የዲጂታል ግንዛቤ “የጤና አልጎሪዝም” ድራማ
Update: 2025-11-22
Description
ይህ “የጤና አልጎሪዝም” የተሰኘው አዲስ እና ባለ 10 ክፍል የዶቸ ቬለ በማድመጥ መማር ድራማ ነው። በዲጂታል ቴክኖሎጂ ግንዛቤ ላይ የሚያተኩረው ድራማ ደራሲ ጄምስ ጄምስ ሙሐንዶ ይባላል። በዚህ ተከታታይ የራዲዮ ድራማ በፍጥነት እያደገ ወደ ሚገኘው የአርቴፊሺያል ኢንተለጀንስ ዓለም በመዝለቅ በዕለት ተለት ሕይወታችን ላይ ምን አይነት ተጽዕኖ እያሳደረ እንደሚገኝ ይመለከታል። አስር ክፍሎች ባሉት ድራማ ጀምበሬ፣ ራሒም እና እምነት በአንድ ፓርታማ በጋራ ወደሚኖሩባት ንቁዋ ኢንዙና ከተማ እንመለሳለን።
እምነት ሥራ የሚበዛበት እና በኢንተርኔት የምትማረክ መምህርት ናት። ራሒም የኮምፒዩተር ባለሙያ ሲሆን በማህበራዊ ኑሮው በጣም ግራ የሚያጋባ ነው። በአንፃሩ ጀምበሬ ግልፅ እና ተግባቢ ናት። በነፃ መንፈስ ለማህበራዊ ሚዲያ ይዘቶች ታቀርባለች።
ደራሲ፦ ጄምስ ሙሐንዶ
ተርጓሚ፦ እሸቴ በቀለ
ፕሮዲውሰር ፦ ልደት አበበ እና ሐና ደምሴ
Comments
In Channel























