንት ዛሬ
የወሎ ላሊበላ የባህል ሙዚቃ ቡድን ከትናንት ዛሬ

የወሎ ላሊበላ የባህል ሙዚቃ ቡድን ከትናንት ዛሬ

Update: 2025-10-16
Share

Description

የወሎ ላሊበላ የባህል ሙዚቃ ቡድን





የባህል ሙዚቃን ከነሙሉ ክዋኔ እና ባህላዊ አልባሳትን ቱባውን ባህል ለህዝብ በማስተዋወቅ ረገድ በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ የጎላ ሚና የተጫወተው የወሎ ላሊበላ የባህል ሙዚቃ ቡድን በ1960ዎቹ አጋማሽ ነበር፡፡ በወሎ ክፍለ ሀገር ያሉ የባህላዊሙዚቃ ተጨዋቾችን በተለምዶ አዝማሪ የሚሰኙትን ባለሙያዎችን በማሰባሰብ የወሎ የሀገር ባህል ተጫዋቾች በሚል መመስረቱን የባህል ቡድኑ መስራች ድምፃዊ መሀመድ ይመር ከመከም ይናገራል፡፡





‹‹የተመሰረተው 1966 /ም የሀገር ባህል ተጨዋቾች ማህበርበሚል በየ ጠጅ ቤቱ የሚዘፍኑ አዝማሪዎችንተሰብስቦእኛም ከገበሬው መጣን፤ ለዋናው የላሊበላ ኪነት ቡድንምክንያት የሆነው 1969 /ም ሙያተኞችንመምረጥ ተጀመረ፤ 1971/ም በኋላ ሀገር አቀፍ መሆን ቻለ፡፡››



በኢትዮጵያ የወሎ ላሊበላ የባህል ሙዚቃ ቡድን በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ባህላዊ ሙዚቃዎች እንዲደመጡ እንደ ጎንደሩ ፋሲለደስ፣ እንደ ጎጃሙ ግሼ አባይ ያሉ የባህል ሙዚቃ ቡድኖች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆኗል ይላሉ የዜማ እና የግጥምደራሲው አርቲስት ዳምጤ መኮንን (ባቢ)፡፡



‹‹የወሎ ላሊበላ ባህል ቡድን ለኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃመመስረት አርአያ ነው፡፡ ብዙዎች የባህልቡድኖችየተመሰረቱት ከላሊበላ መመስረት በኋላ ነው፡፡ ለመድረክበቅተው የነበሩት ዚነት፤ ማሬዋ፣ በአልበምመምጣታቸውለሌሎቹ አርአያ ሆኗል፡፡ ከፋሲለደስ ፍቅርአዲስ ነቃጥበብ፣ አበበ ብርሃኔ፣ ከግሼ አባይ ይሁኔ በላይተገኝተዋል፡፡



ሌሎችምእኛን ተከትለው የመጡ ናቸው፡፡››



የወሎ ላሊበላ ባህል ቡድን የሀገር ባህል ተጫዋቾች ማህበርበሚል ስያሜ ሲመሰረት ማሲንቆን በመጠቀም በየአካባቢውያሉ ባህላዊ ሙዚቃዎች እንዲደመጡ አድርጓል፡፡



‹‹አባይ ቢሞላ አለው መላ መላ፣ ሆታ በጊዜው የወንድ ሙዚቃተጨዋች የለም ነበር፤ የሴትም ማሪቱ ነች፤ የገናንጨዋታምያስተዋወቅነው እኛ ነን፡፡››



ባህል ቡድኑ መነሻው ሀገረሰባዊ ሙዚቃዎች በመሆናቸውበቀዳሚነት የአርሶ አደሩን ባህር የሚገልፁ ስራዎች ነበርየሚሰራው የሚለው የቀድሞው የወሎ ላሊበላ የባህል ቡድንየድምፅ እና ምስል ቀረፃ ክፍለ ኃላፊ መስፍን ደምሴ ከሀገርፍቅር ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቲያትር ጋር በጋራ እንሰራለን ይላል፡፡



‹‹ከአርሶ አደሩ ጋር የተገናኙ አርሶ አደሩ የሚጠቀምባቸውእቃዎች ላዳ፣ መንሽ፣ ጀንዴ ባህሉን የሚጠቅስስራዎችንከአልባሳት ጀምሮ ይዘጋጃሉ፡፡ ከላይ ድጋፍ የሚሰጡን አገርፍቅር፣ ብሔራዊ ቲያትር ነበሩ፡፡››



በኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ ምልክት የሆኑ አራቱ(4) ቅኝቶችባቲ፣ አንችሆዬ፣ አምባሰል እና ትዝታ ቅኝቶችን በማስተዋወቅእና የኢትዮጵያ ሙዚቃ ምልክት እንዲሆኑ በማድረግ ረገድየወሎ ላሊበላ ቡድን አበርክቶው የላቀ ነው፡፡



‹‹የኢትዮጵያ አራቱ ቅኝቶች ወሎ ውስጥ ነው የሚገኙት ትዝታ ማለት ወሎ ማለት ነው፡፡ ደሴ ዙሪያ አካባቢይገኛል፤ ባቲ ደግሞ ከደሴ 60 ኪሎ ሜትር አምባሰልም ከደሴ 30/ሜ ርቀት የሚገኙ የወረዳ ከተሞች ናቸው፡፡አንችሆዬ ለእኔየአርበኛ ቅኝት ነው፡፡ ይህንን ለማስተዋወቅ የወሎ ላሊበላበተለይም ማሬዋ አራቱንም ቅኝቶችበአንድ ስኬልትጫወታለች፡፡ ከወሎ ላሊበላ በኋላ ነው ቅኝቶቹ ይዘታቸውምንነታቸው በደንብ የታወቀው፡፡››



የወሎ ላሊበላ የባህል ሙዚቃ መምጣት ዛሬ ለምንሰማቸውየባህላዊ ሙዚቃዎች መምጣት ምክንያት ነው የሚለውድምፃዊ መሀመድ ይመር ከመከም ሙዚቃ ቡድኑ ለቅኝቶችምመገኘት ሚናው የጎላ ነው ይላል፡፡



‹‹አስተዋጽዖው የላቀ ነው አሁን የሚተላለፉ ሙዚቃዎችመነሻ የወሎ ላሊበላ ነው፡፡ እነ እሪኩም፣ ቃሮዬ፣ከመከም፣አይናማ፣ አያ በለው በለው የሚያውቃቸው አልነበረም፡፡ የአራቱ ቅኝቶችም ከወሎ ላሊበላ በኋላ ነውየታወቁት፡፡››



የሙዚቃ ስራዎች ባህላዊ ይዘታቸውን ጠብቀው ባልባሳትጌጣጌጥ ተሟልተው ባህሉን አሟልተው እንዲቀርቡ ሰፊትኩረት ያለው ስራ ይሰራል የሚለው መስፍን ደምሴ በርካታባለሙያዎች የሚሳተፉበት ነበር ይላል፡፡



‹‹ለምሳሌ ዞብየን ስንሰራ ከሚሴ ተወዛዋዥና ዘፋኝ ይዘንሄደናል፡፡ ቱባ ባህሉን እናያለን ስራዎችን ወደመድረክምእናመጣለን፡፡ አፋርኛ ለመስራት ከአፋር ሰው እናመጣለንእንዲያሰለጥኑ፤ ኦሮሞኛምእንጨምርበታለን፤ ቋንቋውን አስተርጉመን ክትትል እናደርጋለን፤ ወሎ፣ ኦሮሞኛ፣ ትግርኛ፣ አገውኛ እንሰራለን፡፡››



በሙዚቃ ስራ ውስጥ ለሚከወን ውዝዋዜ አልባሳቱ፣ ጌጣጌጡበተለያዩ ገበያዎች ተፈልገው የሚገዙ ሲሆንጭፈራው፣ዜማው፣አልባሳቱ ባህላዊ መገኛቸውን ሳይለቁይሰራል፡፡





‹‹እያንዳንዱ ጌጣጌጥ አልባሳቱ ቱባ የሆነ ነው፡፡ የምንጠቀመው የፈትል ልብስ ነበር፤ ኦሪጂናል፤ መስቀሉ፣አምባሩ፣ደምብሉ፣ ማርዳው፣ ሁሉም ከእያንዳንዱገበያ ተፈልጎ ነበር የሚገዛው፤ ቱባ ባህሉን በማስተዋወቅለኢትዮጵያየባህል ሙዚቃ እድገት የላቀ አስተዋጽዖ አድርጓልወሎ ላሊበላ፡፡››



ከአማርኛ ውጭ በወሎ የሚዜሙ ዜማዎች በኦሮምኛ እና በሌሎች ቋንቋዎች የሚሰራው ድምፃዊ የወሎ ላሊበላ ቡድን አባል አሁን ላይ ባህላዊ መሰረታቸውን እየለቀቁ ሲዜሙእየሰማን ነው ይላል፡፡



‹‹እሪኩም ኦሮምኛ ነው፤ ከበደ ነበር ያመጣው እዚህ ግን እኛጥሩ አድርገን ሰራነው፡፡››



የወሎ ባህላዊ ሙዚቃን በመጫወት ረገድ ከወሎ ላሊበላምስረታ በፊት ባህሩ ቃኘው፣አሰፋ አባተን የመሰሉ ድምፃውያን ቢጫወቱትም የወሎ ላሊበላ መምጣት ግን የባህል ሙዚቃ አብዮቱን ቀይሯል ይላል አርቲስት ዳምጤ መኮንን(ባቢ)፡፡



‹‹ጋሽ ባህሩ፣ አሰፋ አባተ ከወሎ የፈለቁ አዝማሪዎችይጫወቱታል፤ የወሎን ሙዚቃ በማግነን ረገድ ግንከወሎላሊበላ ምስረታ በኋላ ነው ከፍ ብሎ የተጠራው፤ ባህል ቡድኑከፍተኛ አስተዋጽዖ አድርጓል፡፡››



የወሎ ላሊበላ ባህል ቡድን በ1983 ዓ/ም እንዲፈርስ ተደርጎየባህል ቡድኑ አባላት ቢበተኑ ከበርካታ አመታት ቆይታ በኋላምበደቡብ ወሎ ባህል ቱሪዝም መምሪያ እና ወሎ ዩኒቨርስቲ እንደአዲስ ተቋቁሙ ባህላዊ ሙዚቃዎችን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡



ኢሳያስ ገላው



ታምራት ዲንሳ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የወሎ ላሊበላ የባህል ሙዚቃ ቡድን ከትናንት ዛሬ

የወሎ ላሊበላ የባህል ሙዚቃ ቡድን ከትናንት ዛሬ