DiscoverDW | Amharic - Newsየጀርመን ፈጣን የዜግነት ሕግ ለምን ተሰረዘ?
የጀርመን ፈጣን የዜግነት ሕግ ለምን ተሰረዘ?

የጀርመን ፈጣን የዜግነት ሕግ ለምን ተሰረዘ?

Update: 2025-10-14
Share

Description

ከጎርጎሮሳዊው ሰኔ 2024 ዓ.ም. በፊት የውጭ ዜጎች የጀርመን ዜግነት ለማግኘት ቢያንስ ስምንት ዓመት መጠበቅ ነበረባቸው።ይሁንና በጎርጎሮሳዊው 2021 ስልጣን በያዘው የጀርመን መንግሥት የውጭ ዜጎች የጀርመን ዜግነት ለማግኘት ጀርመን መኖር ያለባቸው ጊዜ እንዲያጥር ተደረገ። ያኔ ተጣምረው ሀገሪቱን ይመሩ የነበሩት የመሀል ግራው የሶሻል ዴሞክራቶቹ ፓርቲ እንዲሁም አጋሮቹ ለአካባቢ ጥበቃ የሚቆመው የአረንጓዴዎቹ ፓርቲ፣ እና ነጻ ገበያን የሚያራምደው የነፃ ዴሞክራቶቹ ፓርቲ የውጭ ዜጎች ከ5 ዓመታት የጀርመን ቆይታ በኋላ የጀርመን ዜግነት ለማግኘት ማመልከት እንደሚችሉ ወሰነ። በፍጥነት ከኅብረተሰቡ ጋር ተሳልጠው መኖር ለቻሉት ደግሞ ከ3 ዓመት በኋላ ዜግነት እንዲሰጣቸው ፈቀደ። እነዚህኛዎቹ አመልካቾች በቂ ገቢ ፣ ከፍተኛ የጀርመንኛ ቋንቋ ችሎታ እና ከኅብረተሰቡ ጋር የተዋሀዱ ለምሳሌ በበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችና በመሰል ተግባራት ላይ የሚሳተፉ መሆናቸውን የሚሳይ ማረጋገጫ ማቅረብ ይጠበቅባቸው ነበር።



በመራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልስ ይመራ የነበረው የቀደመው የጀርመን መንግሥት በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠነ የውጭ የሰው ኃይልን ለመሳብ አልሞ ነበር ከአንድ ዓመት በፊት ይህን ሕግ ያወጣው ። ይሁንና በጎርጎሮሳዊው ግንቦት 2025 ዓ.ም. ሥልጣን የያዘው አዲሱ የክርስቲያን ዴሞክራት ኅብረት ፓርቲ በምህጻሩ CDU እና እህት ፓርቲው የክርስቲያን ሶሻል ኅብረት ፓርቲ CSU እንዲሁም የሶሻል ዴሞክራቶቹ ፓርቲ SPD የመሰረቱት ጥምር መንግሥት ፈጣኑ የዜግነት አሰጣጥ ሕግ እንዲሰረዝ ተስማምቶ ረቂቅ ሕጉ ለቡንደስታግ ከተመራ በኋላ ምክርቤቱም የሕጉን መሰረዝ አጽድቋል።



ለመሆኑ መጀመሪያውኑ ይህ ሕግ እንዴት ተግባራዊ ሆነ ? ለምንስ ተሰረዘ? ጀርመን የተማሩትን የሕግ ባለሞያና የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ዶክተር ለማ ይፍራሸዋ ያቀረብነው ጥያቄ ነው። ዶክተር ለማ ለጥያቄአችን መልስ የሰጡት ከቀድሞው የዜግነት ሕግ አሰጣጥ በመነሳት ነው። በፈጣኑ የጀርመን የዜግነት አሰጣጥ ላይ አስተያየታቸውን የጠየቅናቸው የምጣኔ ሀብት ምሁርና የአስተዳደር ባለሞያ ዶክተር ፀጋዬ ደግነህ በበኩላቸው በጀርመናውያን ዘንድ ፈጣኑ የዜግነት አሰጣጥ ሕግ ያን ያህል ተቀባይነት ማግኘቱ አጠራጣሪ መሆኑን ጠቁመዋል። ከዚሁ ጋር ኅብረተሰቡ ብዙም ያልተቀበላቸው የሚመስሉት ይህና መሰል ሕጎች ቀኝ ጽንፈኞች ከከዚህ ቀደሙ የበለጠ ድምጽ እንዲያገኙ አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆኑንም ሳያነሱ አላለፉም።



ፈጣኑ የዜግነት አሰጣጥ ሕግ ከወግ አጥባቂዎቹ ቡድን ጠንካራ ተቃውሞ ከተነሳበት በኋላ ሲሰረዝ የውጭ ዜጎች የጀርመን ዜግነት ለማግኘት ጀርመን መኖር ያለባቸው አነስተኛው ጊዜ ወደ አምስት ዓመት ከፍ ብሏል። በውሳኔው የጀርመን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተበሳጭተዋል። የአረንጓዴዎቹ ፓርቲ ሊቀ መንበር ፌሊክስ ባናስዛክ እርምጃውን በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠነ የሰው ኃይል እጅግ ለሚያስፈልጋት ስለጀርመን የተሳሰተ መልዕክት የሚያስተላልፍ ሲሉ ተችተዋል። ባናስዛክ የዛሬ አንድ ዓመት የተደረገው ማሻሻያ ጀርመንን ይበልጥ ያዘመነ ግልጽ እና ይበልጥ ፍትሀዊ ያደረገ ነበር ሲሉ አወድሰዋል።



ከግራዎቹ ፓርቲ ክላራ ቡንገር ደግሞ የ ፈጣኑ የዜግነት አሰጣጥ ሕግ ስራ ላይ በነበረበት ወቅት አመልክተው ውጤቱን በመጠባበቅ ላይ ያሉ ነገር ግን ውሳኔ ያልተሰጣቸው ብዙ ሰዎች ላይ ተጽእኖ ማሳደሩ አይቀርም ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል። ዶክተር ለማ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በሕጉ መሰረዝ ላይ ስለሰነዘሩት ነቀፋም አስተያየታቸውን አካፍለውናል። በጉዳዩ ላይ የጀርመን ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት ባካሄደው ክርክር፣ የክርስቲያን ሶሻል ኅብረት ፓርቲ ፖለቲከኛ የጀርመን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ዶብሪንት የውጭ ዜጎች በሦስት ዓመት ዜግነት እንዲያገኙ ያስችል የነበረውን ሕግ የተሳሳተ ማበረታቻ ሲሉ አጣጥለዋል።





የዶቼቬለ ባልደረባ የማርሴል ፍርስቱናው ዘገባ እንደሚለው ሕጉ ስራ ላይ ከዋለ ከ15 ወራት በኋላ ጀርመን ከሚኖሩ የውጭ ዜጎችአስፈላጊውን የቋንቋ ችሎታ እና የገቢ መጠን ያሟሉት 13 በመቶ ብቻ ናቸው። በአሁኑ ጊዜ የውጭ ዜጎች የጀርመን ዜግነት ለማግኘት የሚያስገቡዋቸው ማመልከቻዎች ቶሎ መልስ እንደማያገኙ ነው ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ባለሞያዎች የሚናገሩት። ዶቼቬለ ያነጋገራቸው ጃኔስ ጃኮብሰን የተባሉ መቀመጫውን ጀርመን ያደረገ የውህደትና የፍልሰት ጥናት ማዕከል ባልደረባ የተጓተተ ባሉት የጀርመን ቢሮክራሲ ምክንያት የዜግነት ማመልክቻ በአጭር ጊዜ መልስ ላያገኝ ይችላል። እየጨመረ የመጣው የዜግነት ማመልከቻም በብዙ ሂደት የሚያልፍና ጊዜም የሚጠይቅ ነው።



እርሳቸው እንዳሉት እድል የቀናቸው አመልካቾች በስድስት ወራት መልስ ሊያገኙ ይችሉ ይሆናል። ያልቀናቸው ደግሞ ከአራት ዓመት በላይ ሊጠብቁ ይችላሉ። ይህም በሠራተኛ ኃይል እጥረት ምክንያት የሚከሰት መሆኑን ባለሞያው አስረድተዋል። በጃኮብሰን አስተያየት ለውጭ ዜጎች የትምሕርት ማስረጃዎች እውቅና የመስጠቱ ሂደትም ሊቃለል ይገባል።

ባለፈው ሳምንት በተሰዘረው በፈጣኑ የጀርመን ዜግte አሰጣጥ ሕግ ላይ ያተኮረው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን በዚሁ ያበቃል ።



ኂሩት መለሰ

ታምራት ዲንሳ

Comments 
In Channel
loading
00:00
00:00
x

0.5x

0.8x

1.0x

1.25x

1.5x

2.0x

3.0x

Sleep Timer

Off

End of Episode

5 Minutes

10 Minutes

15 Minutes

30 Minutes

45 Minutes

60 Minutes

120 Minutes

የጀርመን ፈጣን የዜግነት ሕግ ለምን ተሰረዘ?

የጀርመን ፈጣን የዜግነት ሕግ ለምን ተሰረዘ?