ኢትዮጵያ ቀውስን በሚከታተለው ዓለም አቀፍ ተቋም 4ኛ ደረጃ ላይ ሰፈረች
Description
ኢትዮጵያ በሚቀጥለው የጎርጎሪዮሱ ዓመት የተባባሰ የሰብአዊ ቀውስ ይደርስባቸዋል ተብለው ከተዘረዘሩ 20 ሃገራት መካከል አራተኛ ደረጃ ላይ መስፈሯ ተገለጠ ። ይህን ይፋ ያደረገው፦ ዓለም አቀፍ ለችግር ደራሽ ኮሚቴ (IRC) የተባለ ድርጅት ነው ። ከተመሠረተ 93 ዓመታት ግድም ያስቆጠረው ድርጅቱ በመላው ዓለም ከሚገኙ 40 ሃገራት በላይ ውስጥ በተለያዩ ቀውሶች እና የተፈጥሮ አደጋዎች ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ድጋፍ በመስጠት ይታወቃል ።
ዓለም አቀፍ ድርጅቱ በቀጣዩ የጎርጎሪዮሱ ዓመት ሰብአዊ ቀውስ ሊባባስባቸው ይችላል ሲል በመገመት (the 2026 Emergency Watchlist) በሚል ርእስ ዘገባውን ትናንት (ታኅሣሥ 7 ቀን፣ 2018 ዓ.ም) ይፋ አድርጓል ። በድርጅቱ የክትትል ዕይታ ውስጥ ከሰፈሩ ሃገራት መካከል ቀውስ ሊባባስባት ይችላል ተብለ በቀዳሚነት የሰፈረችው አገር ሱዳን ናት ። ከሱዳን ተገንጥላ አገር የሆነችው ደቡብ ሱዳንም ሦስተኛ ደረጃ ላይ ሰፍራለች ።
በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ከበባ ውስጥ ያለው የጋዛ ግዛት ነው ተብሏል ። ዓለም አቀፍ ለችግር ደራሽ ኮሚቴ (IRC)ትናንት ይፋ ባደረገው ዘገባ መሠረት የከፋ ቀውስ ሊባባስባቸው አለያም ሊከሰትባቸው ይችላል ካላቸው ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ ከሥሯ ሔይቲን አስከትላ አራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች ። ባልደረባዬ እሸቴ በቀለን በዚህ ጉዳይ አነጋግሬዋለሁ ።
IRC እንደሚለው በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በግጭት በሚታመሱ አካባቢዎች ለችግር ተጋልጠው እንደሚገኙ ያመለክታል። በዘገባው ኢትዮጵያ በመጪው ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት ቀውስ ከሚባባስባቸው ሃገራት ዝርዝር በአራተኛ ደረጃ ትገኛለች ብሏል። ማሳያዎቹን ጠቅሶ ይሆን? ቀዳሚው ጥያቄ ነው ። ሌሎች ነጥቦችም ተነስተዋል
ሙሉ ቃለ መጠይቁን በማገናኛው ማድመጥ ይቻላል።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ
ሸዋዬ ለገሠ






















