የዶቼ ቬለ ነባር አድማጮች ፣ተሳታፊዎችና በተለያየ ሞያ የተሰማሩ ተከታታዮች አስተያየት
Update: 2025-04-06
Description
ላለፉት ስድስት አስርት ዓመታት ከመሀል አውሮጳ በአማርኛ ቋንቋ የሚያሰራጨው ዶቼ ቬለ በመላው ኢትዮጵያ እጅግ በርካታ አድማጮች ብሎም ተሳታፊዎች አሉት። የራዲዮ ስርጭቱ ከተጀመረ እኮ 60 ዓመት ሞላው በማለት አስተያየታቸውን እንዲያጋሩን ከጠይቀናቸው አንዱ ከአገር ቤት ጀምሬ እከታተለው ነበር ያሉን በጀርመን ብሎም በአውሮጳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መሥራች የሆኑት ሊቀካህናት ዶክተር መርዓዊ ተበጀ ናቸው። የዘወትር አድማጭና ተሳታፊያችን የመቶ አለቃ ውቤ ታሪኩም ከ40 ዓመታት በላይ ከዶቼ ቬለ ጋር ተጉዘዋል።
የዶቼ ቬለዉ አንጋፋ ጋዜጠኛ ይልማ ኃይለሚካኤል
አባቴ ካወረሰኝ አንዱ ዶቼ ቬለ ራዲዮ ነው ያሉን ደግሞ ከፍያለው መቀጫ ናቸው ከደቡብ ኢትዮጵያ፤ የዶቼ ቬለ አድማጮች ክበብ አቋቁመው ከ20 ዓመታት በላይ ከዶቼ ቬለ ጋር የዘለቁት ዋቆ ጉቱም ሌላው የረዥም ዓመት አድማጭ ናቸው። ለዓመታት የዶቼ ቬለን አድማጮች አስተያየት፣ ጥቆማና ጥያቄዎች ስታስተናግድ የነበረችው ንጋት ከተማም 60ኛ ዓመቱ አስመልክታ መልእክቷን አስተላልፋለች። ከተለያዩ ቦታዎች በልዩ ልዩ ሙያ ውስጥ ካሉ አድማጮች ያሰባሰብናቸው አስተያየቶችም አሉን ።
ሸዋዩ ከገሠ / ሰሎሞን ሙጬ
ነጋሽ መሐመድ/ኂሩት መለሰ
Comments
In Channel